የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • bm ገጽ 31
  • የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት
  • መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
bm ገጽ 31
ገነት በሆነች ምድር ላይ የሰው ልጆች በአምላክ መንግሥት አገዛዝ ሥር በደስታ ሲኖሩ

የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት

  1. ይሖዋ አዳምንና ሔዋንን ሲፈጥር ዓላማው በገነት ውስጥ ለዘላለም እንዲኖሩ ነበር። ሰይጣን የአምላክን ስም ያጠፋ ከመሆኑም በላይ በአምላክ የመግዛት መብት ላይ ጥያቄ አስነሳ። አዳምና ሔዋን ከሰይጣን ጋር ተባብረው በማመፃቸው በራሳቸውም ሆነ በዘሮቻቸው ላይ ኃጢአትና ሞትን አመጡ

  2. ይሖዋ በዓመፀኞቹ ላይ የፈረደባቸው ሲሆን አዳኝ ወይም ዘር እንደሚመጣ ቃል ገባ፤ ይህ ዘር ሰይጣንን ያጠፋዋል እንዲሁም የዓመፅና የኃጢአት ውጤት የሆኑ ነገሮችን በሙሉ ያስተካክላል

  3. ይሖዋ ለአብርሃምና ለዳዊት፣ ንጉሥ ሆኖ ለዘላለም የሚገዛው ዘር ወይም መሲሕ በእነሱ የትውልድ ሐረግ በኩል እንደሚመጣ ቃል ገባላቸው

  4. ነቢያት፣ መሲሑ ኃጢአትንም ሆነ ሞትን እንደሚያስወግድ በይሖዋ መንፈስ መሪነት ትንቢት ተናገሩ። መሲሑ ከተባባሪ ገዢዎቹ ጋር በመሆን የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ሆኖ ይገዛል፤ ይህ መንግሥት ጦርነትን፣ በሽታንና ሌላው ቀርቶ ሞትን እንኳ ያስወግዳል

  5. ይሖዋ ልጁን ወደ ምድር የላከው ሲሆን መሲሑ ኢየሱስ መሆኑን አሳወቀ። ኢየሱስ ስለ አምላክ መንግሥት የሰበከ ከመሆኑም በላይ ሕይወቱን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ። ከዚያም ይሖዋ መንፈሳዊ አካል ይዞ ከሞት እንዲነሳ አደረገው

  6. ይሖዋ ልጁን በሰማይ ንጉሥ አድርጎ ሾመው፤ ይህም የዚህ ሥርዓት የመጨረሻ ቀኖች መጀመራቸውን የሚያሳይ ምልክት ነው። ኢየሱስ በምድር ላይ ያሉት ተከታዮቹ ስለ አምላክ መንግሥት በዓለም ዙሪያ ሲሰብኩ ይመራቸዋል

  7. ይሖዋ በልጁ አማካኝነት መንግሥቱ ምድርን እንዲገዛ ያደርጋል። ይህ መንግሥት ክፉ የሆኑ ሰብዓዊ መንግሥታትን በሙሉ ያጠፋል፤ ምድርን ገነት ያደርጋል እንዲሁም ታማኝ የሆኑ የሰው ልጆችን ወደ ፍጽምና ያደርሳል። የይሖዋ የመግዛት መብት ይረጋገጣል፤ ስሙም ለዘላለም ይቀደሳል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ