ይበልጥ ለማወቅ ይፈልጋሉ?
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው መልእክት በዚህ ብሮሹር ላይ አጠር ባለና ትኩረት በሚስብ መንገድ ቀርቧል። ይሁንና የብሮሹሩ ዓላማ መጽሐፍ ቅዱስ በእያንዳንዱ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚሰጠውን ትምህርት በዝርዝር ማብራራት አይደለም።
ለምሳሌ ያህል፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚከተሉት ላሉት ጥያቄዎች የሚሰጠውን መልስ ለማወቅ ይፈልጉ ይሆናል፦ አምላክ በእርግጥ በግለሰብ ደረጃ ስለ እኔ ያስባል? ስንሞት ምን እንሆናለን? በሕይወቴ ውስጥ ደስታ ማግኘት የምችለው እንዴት ነው?
የእነዚህንና ትኩረት የሚስቡ የሌሎች ጥያቄዎችን መልስ፣ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? በተባለው በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀ መጽሐፍ ላይ ማግኘት ይችላሉ። ይህ መጽሐፍ፣ መጽሐፍ ቅዱስን በርዕስ ከፋፍሎ ለማጥናት እንዲመች ታስቦ የተዘጋጀ ነው። መጽሐፉ በዚህ መንገድ መዘጋጀቱ ከአንድ ርዕሰ ጉዳይ ጋር የተያያዙ የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በአንድ ላይ ለማግኘት ያስችላል። ይህን መጽሐፍ ማግኘት ከፈለጉ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ሞልተው ከታች ካሉት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
www.pr2711.com/amን ተጠቅመህ አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ እንዲያስተምርህ መጠየቅ አሊያም ከዚህ ድረ ገጽ ላይ ይህን ጽሑፍ ማንበብ ወይም ማውረድ ትችላለህ።