የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • th ጥናት 15 ገጽ 18
  • በእርግጠኝነት መናገር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በእርግጠኝነት መናገር
  • ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በእርግጠኝነት መናገር
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • በጋለ ስሜት መናገር
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • በጭውውት መልክ መናገር
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ግንዛቤ የሚያሰፋ
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
ለተጨማሪ መረጃ
ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
th ጥናት 15 ገጽ 18

ጥናት 15

በእርግጠኝነት መናገር

ጥቅስ

1 ተሰሎንቄ 1:5

ፍሬ ሐሳብ፦ የምትናገረው ነገር ትክክለኛና በጣም አስፈላጊ መሆኑን ከልብህ እንደምታምን በሚያሳይ መንገድ ተናገር።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • በሚገባ ተዘጋጅ። ዋና ዋናዎቹ ነጥቦች ፍንትው ብለው እስኪታዩህ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህን ሐሳቦች እንዴት እንደሚደግፍ በደንብ እስኪገባህ ድረስ ትምህርቱን አጥናው። ከዚያም ዋና ዋናዎቹን ነጥቦች እጥር ምጥን ባለ መንገድ ለማስቀመጥ ሞክር። ትምህርቱ አድማጮችህን እንዴት ሊጠቅም እንደሚችል አስብ። የመንፈስ ቅዱስን እርዳታ ለማግኘት ጸልይ።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    ትምህርቱ በደንብ እንዲዋሃድህና ንግግሩን ጥሩ አድርገህ ማቅረብ እንድትችል ድምፅህን ከፍ አድርገህ ተለማመድ።

  • ትምህርቱን ከልብህ እንደምታምንበት የሚያሳዩ ቃላትን ተጠቀም። በጽሑፉ ላይ የሰፈረውን ሐሳብ ቃል በቃል ከመድገም ይልቅ ሐሳቡን በራስህ አባባል ግለጸው። የምትናገረው ነገር እውነት መሆኑን እንደምታምን የሚያሳዩ አገላለጾችን ተጠቀም።

  • እርግጠኛ እንደሆንክ በሚያሳይ መንገድ ተናገር። ድምፅህ ጎላ ብሎ ሊሰማ ይገባል። በአካባቢያችሁ እንደ ነውር የማይቆጠር ከሆነ የአድማጮችህን ዓይን እያየህ ተናገር።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    በእርግጠኝነት መናገር ሲባል ሌሎችን መጫን፣ ሐሳበ ግትር መሆን ወይም ቅር በሚያሰኝ መንገድ መናገር ማለት አይደለም። ትምህርቱን እንደምታምንበት በሚያሳይ መንገድ መናገር ቢኖርብህም አነጋገርህ ደግነት የሚንጸባረቅበት ሊሆን ይገባል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ