የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • gf ትምህርት 10 ገጽ 16-17
  • እውነተኛውን ሃይማኖት ማግኘት የሚቻልበት መንገድ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እውነተኛውን ሃይማኖት ማግኘት የሚቻልበት መንገድ
  • የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ የሚቀበለው አምልኮ
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • እውነተኛውን ሃይማኖት ለይቶ ማወቅ
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
  • ከሐሰት ሃይማኖት ራቅ!
    የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
  • እውነተኛውን ሃይማኖት ማግኘት የምችለው እንዴት ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ለተጨማሪ መረጃ
የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
gf ትምህርት 10 ገጽ 16-17

ትምህርት 10

እውነተኛውን ሃይማኖት ማግኘት የሚቻልበት መንገድ

የአምላክ ወዳጅ ለመሆን የምትፈልግ ከሆነ አምላክ በሚቀበለው ሃይማኖት መመላለስ አለብህ። ኢየሱስ ‘እውነተኛ አምላኪዎች’ አምላክን ‘ከእውነት’ ጋር በሚስማማ መንገድ እንደሚያመልኩ ተናግሯል። (ዮሐንስ 4:23, 24) አምላክን ለማምለክ የሚያስችለው ትክክለኛው መንገድ አንድ ብቻ ነው። (ኤፌሶን 4:4-6) እውነተኛ ሃይማኖት ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስድ ሲሆን ሐሰተኛ ሃይማኖት ደግሞ ወደ ጥፋት ይወስዳል።—ማቴዎስ 7:13, 14

የተወሰኑ ሰዎች በአካባቢያቸው የሚገኝን አንድ የይሖዋ ምሥክር ሲመለከቱ

ተከታዮቹን በመመልከት እውነተኛውን ሃይማኖት ለይተህ ማወቅ ትችላለህ። ይሖዋ ጥሩ ስለሆነ የእርሱ እውነተኛ አምላኪዎችም ጥሩ ሰዎች መሆን አለባቸው። ጥሩ የብርቱካን ዛፍ መልካም ብርቱካኖችን እንደሚያፈራ ሁሉ እውነተኛ ሃይማኖትም ጥሩ ሰዎችን ያፈራል።—ማቴዎስ 7:15-20

የይሖዋ ወዳጆች ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥልቅ አክብሮት አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ ከአምላክ የተገኘ እንደሆነ ያውቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ነገር ለሕይወታቸው መመሪያ እንዲሆናቸው፣ ለችግሮቻቸው መፍትሄ እንዲያስገኝላቸውና ስለ አምላክ እንዲማሩ እንዲረዳቸው ይፈቅዱለታል። (2 ጢሞቴዎስ 3:16) መስበክ ብቻ ሳይሆን የሚሰብኩትን ነገር በሥራ ላይ ለማዋል ይጥራሉ።

የይሖዋ ወዳጆች እርስ በርሳቸው ይዋደዳሉ። ኢየሱስ ስለ አምላክ በማስተማርና የታመሙትን በመፈወስ ለሰዎች ፍቅር እንዳለው አሳይቷል። በእውነተኛው ሃይማኖት ውስጥ የሚመላለሱ ሰዎችም ለሌሎች ፍቅር ያሳያሉ። እንደ ኢየሱስ ሁሉ እነሱም ድሃ የሆኑ ወይም የተለየ ዘር ያላቸውን ሰዎች አይንቁም። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ እርስ በርሳቸው በሚያሳዩት ፍቅር ተለይተው እንደሚታወቁ ተናግሯል።—ዮሐንስ 13:35

የአምላክ ወዳጆች ይሖዋ ለሚለው የአምላክ ስም አክብሮት አላቸው። በስምህ ሊጠራህ የማይፈልግ ሰው የቅርብ ወዳጅህ ሊሆን ይችላልን? በጭራሽ! ወዳጅ ካለን በስሙ እንጠራዋለን እንዲሁም ስለዚህ ወዳጅ ጥሩ የሆኑ ነገሮችን ለሌሎች እንናገራለን። ስለዚህ የአምላክ ወዳጅ ለመሆን የሚፈልጉ ሁሉ በስሙ መጠቀምና ስለ እርሱ ለሌሎች መናገር ይኖርባቸዋል። ይሖዋ እንዲህ እንድናደርግ ይፈልጋል።—ማቴዎስ 6:9፤ ሮሜ 10:13, 14

ልክ እንደ ኢየሱስ የአምላክ ወዳጆች ስለ አምላክ መንግሥት ለሰዎች ያስተምራሉ። የአምላክ መንግሥት ምድርን ገነት የሚያደርግ በሰማይ የሚገኝ መስተዳድር ነው። የአምላክ ወዳጆች ስለ አምላክ መንግሥት የሚናገረውን ይህን ምሥራች ለሌሎች ያካፍላሉ።—ማቴዎስ 24:14

የይሖዋ ምሥክሮች የአምላክ ወዳጅ ለመሆን ይጥራሉ። የይሖዋ ምሥክሮች ለመጽሐፍ ቅዱስ አክብሮት አላቸው እንዲሁም እርስ በርስ ይዋደዳሉ። በተጨማሪም በአምላክ ስም ይጠቀማሉ፣ ያከብራሉ እንዲሁም ስለ አምላክ መንግሥት ለሌሎች ያስተምራሉ። በዛሬው ጊዜ በምድር ላይ በእውነተኛው ሃይማኖት እየተመላለሱ ያሉት የይሖዋ ምሥክሮች ናቸው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ