የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 72 ገጽ 170-ገጽ 171 አን. 2
  • ኢየሱስ በአሥራ ሁለት ዓመቱ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ በአሥራ ሁለት ዓመቱ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መለኮታዊ መመሪያን ተቀብሏል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ቤተሰቡን ጠብቋል፣ ተንከባክቧል፣ ኃላፊነቱን ተወጥቷል
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
  • ቤተሰቡን ጠብቋል፣ ተንከባክቧል፣ ኃላፊነቱን ተወጥቷል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • በናዝሬት አደገ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 72 ገጽ 170-ገጽ 171 አን. 2
ኢየሱስ በአሥራ ሁለት ዓመቱ በቤተ መቅደሱ በሚገኙ አስተማሪዎች መካከል ተቀምጦ

ትምህርት 72

ኢየሱስ በአሥራ ሁለት ዓመቱ

ዮሴፍና ማርያም ከኢየሱስና ከሌሎች ልጆቻቸው ጋር በናዝሬት ይኖሩ ነበር። ዮሴፍ የአናጺነት ሥራ በመሥራት ቤተሰቡ የሚያስፈልገውን ነገር ያቀርብ ነበር፤ እንዲሁም ቤተሰቡን ስለ ይሖዋና ስለ ሕጉ አስተምሯል። ቤተሰቡ አዘውትረው ወደ ምኩራብ በመሄድ አምልኳቸውን ያከናውኑ ነበር፤ እንዲሁም በየዓመቱ የፋሲካ በዓልን ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም ይጓዛሉ።

ኢየሱስ የ12 ዓመት ልጅ ሳለ ቤተሰቡ እንደተለመደው ረጅም ርቀት ተጉዘው ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ። ኢየሩሳሌም የፋሲካ በዓልን ለማክበር በመጡ ሰዎች ተጨናንቃ ነበር። ዮሴፍና ማርያም በዓሉን ካከበሩ በኋላ ወደ ቤታቸው ለመመለስ ጉዞ ጀመሩ፤ በዚህ ጊዜ ኢየሱስ አብረዋቸው ከሚጓዙት ሰዎች ጋር ያለ መስሏቸው ነበር። ሆኖም ዘመዶቻቸው ጋ ሲፈልጉት ሊያገኙት አልቻሉም።

ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ለሦስት ቀን ያህል ሲፈልጉት ቆዩ። በመጨረሻም ወደ ቤተ መቅደሱ ሄዱ። ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ባሉ አስተማሪዎች መካከል ቁጭ ብሎ በደንብ እያዳመጣቸውና ጥያቄ እየጠየቃቸው ነበር። አስተማሪዎቹ በጣም ከመገረማቸው የተነሳ እነሱም ጥያቄ ይጠይቁት ጀመር። በሚሰጣቸውም መልስ በጣም ተደነቁ። ኢየሱስ የይሖዋን ሕግ በሚገባ እንደሚያውቅ ማስተዋል ቻሉ።

ዮሴፍና ማርያም በጣም ተጨንቀው ነበር። ማርያም ኢየሱስን እንዲህ አለችው፦ ‘ልጄ፣ እኛ እኮ አንተን ፍለጋ ያልሄድንበት ቦታ የለም! የት ሄደህ ነው?’ እሱም ‘በአባቴ ቤት መሆን እንደሚገባኝ አታውቁም?’ አላቸው።

ኢየሱስ ከወላጆቹ ጋር ወደ ናዝሬት ተመለሰ። ዮሴፍ ኢየሱስን የአናጺነት ሙያ አስተማረው። ኢየሱስ በወጣትነቱ ምን ዓይነት ሰው የነበረ ይመስልሃል? ኢየሱስ እያደገ ሲመጣ ይበልጥ ጥበበኛ እየሆነ እንዲሁም በአምላክና በሰው ፊት ሞገስ እያገኘ ሄደ።

ዮሴፍና ማርያም ከኢየሱስ እንዲሁም ከወንድሞቹና እህቶቹ ጋር ተቀምጠው

“አምላኬ ሆይ፣ ፈቃድህን ማድረግ ያስደስተኛል፤ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።”—መዝሙር 40:8

ጥያቄ፦ ዮሴፍና ማርያም ኢየሱስን ያገኙት የት ነው? ኢየሱስ ወደዚያ የሄደው ለምንድን ነው?

ማቴዎስ 13:55, 56፤ ማርቆስ 6:3፤ ሉቃስ 2:40-52፤ 4:16፤ ዘዳግም 16:15, 16

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ