የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lff ትምህርት 8
  • የይሖዋ ወዳጅ መሆን ትችላለህ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የይሖዋ ወዳጅ መሆን ትችላለህ
  • ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጠለቅ ያለ ጥናት
  • ማጠቃለያ
  • ምርምር አድርግ
  • ጥሩ ጓደኞች መምረጥ የምንችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • አምላክ ወዳጁ እንድትሆን ይጋብዝሃል
    የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
  • ጓደኞችህን በጥበብ ምረጥ
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • እውነተኛ ጓደኞቼ እነማን ናቸው?
    ንቁ!—2011
ለተጨማሪ መረጃ
ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
lff ትምህርት 8
ምዕራፍ 8. ወንበር ላይ ተቀምጦ ወደ ሰማይ የሚመለከት ሰው

ምዕራፍ 08

የይሖዋ ወዳጅ መሆን ትችላለህ

በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው

ይሖዋ በደንብ እንድታውቀው ይፈልጋል። ለምን? ምክንያቱም ስለ ባሕርያቱ፣ ስለ ዓላማውና አንዳንድ ነገሮችን ስለሚያከናውንበት መንገድ ይበልጥ ባወቅክ መጠን የእሱ ወዳጅ ለመሆን ያለህ ፍላጎትም ሊጨምር እንደሚችል ያውቃል። በእርግጥ የአምላክ ወዳጅ መሆን ይቻላል? (መዝሙር 25:14⁠ን አንብብ።) የእሱ ወዳጅ ለመሆን ምን ማድረግ ይኖርብሃል? መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል፤ በተጨማሪም ከይሖዋ ጋር የምትመሠርተው ወዳጅነት ከየትኛውም ወዳጅነት የላቀ የሆነበትን ምክንያት ይገልጻል።

1. ይሖዋ ምን ግብዣ አቅርቦልሃል?

“ወደ አምላክ ቅረቡ፤ እሱም ወደ እናንተ ይቀርባል።” (ያዕቆብ 4:8) ይህ ምን ማለት ነው? ይሖዋ የእሱ ወዳጅ እንድትሆን ግብዣ አቅርቦልሃል። አንዳንዶች ከማያዩት አካል ጋር ወዳጅ መሆን እንደማይቻል ይሰማቸዋል፤ ከአምላክ ጋር ወዳጅ መሆንማ ጨርሶ የማያስቡት ነገር ነው። ይሖዋ ግን ወደ እሱ እንድንቀርብ ስለሚፈልግ በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ እሱ ማወቅ የሚያስፈልገንን ነገር በሙሉ አስፍሮልናል። ይሖዋን አይተነው የማናውቅ ቢሆንም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሰፈረልንን መልእክት ስናነብ ከእሱ ጋር ያለን ወዳጅነት ይበልጥ ይጠናከራል።

2. ይሖዋ ከማንም የተሻለ ወዳጅ የሆነው ለምንድን ነው?

የይሖዋን ያህል የሚወድህ የለም። ደስተኛ እንድትሆንና እርዳታ በሚያስፈልግህ ጊዜ ሁሉ ወደ እሱ እንድትጸልይ ይፈልጋል። ‘የሚያስጨንቅህን ነገር ሁሉ በእሱ ላይ መጣል’ ትችላለህ፤ ‘ምክንያቱም እሱ ስለ አንተ ያስባል።’ (1 ጴጥሮስ 5:7) ይሖዋ ምንጊዜም ቢሆን ወዳጆቹን ለመደገፍ፣ ለማጽናናትና ለማዳመጥ ዝግጁ ነው።—መዝሙር 94:18, 19⁠ን አንብብ።

3. የይሖዋ ወዳጅ ለመሆን ምን ማድረግ ያስፈልጋል?

ይሖዋ ሁሉንም ሰዎች ይወዳል፤ ‘የጠበቀ ወዳጅነት ያለው ግን ከቅኖች ጋር ነው።’ (ምሳሌ 3:32) ይሖዋ ወዳጆቹ በእሱ ፊት ጥሩ የሆኑትን ነገሮች እንዲያደርጉና በእሱ ፊት መጥፎ ከሆኑ ነገሮች እንዲርቁ ይፈልጋል። አንዳንዶች ይሖዋ ጥሩና መጥፎ የሆነውን ነገር በተመለከተ ያወጣውን መሥፈርት ፈጽሞ ሊያሟሉ እንደማይችሉ ይሰማቸው ይሆናል። ሆኖም ይሖዋ ያለብንን የአቅም ገደብ ይረዳል። ከልባችን እስከወደድነውና እሱን ለማስደሰት የምንችለውን ሁሉ እስካደረግን ድረስ ይቀበለናል።—መዝሙር 147:11፤ የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35

ጠለቅ ያለ ጥናት

የይሖዋ ወዳጅ መሆን የምትችለው እንዴት እንደሆነና ይሖዋ ከማንም የተሻለ ወዳጅ ይሆንልሃል የምንለው ለምን እንደሆነ እንመለከታለን።

4. አብርሃም የይሖዋ ወዳጅ ነበር

ስለ አብርሃም (አብራም ተብሎም ተጠርቷል) የሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ የአምላክ ወዳጅ መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ ያስችለናል። በዘፍጥረት 12:1-4 ላይ የሚገኘውን ስለ አብርሃም የሚገልጽ ዘገባ አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ይሖዋ አብርሃምን ምን እንዲያደርግ ጠይቆታል?

  • ይሖዋ ለአብርሃም ምን ቃል ገብቶለታል?

  • አብርሃም ይህ ትእዛዝ ሲሰጠው ምን አደረገ?

5. ይሖዋ ከወዳጆቹ የሚጠብቃቸው ነገሮች

ማናችንም ብንሆን ከጓደኞቻችን አንዳንድ ነገሮች መጠበቃችን አይቀርም።

  • አንተ ጓደኞችህ እንዲያደርጉ የምትፈልጋቸው አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው?

አንደኛ ዮሐንስ 5:3⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ይሖዋ ወዳጆቹ ምን እንዲያደርጉ ይፈልጋል?

ይሖዋን ለመታዘዝ በምግባራችን ወይም በባሕርያችን ላይ ለውጥ ማድረግ ሊያስፈልገን ይችላል። ኢሳይያስ 48:17, 18⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ይሖዋ ወዳጆቹ አንዳንድ ለውጦችን እንዲያደርጉ የሚፈልገው ለምንድን ነው?

አንድ የግንባታ ሠራተኛ አብሮት ለሚሠራ ሰው የራስ መሸፈኛ ሄልሜት ሲሰጠው

አንድ ጥሩ ወዳጅ የሚጠቅመንን እና ከአደጋ የሚጠብቀንን ነገር እንድናደርግ ይመክረናል። ይሖዋም ለወዳጆቹ እንዲሁ ያደርጋል

6. ይሖዋ ለወዳጆቹ የሚያደርጋቸው ነገሮች

ይሖዋ ወዳጆቹ ያጋጠሟቸውን ችግሮች መቋቋም እንዲችሉ ይረዳቸዋል። ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

ቪዲዮ፦ ይሖዋ ብዙ ነገር አድርጎልኛል (3:20)

  • ይሖዋ በቪዲዮው ላይ የታየችው ሴት የነበራትን አሉታዊ አስተሳሰብና ስሜት እንድታሸንፍ የረዳት እንዴት ነው?

ኢሳይያስ 41:10, 13⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ይሖዋ ለወዳጆቹ ሁሉ ምን እንደሚያደርግላቸው ቃል ገብቷል?

  • ይሖዋ ጥሩ ወዳጅ የሚሆንህ ይመስልሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

የቅርብ ጓደኛሞች ሲረዳዱ የሚያሳዩ ሥዕሎች፦ 1. አንድ ሰው ሌላን ሰው ትልቅ ጠረጴዛ ማንቀሳቀስ ሲያግዘው 2. አንዲት ሴት ያሳሰባትን ነገር ለሌላ ሴት ስትነግራት 3. አንድ ሰው ከዘራ ይዞ የሚራመድን ሌላ ሰው ደግፎት

የቅርብ ወዳጆችህ በሚያስፈልግህ ጊዜ ሁሉ ይረዱሃል። ይሖዋም ልክ እንደዚሁ ያደርጋል

7. የይሖዋ ወዳጅ ለመሆን ከእሱ ጋር መነጋገር ያስፈልጋል

ወዳጅነት ሊጠናከር የሚችለው ጥሩ የሐሳብ ግንኙነት ሲኖር ነው። መዝሙር 86:6, 11⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ይሖዋን ማነጋገር የምንችለው እንዴት ነው?

  • ይሖዋ እኛን የሚያነጋግረን እንዴት ነው?

1. አንዲት ሴት ስትጸልይ። ከጭንቅላቷ በላይ ያለው ቀስት ወደ ላይ ይጠቁማል። 2. አንዲት ሴት መጽሐፍ ቅዱስ ስታነብ። ከጭንቅላቷ በላይ ያለው ቀስት ወደ ታች ይጠቁማል።

በጸሎት አማካኝነት ይሖዋን እናነጋግረዋለን፤ እሱ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ያነጋግረናል

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “ከአምላክ ጋር ወዳጅነት መመሥረት የማይቻል ነገር ነው።”

  • የይሖዋ ወዳጅ መሆን እንደምንችል ለማስረዳት የትኛውን ጥቅስ ትጠቀማለህ?

ማጠቃለያ

ይሖዋ ወዳጅህ መሆን ይፈልጋል፤ ደግሞም ወደ እሱ እንድትቀርብ ይረዳሃል።

ክለሳ

  • ይሖዋ ወዳጆቹን የሚረዳቸው እንዴት ነው?

  • ይሖዋ ወዳጆቹ አንዳንድ ለውጦችን እንዲያደርጉ የሚፈልገው ለምንድን ነው?

  • የይሖዋ ወዳጅ መሆን ከአቅም በላይ የሆነ ነገር እንደሆነ ይሰማሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

ግብ

ምርምር አድርግ

ከይሖዋ ጋር ወዳጅነት መመሥረትህ የሚጠቅምህ እንዴት ነው?

“ይሖዋ—ልናውቀው የሚገባ አምላክ” (መጠበቂያ ግንብ የካቲት 15, 2003)

የአምላክ ወዳጅ መሆን የምትችለው እንዴት እንደሆነ አንብብ።

“የአምላክ ወዳጅ መሆን የምችለው እንዴት ነው?” (ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 2፣ ምዕራፍ 35)

አንዲት ሴት ከይሖዋ ጋር ወዳጅነት መመሥረቷ የጠቀማት እንዴት እንደሆነ አንብብ።

“ሞትን እፈራ ነበር!” (መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 1 2017)

ወጣቶች ከይሖዋ ጋር ስላላቸው ወዳጅነት ምን እንደሚሰማቸው ሲናገሩ አዳምጥ።

የአምላክ ወዳጅ መሆን ማለት ምን ማለት ነው? (1:46)

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ