የክፍል 1 ማስተዋወቂያ
መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ስንጀምር ስለ አምላክ የፍጥረት ሥራ የሚገልጽ ታሪክ እናገኛለን፤ ይህ ታሪክ ይሖዋ በሰማይም ሆነ በምድር ስለፈጠራቸው ውብ ነገሮች እንድናውቅ ያስችለናል። ወላጅ ከሆንክ ልጅህ፣ ይሖዋ የፈጠራቸውን ብዙ ዓይነት ፍጥረታት እንዲያስተውል እርዳው። አምላክ የሰው ልጆችን ከእንስሳት እጅግ የላቁ አድርጎ እንደፈጠራቸው ይኸውም የመናገር፣ የማገናዘብ፣ አዳዲስ ነገሮችን የመፈልሰፍ፣ የመዘመርና የመጸለይ ችሎታ እንደሰጣቸው ግለጽለት። የይሖዋን ኃይልና ጥበብ በተለይ ደግሞ እኛን ጨምሮ ለፍጥረታቱ በሙሉ ያሳየውን ፍቅር እንዲያደንቅ እርዳው።