የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • bsi08-1 ገጽ 24-25
  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 48—ገላትያ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 48—ገላትያ
  • “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 16
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት
“ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 16
bsi08-1 ገጽ 24-25

የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 48​—⁠ገላትያ

ጸሐፊው:- ጳውሎስ

የተጻፈበት ቦታ:- ቆሮንቶስ ወይም በሶርያ የምትገኘው አንጾኪያ

ተጽፎ ያለቀው:- ከ50–52 ከክ.ል.በኋላ ገደማ

ጳውሎስ በገላትያ 1:2 ላይ የጠቀሳቸው የገላትያ ጉባኤዎች በጲስድያ በምትገኘው አንጾኪያ፣ በኢቆንዮን፣ በልስጥራንና በደርቤን ያሉትን ሳያካትቱ አይቀሩም። እነዚህ ቦታዎች በተለያዩ አውራጃዎች ውስጥ የሚገኙ ቢሆኑም እንኳ ሁሉም በዚህ የሮም ግዛት ሥር የታቀፉ ነበሩ። የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 13 እና 14 ጳውሎስ ከበርናባስ ጋር በመሆን በዚህ አካባቢ ስላደረገው የመጀመሪያ ሚስዮናዊ ጉዞው ይናገራሉ። ይህ ጉዞ በገላትያ ያሉት ጉባኤዎች እንዲደራጁ ለማድረግ አስችሏል። እነዚህ ጉባኤዎች አይሁዳውያን የሆኑና ያልሆኑ ሰዎችን ያቀፉ ነበሩ። ከእነዚህ የተለያዩ ሕዝቦች መካከል ሴልቶች ወይም የጎል ተወላጆች እንደሚገኙበት ምንም አያጠራጥርም። ይህ የሆነው ጳውሎስ በ46 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ገደማ ኢየሩሳሌምን ከጎበኘ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ነበር።—ሥራ 12:25

2 በ49 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ጳውሎስ ሁለተኛ የሚስዮናዊ ጉዞውን የጀመረው ከሲላስ ጋር ሆኖ በገላትያ ክልል ውስጥ በማገልገል ነበር። ይህም ጉባኤዎች ‘በእምነት እየበረቱና ዕለት ዕለት በቁጥር እየጨመሩ እንዲሄዱ’ አስችሏል። (ሥራ 16:5፤ 15:40, 41፤ 16:1, 2) ይሁን እንጂ ወዲያውኑ የአይሁድን እምነት የሚያስፋፉ ሐሰተኛ አስተማሪዎች እንቅስቃሴያቸውን ይበልጥ በማጠናከር በገላትያ ጉባኤዎች ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ሰዎችን፣ መገረዝና የሙሴን ሕግ ማክበር እውነተኛው ክርስትና ሊያሟላቸው የሚገቡ አስፈላጊ ነገሮች ናቸው ብለው እንዲያምኑ አድርገዋቸው ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ ጳውሎስ ሚስያን አልፎ ወደ መቄዶንያ እና ግሪክ፣ በመጨረሻም ከወንድሞች ጋር አንድ ዓመት ከመንፈቅ ወደሰነበተበት ወደ ቆሮንቶስ ተጉዟል። ከዚያም በ52 ከክርስቶስ ልደት በኋላ፣ በኤፌሶን በኩል አድርጎ ቋሚ መኖሪያው ወደሆነችው በሶርያ ወደምትገኘው አንጾኪያ አቀና።—ሥራ 16:8, 11, 12፤ 17:15፤ 18:1, 11, 18-22

3 ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች ደብዳቤ የጻፈው መቼ እና የት ሆኖ ነበር? የአይሁድን እምነት የሚያስፋፉ አንዳንድ ሰዎች ስለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ከሰማ በኋላ ወዲያውኑ እንደጻፈው ምንም አያጠራጥርም። ይህ የሆነው በቆሮንቶስ፣ በኤፌሶን ወይም በሶርያ በምትገኘው አንጾኪያ በነበረበት ወቅት ሊሆን ይችላል። በተለይ ደግሞ ከ50-52 ከክርስቶስ ልደት በኋላ በቆሮንቶስ ለአንድ ዓመት ተኩል በቆየበት ጊዜ፣ ከገላትያ መረጃ ለማግኘት በቂ ጊዜ ስለሚኖረው ደብደቤውን የጻፈው በዚያ ሳለ ሊሆን ይችላል። ደብደቤውን የጻፈው በኤፌሶን ሳለ የመሆን አጋጣሚው አነስተኛ ነው፤ ምክንያቱም የመልስ ጉዞውን ባደረገበት ጊዜ በዚያ የቆየው ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነበር። ይሁንና ከዚህ በኋላ ማለትም በ52 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ባለው የክረምት ወቅት አካባቢ ቋሚ በሆነው መኖሪያው ይኸውም በሶርያ በምትገኘው አንጾኪያ “ጥቂት ጊዜ ቆይቶ ነበር።” በተጨማሪም በዚህች ከተማና በትንሿ እስያ መካከል ጥሩ የመገናኛ መስመር ስለነበር የአይሁድን እምነት ስለሚያስፋፉ ሰዎች ሊሰማ ይችላል። በመሆኑም ለገላትያ ሰዎች ደብዳቤ የጻፈላቸው በ52 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ገደማ በአንጾኪያ ሆኖ ሊሆንም ይችላል።—ሥራ 18:23

4 ደብዳቤው ጳውሎስን “ከሰዎች ወይም በሰው ከተላከው ሳይሆን፣ በኢየሱስ ክርስቶስና ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ [የሆነ]” በማለት ይገልጸዋል። በተጨማሪም ሐዋርያ እንደመሆኑ መጠን ጳውሎስ በኢየሩሳሌም ከሚገኙ ሌሎች ሐዋርያት ጋር በስምምነት እንደሚሠራና ሌላው ቀርቶ ሥልጣኑን አንድን ሌላ ሐዋርያ ማለትም ጴጥሮስን ለማረም እንደተጠቀመበት በመግለጽ ስላሳለፈው ሕይወትና የሐዋርያነት አገልግሎት ይተርካል።—ገላ. 1:1, 13-24፤ 2:1-14

5 የገላትያ መልእክት ለትክክለኛነቱና የቅዱሳን ጽሑፎች ክፍል ለመሆኑ ምን ማረጋገጫዎች አሉን? ኢረንየስ፣ የእስክንድሪያው ክሌመንት፣ ተርቱሊያንና ኦሪጀን በጽሑፎቻቸው ውስጥ በስም ጠቅሰውታል። ከዚህም በላይ በሚከተሉት የላቀ ግምት በሚሰጣቸው በእጅ የተገለበጡ ጥንታዊ የቅዱሳን መጻሕፍት ቅጂዎች ውስጥ ይገኛል:- ሳይናይቲክ፣ አሌክሳንድራይን፣ ቫቲካን ቁ. 1209፣ ኮዴክስ ኤፍሬሚ ሳየሪ ረስክሪፕተስ፣ ኮዴክስ ቢዜ እንዲሁም ቼስተር ቢቲ ፓፒረስ ቁ. 2 (P46)። ከዚህም በላይ ከሌሎቹ የግሪክኛና የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ጋር ሙሉ በሙሉ ስምምነት ያለው ሲሆን ከእነዚህ መጽሐፍትም ደጋግሞ ይጠቅሳል።

6 ጳውሎስ “ለገላትያ አብያተ ክርስቲያናት” ወይም ጉባኤዎች በላከው ጠንካራና ቀጥተኛ ምክር ያዘለ ደብዳቤ ላይ (1) እውነተኛ ሐዋርያ መሆኑን (የአይሁድን እምነት የሚያስፋፉ ሰዎች ጳውሎስን ተቀባይነት ለማሳጣት ሲያነሱት የነበረው አንዱ ጉዳይ ነው) እንዲሁም (2) መጽደቅ የሚቻለው በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን እንጂ የሙሴን ሕግ በመጠበቅ ባለመሆኑ ክርስቲያኖች የግዴታ መገረዝ እንደማያስፈልጋቸው አስረድቷል። ጳውሎስ መልእክቶቹን ለማስጻፍ በጸሐፊዎች የመጠቀም ልማድ የነበረው ቢሆንም ለገላትያ ሰዎች የላከውን ደብዳቤ ግን ‘በታላላቅ ፊደላት በገዛ እጁ ጽፏል።’ (6:11) መጽሐፉ የያዛቸው ቁም ነገሮች ለጳውሎስም ሆነ ለገላትያ ሰዎች እጅግ አስፈላጊ ነበሩ። መጽሐፉ እውነተኛ ክርስቲያኖች በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ላገኙት ነፃነት አድናቆት ማሳየት እንዳለባቸው ጎላ አድርጎ ይገልጻል።

ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት

14 ለገላትያ ሰዎች የተላከው ደብዳቤ አሳዳጅና አጥፊ የነበረው ጳውሎስ ተለውጦ ለወንድሞቹ የችግራቸው ደራሽና ቀናተኛ የአሕዛብ ሐዋርያ መሆኑን ይገልጻል። (1:13-16, 23፤ 5:7-12) ጳውሎስ አንድ የበላይ ተመልካች የተሳሳተ አስተሳሰብን ለማረም አሳማኝ ማስረጃ በማቅረብና ቅዱስ ጽሑፉን በመጠቀም ችግሮችን ለመፍታት አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት በምሳሌ አሳይቷል።—1:6-9፤ 3:1-6

15 ደብዳቤው የገላትያ ክርስቲያኖች በክርስቶስ ያገኙትን ነፃነት በግልጽ የሚያስረዳና ምሥራቹን የሚያጣምሙትን ሐሰተኝነት የሚያጋልጥ ስለነበር በገላትያ የሚገኙትን ጉባኤዎች ጠቅሟቸዋል። አንድ ሰው የሚጸድቀው በእምነት ስለሆነ መዳን ለማግኘት የግድ መገረዝ እንደማያስፈልግ ይገልጻል። (2:16፤ 3:8፤ 5:6) እንደዚህ የመሳሰሉ መከፋፈልን የሚፈጥሩ ነገሮችን ወደ ጎን መተዉ አይሁድና አሕዛብ በአንድ ጉባኤ ውስጥ አብረው እንዲያገለግሉ ለማድረግ አስችሏል። ከሕጉ ነፃ መሆን ሥጋዊ ፍላጎቶችን ለመፈጸም ሰበብ ሊሆን አይገባም፤ ምክንያቱም “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚለው መሠረታዊ ሥርዓት አሁንም ይሠራል። ይህ በጊዜያችን ለሚገኙ ክርስቲያኖችም መመሪያ ሆኖ ማገልገሉን ቀጥሏል።—5:14

16 የጳውሎስ ደብዳቤ ከዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ላይ ጠንካራ ምሳሌዎችን በመውሰድ የገላትያ ሰዎች በበርካታ መሠረተ ትምህርቶች ላይ ጥሩ ግንዛቤ እንዲያገኙ ረድቷቸዋል። “ከላይ የሆነችው ኢየሩሳሌም” የይሖዋ ሴት መሆኗን ለይቶ በማሳወቅ ለ​ኢሳይያስ 54:1-6 በመንፈስ አነሳሽነት የተሰጠውን ትርጉም ዘግቧል። ስለ አጋርና ስለ ሣራ በሚናገረው ‘ምሳሌያዊ’ ድራማ ላይ እንደተገለጸው የአምላክ ተስፋ ወራሾች በሕጉ ባርነት ሥር የሚገኙት ሳይሆኑ በክርስቶስ ነፃ የሆኑ ሰዎች መሆናቸውን ያብራራል። (ገላ. 4:21-26፤ ዘፍ. 16:1-4, 15፤ 21:1-3, 8-13) የሕጉ ቃል ኪዳን ከአብርሃም ቃል ኪዳን ጋር እንደማይቃረንና ከዚህ ይልቅ በእሱ ላይ የተጨመረ መሆኑን ይገልጻል። በተጨማሪም በሁለቱ ቃል ኪዳኖች መካከል ያለው የጊዜ ልዩነት 430 ዓመት መሆኑን ያሳያል። ይህ ደግሞ ለመጽሐፍ ቅዱስ የዘመናት ስሌት ጠቃሚ መረጃ ነው። (ገላ. 3:17, 18, 23, 24) እነዚህ ዘገባዎች ተጠብቀው የቆዩት በዛሬው ጊዜ ያሉትን ክርስቲያኖች እምነት ለመገንባት ነው።

17 ከሁሉ በላይ ደግሞ ገላትያ “የተስፋውም ቃል የተነገረው ለአብርሃምና ለዘሩ ነበር፤ . . . እርሱም ክርስቶስ ነው” በማለት ነቢያት ሁሉ መምጣቱን ይጠባበቁ የነበረው የመንግሥቱ ዘር ማን መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ለይቶ ጠቅሷል። በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የአምላክ ልጆች የሆኑ ሰዎች የዘሩ ክፍል እንዲሆኑ ተቀባይነት ማግኘታቸውም ተገልጿል። “የክርስቶስ ከሆናችሁ፣ እናንተ የአብርሃም ዘር ናችሁ፤ እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ።” (3:16, 29) እነዚህ የመንግሥቱ ወራሾችም ሆኑ ከእነሱ ጋር አብረው የሚሠሩት ‘ክርስቶስ በሰጣቸው ነፃነት ጸንተው እንዲቆሙ’ በገላትያ መጽሐፍ ውስጥ የተሰጣቸውን ግሩም ምክር በተግባር ላይ ያውላሉ። ‘በጎ ነገር ከማድረግ አትታክቱ፤ ተስፋ ካልቈረጥን ጊዜው ሲደርስ መከሩን እናጭዳለን።’ ‘በተለይም ለእምነት ቤተ ሰቦች መልካም አድርጉ።’—5:1፤ 6:9, 10

18 በመጨረሻም የሥጋ ሥራን የሚያደርጉ ሰዎች ‘የአምላክን መንግሥት እንደማይወርሱ’ የሚገልጽ ኃይለኛ ማስጠንቀቂያ ይገኛል። እንግዲያው ሁላችንም በዓለም ውስጥ ከሚገኘው ቆሻሻና ጠብ ፈጽሞ በመራቅ የመንፈስ ፍሬ የሆኑትን ‘ፍቅርን፣ ደስታን፣ ሰላምን፣ ትዕግሥትን፣ ደግነትን፣ ጥሩነትን፣ እምነትን፣ ገርነትንና ራስን መግዛትን’ ለማፍራት ቁርጥ ውሳኔ እናድርግ።—5:19-23 NW

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ