የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • gf ትምህርት 3 ገጽ 5
  • ስለ አምላክ መማር ይኖርብሃል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ስለ አምላክ መማር ይኖርብሃል
  • የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የይሖዋ ወዳጅ መሆን ትችላለህ
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • አምላክ ወዳጁ እንድትሆን ይጋብዝሃል
    የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
  • እውነተኛውን ሃይማኖት ማግኘት የሚቻልበት መንገድ
    የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
  • ወዳጆች ማፍራት የምትችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
ለተጨማሪ መረጃ
የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
gf ትምህርት 3 ገጽ 5

ትምህርት 3

ስለ አምላክ መማር ይኖርብሃል

የአምላክ ወዳጅ ለመሆን ከፈለግህ ስለ እርሱ መማር ይኖርብሃል። ወዳጆችህ ስምህን ያውቁታል? በስምህስ ይጠሩሃል? አዎን። አምላክም ስሙን እንድታውቅና ስሙን እንድትጠራ ይፈልጋል። የአምላክ ስም ይሖዋ ነው። (መዝሙር 83:18 NW፤ ማቴዎስ 6:9) ከዚህም በተጨማሪ አምላክ ስለሚወድደውና ስለሚጠላው ነገር መማር አለብህ። ወዳጆቹንና ጠላቶቹን ለይተህ ማወቅ ይኖርብሃል። አንድን ሰው በደንብ ለማወቅ ጊዜ ይጠይቃል። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ይሖዋ ለመማር ጊዜ መመደብ ጥበብ እንደሆነ ይናገራል።—ኤፌሶን 5:15, 16

የአምላክ ወዳጆች እርሱን የሚያስደስቱትን ነገሮች ያደርጋሉ። እስቲ ስለ ወዳጆችህ አስብ። መጥፎ ባሕርይ የምታሳያቸውና የማይወዱትን ነገር የምታደርግ ብትሆን ከአንተ ጋር ያላቸውን ወዳጅነት የሚቀጥሉ ይመስልሃል? በፍጹም! በተመሳሳይም የአምላክ ወዳጅ መሆን ከፈለግህ እርሱን የሚያስደስተውን ነገር ማድረግ ይኖርብሃል።—ዮሐንስ 4:24

ጠባብ በሆነ በር ላይ የቆመ አንድ ቤተሰብ በቀጭን መንገድ ላይ  የሚጓዙ ሰዎችን እየተመለከተ

ከአምላክ ጋር ወዳጅነት እንድትመሠርት የሚረዱህ ሁሉም ሃይማኖቶች አይደሉም። የአምላክ የቅርብ ወዳጅ የሆነው ኢየሱስ ስለ ሁለት መንገዶች ተናግሯል። አንደኛው መንገድ ሰፊና በሰዎች የተሞላ ነው። ይህ መንገድ ወደ ጥፋት ይወስዳል። ሌላኛው መንገድ ደግሞ ጠባብ ሲሆን የሚጓዙበትም ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው። ይህ መንገድ ወደ ዘላለም ሕይወት ይወስዳል። ይህም የአምላክ ወዳጅ ለመሆን የምትፈልግ ከሆነ እርሱ የሚመለክበትን ትክክለኛ መንገድ መማር አለብህ ማለት ነው።—ማቴዎስ 7:13, 14

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ