የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 25—ሰቆቃወ ኤርምያስ
ጸሐፊው:- ኤርምያስ
የተጻፈበት ቦታ:- በኢየሩሳሌም አቅራቢያ
ተጽፎ ያለቀው:- 607 ከክ. ል. በፊት
በመንፈስ አነሳሽነት ከተጻፉት መጻሕፍት አንዱ ለሆነው ለዚህ መጽሐፍ የተሰጠው ስያሜ በጣም ተስማሚ ነው። መጽሐፉ፣ የባቢሎኑ ንጉሥ ናቡከደነፆር በ607 ከክርስቶስ ልደት በፊት ኢየሩሳሌምን ሲያጠፋ አምላክ በመረጣቸው ሕዝቦቹ ላይ የደረሰው መከራ ያስከተለውን ጥልቅ ሐዘን የሚገልጽ የሐዘን እንጉርጉሮ ነው። መጽሐፉ በዕብራይስጥ ኤህከሃህ! ተብሎ ተሰይሟል። ይህን ስያሜ ያገኘው የመጽሐፉ መክፈቻ ከሆነው ከመጀመሪያው ቃል ሲሆን “እንዴት!” የሚል ትርጉም አለው። የግሪክ ሰብዓ ሊቃናት ተርጓሚዎች መጽሐፉን ትሬኖይ ብለው የጠሩት ሲሆን ይህም “ሙሾ፣ የሰቆቃ ለቅሶ” ማለት ነው። የባቢሎናውያን ታልሙድ “ሙሾ፣ የሐዘን እንጉርጉሮ” የሚል ትርጉም ባለው ኪኖዝ በተባለው ቃል ይጠቀማል። በላቲኑ ጽሑፍ ውስጥ ይህንን መጽሐፍ ላመንቴይሽንስ ብሎ የሰየመው ጀሮም ሲሆን ትርጉሙም የሰቆቃ ለቅሶ ማለት ነው።
2 የሰቆቃወ ኤርምያስ መጽሐፍ በበርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ውስጥ ከኤርምያስ ቀጥሎ የሚገኝ ቢሆንም በዕብራይስጥ የቅዱሳን መጻሕፍት ዝርዝር ውስጥ ሃጊዮግራፋ ወይም መጻሕፍት ተብሎ በሚጠራው ክፍል ውስጥ ይገኛል። በዚህ አነስተኛ ስብስብ ውስጥ የማሕልየ መሓልይ፣ የሩት፣ የመክብብና የአስቴር መጻሕፍት የሚገኙ ሲሆን አምስቱ ሜግሂሎዝ (ጥቅሎች) በሚል ስያሜ ይታወቃል። የሰቆቃወ ኤርምያስ መጽሐፍ በአንዳንድ ዘመናዊ የዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱሶች ውስጥ በሩትና በመክብብ ወይም በአስቴርና በመክብብ መጻሕፍት መካከል ቢገኝም በጥንት ቅጂዎች ውስጥ ግን በእጃችን ከሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ጋር በሚመሳሰል መልኩ መጽሐፉ የሚገኘው ከኤርምያስ ቀጥሎ እንደሆነ ይነገራል።
3 መጽሐፉ ጸሐፊውን አይጠቅስም። ሆኖም ኤርምያስ እንደጻፈው ምንም አያጠራጥርም። በግሪክኛው ሰብዓ ሊቃናት ትርጉም ውስጥ መጽሐፉ የሚከተለው መግቢያ አለው:- “እስራኤላውያን ከተማረኩና ኢየሩሳሌም ከጠፋች በኋላ ኤርምያስ ቁጭ ብሎ በማልቀስ እንደሚከተለው በማለት ስለ ኢየሩሳሌም የሐዘን እንጉርጉሮ አወረደ።” ጀሮም እነዚህ ቃላት እውነት ስላልመሰሉት ባዘጋጀው ትርጉም ውስጥ አልጨመራቸውም። ሆኖም ሰቆቃወ ኤርምያስን የጻፈው ኤርምያስ መሆኑ በአይሁዶች ዘንድ ተቀባይነት ከማግኘቱም በተጨማሪ በሶሪያ ቋንቋ የተዘጋጀው የሲሪያክ ትርጉም፣ የላቲኑ ቩልጌት፣ የጆናታን ታርገምና የባቢሎናውያን ታልሙድ እንዲሁም ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ይህንን ያረጋግጣሉ።
4 አንዳንድ ተቺዎች የሰቆቃወ ኤርምያስ ጸሐፊ ኤርምያስ እንዳልሆነ የሚያሳይ ማስረጃ ለማቅረብ ሞክረዋል። ነገር ግን ኤ ኮሜንታሪ ኦን ዘ ሆሊ ባይብል የተባለው መጽሐፍ እንዲህ በማለት መጽሐፉን ኤርምያስ እንደጻፈው የሚያሳይ ማስረጃ ያቀርባል:- “በምዕ. 2 እና 4 ላይ ስለ ኢየሩሳሌም የሰፈረው ዝርዝር መግለጫ የዓይን ምሥክር የነበረ ሰው እንደጻፈው ያሳያል። እንዲሁም በጽሑፉ ላይ የሚንጸባረቀው ጥልቅ የሐዘን ስሜት፣ የግጥሞቹ ትንቢታዊ መንፈስ፣ አጻጻፉ፣ የቃላት ምርጫውና ሐሳቡ በጠቅላላ የኤርምያስን የአጻጻፍ ዘይቤ የተከተለ ነው።”a በሰቆቃወ ኤርምያስና በኤርምያስ መጽሐፍ ውስጥ ብዙ ተመሳሳይ አገላለጾች አሉ። በጣም ማዘኑን የሚያሳየው “ዐይኖቼ በእንባ ተሞልተዋል” የሚለው (ሰቆ. 1:16፤ 2:11፤ 3:48, 49፤ ኤር. 9:1፤ 13:17፤ 14:17) እንዲሁም ነቢያትና ካህናት ምግባረ ብልሹ በመሆናቸው የተነሳ ምን ያህል እንደጠላቸው የሚያሳዩት አገላለጾች ለዚህ ምሳሌ ይሆኑናል። (ሰቆ. 2:14፤ 4:13, 14፤ ኤር. 2:34፤ 5:30, 31፤ 14:13, 14) በኤርምያስ 8:18-22 እና 14:17, 18 ላይ ያለው ሐሳብ፣ በሰቆቃወ ኤርምያስ ላይ የሚገኘው የሐዘን እንጉርጉሮ የኤርምያስን የአጻጻፍ ዘይቤ የተከተለ እንደሆነ ያሳያል።
5 መጽሐፉ የተጻፈው ኢየሩሳሌም በ607 ከክርስቶስ ልደት በፊት ከጠፋች በኋላ ብዙም ሳይቆይ እንደሆነ በሰፊው ይታመናል። ኤርምያስ ከተማዋ መከበቧና መቃጠሏ የፈጠረበት ታላቅ ድንጋጤ ከአእምሮው ስላልጠፋ ሥቃዩን በዝርዝር አስፍሮታል። በአንድ ቦታ ላይ ሙሉ በሙሉ የተገለጸ አንድ ዓይነት የሐዘን እንጉርጉሮ እንደሌለና እያንዳንዱ የሐዘን እንጉርጉሮ በተለያዩ ግጥሞች ውስጥ በተደጋጋሚ እንደተገለጸ አንድ ተንታኝ ተናግረዋል። ከዚያም “ይህ የሐሳብ መመሰቃቀል . . . መጽሐፉ የተጻፈው ሊያስተላልፋቸው የፈለጋቸው ጉዳዮች ከተፈጸሙበት ጊዜ ብዙም ሳይርቅ እንደሆነ ከሚያሳዩት ጠንካራ ማስረጃዎች አንዱ ነው” ብለዋል።b
6 የሰቆቃወ ኤርምያስ መጽሐፍ ቅንብር የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራንን ትኩረት ይስባል። አምስት ምዕራፎች ወይም አምስት ግጥሞች አሉት። የመጀመሪያዎቹ አራት ምዕራፎች በፊደል ቅደም ተከተል የተጻፉ ሲሆን እያንዳንዱ ቁጥር ከ22ቱ የዕብራይስጥ ፊደላት ውስጥ በቅደም ተከተላቸው መሠረት በአንዱ ይጀምራል። በሌላ በኩል ደግሞ ሦስተኛው ምዕራፍ 66 ቁጥሮች ስላሉት በአንድ ፊደል ሥር ሦስት ቁጥሮች እናገኛለን። አምስተኛው ግጥም ግን 22 ቁጥሮች ቢኖሩትም በፊደላት ቅደም ተከተል አልተቀመጠም።
7 የሰቆቃወ ኤርምያስ መጽሐፍ ኢየሩሳሌም በናቡከደነፆር መከበቧ፣ መያዟና መጥፋቷ ያስከተለውን ጥልቅ ሐዘን የሚገልጽ ሲሆን በግልጽነቱና በአሳዛኝነቱ የሚተካከለው ጽሑፍ የለም። ጸሐፊው በተመለከተው ጥፋት፣ ሥቃይና ግራ መጋባት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጿል። ረሃብ፣ ሰይፍና ሌሎች አሠቃቂ ነገሮች በከተማዪቱ ውስጥ ከፍተኛ መከራ አስከትለው ነበር። ይህ ሁሉ የደረሰው ሕዝቡ፣ ነቢያቱና ካህናቱ በፈጸሙት ኃጢአት ምክንያት አምላክ ስለቀጣቸው ነው። በዚህም ጊዜ ቢሆን በይሖዋ ላይ ተስፋ ማድረግና እምነት መጣል ስለሚቻል ጸሐፊው ሁኔታዎቹ ተመልሰው እንዲስተካከሉ ጸልዮአል።
ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት
13 የሰቆቃወ ኤርምያስ መጽሐፍ ኤርምያስ በአምላክ ሙሉ በሙሉ ይታመን እንደነበረ ይገልጻል። ነቢዩ፣ በጥልቅ ሐዘን ተውጦና ቅስሙ ተሰብሮ በነበረበት እንዲሁም ከማንኛውም ሰብዓዊ ምንጭ መጽናኛ ማግኘት በማይችልበት ወቅት ላይ መዳንን ለማግኘት የአጽናፈ ዓለሙን ታላቅ አምላክ ይሖዋን ይጠባበቅ ነበር። ሰቆቃወ ኤርምያስ ሁሉም እውነተኛ አምላኪዎች ታዛዥና ታማኝ እንዲሆኑ ከማበረታታቱም በተጨማሪ ታላቁን ስምና ስሙ የሚያመለክተውን አካል ለማያከብሩ ሰዎች አስፈሪ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል። በመጥፋቷ ምክንያት እንዲህ ያለ አሳዛኝና ልብ የሚነካ የሐዘን እንጉርጉሮ የተጻፈላት ሌላ ከተማ በታሪክ ውስጥ አናገኝም። አምላክ በዓመጸኝነታቸው በሚቀጥሉ፣ አንገተ ደንዳኖች በሆኑና ንስሐ በማይገቡ ሰዎች ላይ የሚወስደውን ከበድ ያለ እርምጃ በመግለጽ ረገድ ጠቃሚ መጽሐፍ ነው።
14 ሰቆቃወ ኤርምያስ ብዛት ያላቸው መለኮታዊ ማስጠንቀቂያዎችና ትንቢቶች ያገኙትን ፍጻሜ በማሳየት በኩልም ጥቅም አለው። (ሰቆ. 1:2—ኤር. 30:14፤ ሰቆ. 2:15—ኤር. 18:16፤ ሰቆ. 2:17—ዘሌ. 26:17፤ ሰቆ. 2:20—ዘዳ. 28:53) በተጨማሪም ሰቆቃወ ኤርምያስ ዘዳግም 28:63-65 ለመፈጸሙ ግልጽ ማስረጃ ነው። ከዚህም በላይ ብዙ ጊዜ ከሌሎች የቅዱሳን መጻሕፍት ክፍሎች ይጠቅሳል። (ሰቆ. 2:15—መዝ. 48:2፤ ሰቆ. 3:24—መዝ. 119:57) ዳንኤል 9:5-14 በሕዝቡ ላይ የደረሰው ጥፋት ሕጉን በመተላለፋቸው ምክንያት እንደመጣ በመግለጽ ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:5ን እና 3:42ን ይደግፋል።
15 በኢየሩሳሌም ላይ የደረሰው ሰቆቃ በእርግጥም አሳዛኝ ነበር! የሰቆቃወ ኤርምያስ መጽሐፍ ጸሐፊ፣ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እያሉም እንኳ ይሖዋ ፍቅራዊ ደግነትና ምሕረት በማሳየት ጽዮንን እንደሚያስባትና ከምርኮ እንደሚመልሳት ያለውን እምነት ያስተጋባል። (ሰቆ. 3:31, 32፤ 4:22) መጽሐፉ፣ ጥንት ንጉሥ ዳዊትና ሰሎሞን በኢየሩሳሌም በነገሡበት ጊዜ እንደነበረው ያለ “አዲስ ዘመን” እንደሚመጣ የሚገልጽ ተስፋ ይዟል። ይሖዋ የዘላለም መንግሥት ለመመሥረት ከዳዊት ጋር የገባው ቃል ኪዳን እንደተጠበቀ ነበር! “ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው።” በጽድቅ መንግሥቱ ሥር የሚኖሩ ይሖዋን የሚወዱ ፍጥረታት ሁሉ “እግዚአብሔር ዕድል ፈንታዬ ነው” በማለት ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በምስጋና እስከሚዘምሩበት ጊዜ ድረስ ርኅራኄ ማሳየቱን ይቀጥላል።—5:21፤ 3:22-24
[የግርጌ ማስታወሻዎች]
a በጄ አር ዱምሎው በ1952 የታተመ፣ ገጽ 483
b ስተዲስ ኢን ዘ ቡክ ኦቭ ላመንቴይሽንስ 1954 ኖርመን ጎትቫልድ ገጽ 31