የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 10/12 ገጽ 3
  • ተነሳሽነት ይኑርህ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ተነሳሽነት ይኑርህ
  • ንቁ!—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ትምህርት ቢያስጠላኝስ?
    የወጣቶች ጥያቄ
  • ወደ ትምህርት ቤት እየሄድህ መማር ያለብህ ለምንድን ነው?
    ወጣትነትህን በተሻለ መንገድ ተጠቀምበት
  • ትምህርቴን ማቋረጥ ይኖርብኛልን?
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች
  • የትምህርት ቤት ሕይወታችሁን በተሻለ መንገድ ተጠቀሙበት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2012
g 10/12 ገጽ 3

ተነሳሽነት ይኑርህ

ለማንኛውም ነገር ተነሳሽነቱ እንዲኖርህ በቅድሚያ ጠቀሜታውን መገንዘብ ይኖርብሃል።

መማር ምን ጥቅም ያስገኛል? ትምህርት ጥበብ እንድታገኝ የሚረዳህ ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ “ጥበብ ጥላ ከለላ ነው” በማለት ይናገራል። (መክብብ 7:12) እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? ለምሳሌ፣ በአንድ አደገኛ አካባቢ በእግር እየተጓዝክ ነው እንበል። ታዲያ በዚህ ወቅት ብቻህን ብትሆን ይሻልሃል? ወይስ አንድ አደጋ ቢፈጠር እንኳ ሊጠብቁህ ከሚችሉ ጓደኞችህ ጋር ብትሄድ ትመርጣለህ? መሠረታዊ የሆነ ጥሩ ትምህርት ቀሰምክ ማለትም ምንጊዜም ከአንተ የማይለዩ “ጓደኞች” አፈራህ ማለት ነው። እነሱም የሚከተሉት ናቸው፦

  • የማሰብ ችሎታ፦ ትምህርት ቤት ገብተህ መማርህ መጽሐፍ ቅዱስ “ማስተዋልና የማመዛዘን ችሎታ” በማለት የሚጠራቸውን ባሕርያት እንድታዳብር ሊረዳህ ይችላል። (ምሳሌ 3:21 ኮንቴምፖራሪ ኢንግሊሽ ቨርዥን) እነዚህን ችሎታዎች ማዳበርህ ደግሞ ሁልጊዜ የሌሎችን እርዳታ ከመጠበቅ ይልቅ የሚያጋጥሙህን ችግሮች ራስህ መፍታት እንድትችል ይረዳሃል።

  • ከሰዎች ጋር የመግባባት ችሎታ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያኖች እንደ ትዕግሥትና ራስን መግዛት ያሉ ባሕርያትን እንዲያዳብሩ ይመክራል። (ገላትያ 5:22, 23) በትምህርት ቤት ከተለያዩ ልጆች ጋር ጊዜ ማሳለፍህ ትልቅ ሰው ስትሆን በጣም የሚጠቅሙህን እነዚህን ባሕርያት ጨምሮ እንደ መቻቻል፣ ለሌሎች አክብሮት ማሳየትና መራራት የመሳሰሉ ግሩም ባሕርያትን እንድታዳብር ጥሩ አጋጣሚ ይከፍትልሃል።

  • ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ሥልጠና፦ ትምህርት ጥሩ የሥራ ባሕል ያለውን ጠቀሜታ እንድትገነዘብ የሚያደርግህ ሲሆን ይህ ደግሞ ሥራ ለማግኘትና ሥራውን እንደያዝክ ለመቀጠል ይረዳሃል። በተጨማሪም በዙሪያህ ስላለው ዓለም ብዙ ባወቅህ መጠን ስለ ማንነትህና ስለምታምንበት ነገር የተሻለ ግንዛቤ ይኖርሃል። (ምሳሌ 14:15) እንዲህ ዓይነት ጠንካራ እምነት ካለህ ደግሞ አክብሮት በተሞላበት መንገድ ስለምታምንባቸው ነገሮች ለሌሎች ማስረዳት ትችላለህ።—1 ጴጥሮስ 3:15

ዋናው ነጥብ፦ ትምህርት እንዲህ ያለ ጠቀሜታ የሚያስገኝልህ ከሆነ ትምህርትን እንድትጠላ በሚያደርጉ ነገሮች ላይ ማብሰልሰልህ ምንም ፋይዳ የለውም። ከዚህ ይልቅ ከላይ የተገለጹትን እንድትማር የሚገፋፉ ምክንያቶች በማሰብ ለመማር ተነሳሳ። መማር የሚያስገኛቸውን ሌሎች ጥቅሞችም ማሰብ ትችላለህ።

አሁኑኑ ለምን አትጀምርም? በግለሰብ ደረጃ ለመማር እንድትነሳሳ የሚያደርግህን ዋነኛ ምክንያት ለማሰብ ሞክር።

ጥሩ አስተማሪዎች አድናቆት ያተርፋሉ!

“ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሳለሁ ኢኮኖሚክስ አስተማሪያችን በአንድ ትልቅ የገንዘብ ተቋም ውስጥ መሥራት የሚችል ሰው የነበረ ቢሆንም አነስተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች የመጡ ልጆች በሚማሩበት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስተማር መርጦ ነበር፤ በዚህ ላይ ደግሞ አብዛኞቹ ልጆች ስለ ኢኮኖሚክስ ምንም ደንታ አልነበራቸውም። ያም ሆኖ ትምህርቱን ቀላል በሆነ መንገድ፣ በቀልድ እያዋዛና የትምህርቱን ጥቅም እንድንረዳ በሚያስችል ሁኔታ ያስተምረን ነበር። እንዲያውም በአንድ ወቅት እንድንጽፍ ያዘዘንን መጣጥፍ ጥሩ አድርጌ በመጻፌ ለእናቴ ስልክ ደውሎ ነግሯት ነበር። በሌላ ጊዜ ደግሞ በትምህርት ቤታችን ለማስተማር የመረጠው ለምን እንደሆነ ተማሪዎች ሲጠይቁት ይህን ሥራ ከዚህ በፊት ከሠራቸው ሥራዎች ሁሉ አስበልጦ እንደሚወደው ተናግሯል። ስሜታችንን ይረዳልንና ያስብልን የነበረ ከመሆኑም በላይ ያመሰግነን ነበር። ካስተማሩኝ አስተማሪዎች ሁሉ የማደንቀው እሱን ነው!”—ሬየን፣ ዩናይትድ ስቴትስ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ