የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 1 ገጽ 8-ገጽ 9 አን. 4
  • አምላክ ሰማይንና ምድርን ሠራ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ ሰማይንና ምድርን ሠራ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ የተለያዩ ነገሮችን መፍጠር ጀመረ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • እንስሳት
    ንቁ!—2015
  • ውብ የአትክልት ቦታ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ሁሉንም ነገሮች የሠራው ፈጣሪ
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 1 ገጽ 8-ገጽ 9 አን. 4
የኤደን የአትክልት ስፍራ

ትምህርት 1

አምላክ ሰማይንና ምድርን ሠራ

ይሖዋ አምላክ ፈጣሪያችን ነው። በዓይን የሚታዩትንም ሆነ የማይታዩትን ነገሮች በሙሉ የሠራው እሱ ነው። በዓይን የሚታዩትን ነገሮች ከመሥራቱ በፊት ብዙ መላእክትን ፈጥሯል። መላእክት እነማን እንደሆኑ ታውቃለህ? መላእክት የይሖዋ አገልጋዮች ናቸው። አምላክን ማየት እንደማንችል ሁሉ እነሱንም ማየት አንችልም። አምላክ የፈጠረው የመጀመሪያው መልአክ የእሱ ረዳት ሆኖ አገልግሏል። ይህ መልአክ ይሖዋ ከዋክብትንና ሌሎች ነገሮችን ሁሉ ሲሠራ አብሮት ሠርቷል። ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዷ ውብ መኖሪያችን የሆነችው ምድር ነች።

ከዚያም ይሖዋ ምድርን ለእንስሳትና ለሰዎች ተስማሚ መኖሪያ እንድትሆን አድርጎ አዘጋጃት። ፀሐይ ብርሃኗን ምድር ላይ እንድታበራ አደረገ። ተራሮችን፣ ወንዞችንና ባሕርን ሠራ።

ከዚያስ ምን አደረገ? ይሖዋ ‘ሣርን፣ ተክሎችንና ዛፎችን እፈጥራለሁ’ አለ። ብዙ ዓይነት ፍራፍሬ፣ አትክልትና አበቦች መብቀል ጀመሩ። ከዚያም ይሖዋ የሚበርሩ፣ የሚዋኙና መሬት ላይ የሚሳቡ እንስሳትን በሙሉ ፈጠረ። በተጨማሪም እንደ አይጥ ያሉ ትናንሽ እንስሳትንና እንደ ዝሆን ያሉ ትላልቅ እንስሳትን ፈጠረ። አንተ በጣም የምትወደው እንስሳ የቱ ነው?

ቀጥሎም ይሖዋ አብሮት እየሠራ የነበረውን የመጀመሪያውን መልአክ ‘ሰውን እንሥራ’ አለው። ሰዎች ከእንስሳት የተለዩ ናቸው። አዳዲስ ነገሮችን መፈልሰፍ ወይም መሥራት ይችላሉ። ከዚህም ሌላ መናገር፣ መሳቅና መጸለይ ይችላሉ። እንዲሁም ምድርንና እንስሳትን ይንከባከባሉ። አምላክ መጀመሪያ የፈጠረው ሰው ማን እንደሆነ ታውቃለህ? እስቲ እንመልከት።

“በመጀመሪያ አምላክ ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።”—ዘፍጥረት 1:1

ጥያቄ፦ ይሖዋ አምላክ ማን ነው? ይሖዋ የትኞቹን ነገሮች ፈጥሯል?

ዘፍጥረት 1:1-26፤ ምሳሌ 8:30, 31፤ ኤርምያስ 10:12፤ ቆላስይስ 1:15-17

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ