የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • gf ትምህርት 17 ገጽ 28-29
  • ወዳጅነትህን ጠብቀህ ለማቆየት አንተ ራስህ ወዳጅ መሆን አለብህ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ወዳጅነትህን ጠብቀህ ለማቆየት አንተ ራስህ ወዳጅ መሆን አለብህ
  • የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአምላክ ፍቅር ለዘላለም ይኖራል
    ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ ኑሩ
  • የምትገነባው በአሸዋ ላይ ነው ወይስ በዓለት ላይ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • “አምላክን መውደድ” ሲባል ምን ማለት ነው?
    ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
  • “ወዳጆች ብዬ ጠርቻችኋለሁ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020
ለተጨማሪ መረጃ
የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
gf ትምህርት 17 ገጽ 28-29

ትምህርት 17

ወዳጅነትህን ጠብቀህ ለማቆየት አንተ ራስህ ወዳጅ መሆን አለብህ

ወዳጅነት በፍቅር ላይ የተመሠረተ ነው። ስለ ይሖዋ ይበልጥ እየተማርክ በሄድክ መጠን ለእርሱ የሚኖርህ ፍቅር የዚያኑ ያህል እያደገ ይሄዳል። ለአምላክ ያለህ ፍቅር እያደገ ሲሄድ እርሱን ለማገልገል ያለህ ፍላጎትም እያደገ ይሄዳል። ይህም የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር እንድትሆን ይገፋፋሃል። (ማቴዎስ 28:19) ከይሖዋ ምሥክሮች ደስተኛ ቤተሰብ ጋር በመቀላቀል ከይሖዋ ጋር ያለህን ወዳጅነት ለዘላለም ጠብቀህ ማቆየት ትችላለህ። ታዲያ ምን ማድረግ አለብህ?

የአምላክን ሕግጋት በመጠበቅ ለአምላክ ፍቅር እንዳለህ ማሳየት ይገባሃል። “ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።”—1 ዮሐንስ 5:3

የተማርካቸውን ነገሮች በሥራ ላይ አውል። ኢየሱስ ይህንን ጉዳይ በምሳሌ ለማስረዳት አንድ ታሪክ ተናግሯል። አንድ ጠቢብ ሰው ቤቱን በዓለት ላይ ሠራ። አንድ ሰነፍ ሰው ደግሞ ቤቱን በአሸዋ ላይ ሠራ። ከባድ ዝናብ በዘነበ ጊዜ በዓለት ላይ የተሠራው ቤት ከመፍረስ ተረፈ። በአሸዋ ላይ የተሠራው ግን ሙሉ በሙሉ ፈረሰ። ኢየሱስ ትምህርቱን ሰምተው የሚያደርጉት ቤቱን በዓለት ላይ የሠራውን ሰው ይመስላሉ በማለት ተናገረ። ይሁን እንጂ ትምህርቱን ሰምተው የማያደርጉት ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራውን ሰነፍ ሰው ይመስላሉ። የትኛውን ሰው መምሰል ትፈልጋለህ?—ማቴዎስ 7:24-27

በዓለት ላይ የተሠራ ቤት እና በአሸዋ ላይ የተሠራ ቤት

ራስን ለአምላክ መወሰን። ይህ ማለት በጸሎት ወደ ይሖዋ ቀርበህ ፈቃዱን ለዘላለም ማድረግ እንደምትፈልግ መንገር ማለት ነው። የአምላክን ፈቃድ ማድረግ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር መሆንህን ያሳያል።—ማቴዎስ 11:29

አንዲት ሴት ሕይወቷን ለይሖዋ መወሰኗን በጸሎት ስትገልጽ

መጠመቅ። “ተነሣና ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ ከኃጢአትህም ታጠብ።”—ሥራ 22:16

አንድ ሰው ሲጠመቅ

በአምላክ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ መካፈል። “ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፣ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት [“በሙሉ ነፍስ፣” NW] አድርጉት።”—ቆላስይስ 3:23

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ