የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 2/13 ገጽ 3
  • ከዓለም አካባቢ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከዓለም አካባቢ
  • ንቁ!—2013
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እስራኤል
  • አውስትራሊያ
  • ግሪክ
  • ዩናይትድ ስቴትስ
  • ማዳጋስካር
  • መጽሐፍ ቅዱስን የምታውቀው ምን ያህል ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ይሖዋን ለማገልገል ቆርጠናል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • ለመንሸራተት ከሚያስችል “ምቹ ማዕበል” የበለጠ ነገር
    ንቁ!—2007
  • ወርቅ ፍለጋ ሄደው አገር አገኙ
    ንቁ!—2011
ንቁ!—2013
g 2/13 ገጽ 3

ከዓለም አካባቢ

እስራኤል

Haaretz.com የተባለው ድረ ገጽ እንደዘገበው ከአሁን በኋላ “ከወሊድ በፊት ሊታወቅ የሚችል የጤና እክል ይዘው የሚወለዱ” ልጆች አካል ጉዳተኞች እንደሚሆኑ እያወቁ እንዲወለዱ ያደረጓቸውን የሕክምና ባለሙያዎች መክሰስ አይችሉም። ይሁንና ወላጆች “አካል ጉዳተኛ የሆነን ልጅ ለማሳደግና በመላው ሕይወቱ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ለማሟላት ተጨማሪ ወጪ” ስለሚያስወጣ ካሳ ለመጠየቅ ክስ መመሥረት ይችላሉ።

አውስትራሊያ

በአውስትራሊያ ከ10 ጥንዶች መካከል 8ቱ አብረው መኖር የጀመሩት ሳይጋቡ በፊት ነው።

ግሪክ

የግሪክ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ያወጣው አኃዛዊ መረጃ እንዳመለከተው በግሪክ በ2011 በመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት ውስጥ ራሳቸውን ያጠፉት ሰዎች ቁጥር በ2010 በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ሕይወታቸውን ካጠፉት ጋር ሲወዳደር 40 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ይህ ጭማሪ የታየው የ2011 የኢኮኖሚ ቀውስ በተከሰተበት ወቅት ላይ ነው።

ዩናይትድ ስቴትስ

ከተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን የሚያከናውነው ቢሮ እንደገለጸው በአገሪቱ 40 በመቶ ገደማ የሚያህል ምግብ ይባክናል። ለምሳሌ 7 በመቶ የሚሆነው ሰብል እንደማይታጨድ፣ በምግብ ቤቶችና በሻይ ቤቶች ውስጥ ከሚቀርበው ምግብ 17 በመቶ የሚሆነው እንደማይበላ እንዲሁም ቤተሰቦች ከሚሸምቱት የምግብ ሸቀጥ ውስጥ 25 በመቶ የሚሆነውን እንደሚጥሉት ተገምቷል።

ማዳጋስካር

በዓለም ላይ ትንሿ እስስት በቅርቡ በማዳጋስካር ተገኝታለች። ቡኒ ቀለም ያላቸው እነዚህ ትናንሽ የእንሽላሊት ዝርያዎች 29 ሚሊ ሜትር ድረስ የሚያድጉ ሲሆን ተመቻችተው ለመቀመጥ የጣት ጥፍር የሚያህል ቦታ ይበቃቸዋል። ይህች እንስሳ፣ ሰዎች በመኖሪያዋ ላይ በሚያደርሱት ጥፋት የተነሳ ከምድር ገጽ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባታል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ