የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • gf ትምህርት 11 ገጽ 18-19
  • ከሐሰት ሃይማኖት ራቅ!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከሐሰት ሃይማኖት ራቅ!
  • የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሐሰት ሃይማኖቶች የአምላክን ስም ያሰደቡት እንዴት ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • የሐሰት ሃይማኖት የሚጠፋበት ጊዜ ቀርቧል!
    የሐሰት ሃይማኖት የሚጠፋበት ጊዜ ቀርቧል!
  • አምላክ ሁሉንም ሃይማኖቶች ይቀበላል?
    ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን መንገድ አግኝተኸዋል?
  • ከሐሰት ሃይማኖት መላቀቅ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
ለተጨማሪ መረጃ
የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
gf ትምህርት 11 ገጽ 18-19

ትምህርት 11

ከሐሰት ሃይማኖት ራቅ!

ሰይጣንና አጋንንቱ አምላክን እንድታገለግል አይፈልጉም። ከቻሉ ሁሉንም ሰው ከአምላክ ለማራቅ ይፈልጋሉ። ይህን ለማድረግ የሚሞክሩት እንዴት ነው? አንደኛው መንገድ በሐሰት ሃይማኖት አማካኝነት ነው። (2 ቆሮንቶስ 11:13-15) አንድ ሃይማኖት ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነትን የማያስተምር ከሆነ ሐሰተኛ ነው። የሐሰት ሃይማኖት ከሐሰት የብር ኖት ጋር ይመሳሰላል። የብር ኖቱ ሲያዩት ትክክለኛ ገንዘብ ይመስላል፤ ሆኖም ዋጋ የለውም። ከባድ ችግር ውስጥ ሊከትህ ይችላል።

አንድ ባልና ሚስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲጸልዩ

የሐሰት ሃይማኖት የእውነት አምላክ የሆነውን ይሖዋን ፈጽሞ አያስደስተውም። ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ጊዜ እርሱን ለመግደል የሚፈልግ አንድ የሃይማኖት ቡድን ነበር። ይከተሉት የነበረው የአምልኮ መንገድ ትክክለኛ እንደሆነ አድርገው ያስቡ ነበር። “አንድ አባት አለን እርሱም እግዚአብሔር ነው” ይሉ ነበር። ታዲያ ኢየሱስ በዚህ አባባላቸው ተስማማ? በጭራሽ! “እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ” አላቸው። (ዮሐንስ 8:41, 44) በዛሬው ጊዜ ያሉ ብዙ ሰዎች አምላክን እያመለኩ እንዳሉ ሆኖ ይሰማቸዋል። ሆኖም በእርግጥ እያመለኩ ያሉት ሰይጣንንና አጋንንቱን ነው!—1 ቆሮንቶስ 10:20

ክፉ ዛፍ መጥፎ ፍሬ እንደሚያፈራ ሁሉ የሐሰት ሃይማኖትም መጥፎ ነገር የሚሠሩ ሰዎችን ያፈራል። ሰዎች በሚፈጽሟቸው መጥፎ ተግባሮች ምክንያት ዓለም በችግር ተሞልታለች። የሥነ ምግባር ብልግና፣ ጥል፣ ስርቆት፣ ጭቆና፣ ነፍስ ግድያና አስገድዶ መድፈር አለ። እነዚህን መጥፎ ድርጊቶች የሚፈጽሙ ብዙዎቹ ሰዎች ሃይማኖት ያላቸው ቢሆንም ሃይማኖታቸው መልካም የሆነውን እንዲያደርጉ አያንቀሳቅሳቸውም። መጥፎ የሆኑ ነገሮችን መሥራት እስካላቆሙ ድረስ የአምላክ ወዳጆች መሆን አይችሉም።—ማቴዎስ 7:17, 18

የሐሰት ሃይማኖት ሰዎች ለጣዖታት እንዲጸልዩ ያስተምራል። አምላክ ለጣዖታት መጸለይን ይከለክላል። ይህ ደግሞ ምክንያታዊ ነው። አንድ ሰው አንተን ሳይሆን ፎቶህን ብቻ ማነጋገር ቢፈልግ ደስ ይልሃል? ይህ ሰው እውነተኛ ወዳጅህ ሊሆን ይችላል? በጭራሽ ሊሆን አይችልም። ይሖዋ ሰዎች ሕይወት ለሌለው ምስል ወይም ሥዕል እንዲናገሩ ሳይሆን እርሱን እንዲያነጋግሩ ይፈልጋል።—ዘጸአት 20:4, 5

ጠመንጃ የያዙ ወታደሮች

የሐሰት ሃይማኖት በጦርነት ጊዜ ሰዎችን መግደል ምንም ስህተት እንደሌለው ያስተምራል። ኢየሱስ የአምላክ ወዳጆች እርስ በርሳቸው እንደሚዋደዱ ተናግሯል። የምንወዳቸውን ሰዎች አንገድላቸውም። (ዮሐንስ 13:35) መጥፎ ሰዎችን መግደል እንኳ ስህተት ነው። ኢየሱስ ጠላቶቹ ሊይዙት በመጡ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ እርሱን ለማስጣል ብለው እንዲዋጉ አልፈቀደም።—ማቴዎስ 26:51, 52

የሐሰት ሃይማኖት ክፉ ሰዎች በሲኦል እሳት እንደሚሠቃዩ ያስተምራል። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ የኃጢአት ውጤት ሞት እንደሆነ ይናገራል። (ሮሜ 6:23) ይሖዋ የፍቅር አምላክ ነው። አፍቃሪ የሆነ አምላክ ሰዎችን ለዘላለም ያሠቃያል? በጭራሽ እንደዚያ አያደርግም! በገነት ውስጥ ይሖዋ የሚቀበለው አንድ ሃይማኖት ብቻ ይኖራል። (ራእይ 15:4) በሰይጣን ውሸቶች ላይ የተመሠረቱ ሃይማኖቶች በሙሉ ይጠፋሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ