የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • scl ገጽ 3-5
  • መግቢያ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መግቢያ
  • ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት
ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት
scl ገጽ 3-5

መግቢያ

ያጋጠመህ ተፈታታኝ ሁኔታ አለ? ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት፣ አሁን ላለህበት ሁኔታ የሚሠሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችንና ታሪኮችን በቀላሉ ፈልገህ ለማግኘት ይረዳሃል። እንዲሁም ሌሎችን ማበረታታትና ይሖዋን የሚያስከብር ውሳኔ እንዲያደርጉ መርዳት ስትፈልግ ለሁኔታው ተስማሚ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳቦች ለማግኘት ያስችልሃል። ከአንተ የሚጠበቀው የምትፈልገውን ርዕሰ ጉዳይ መምረጥ ነው፤ እያንዳንዱ ርዕሰ ጉዳይ ጥያቄዎችና በአጭሩ የተቀመጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ይዟል። (“በዚህ ጽሑፍ መጠቀም የምትችለው እንዴት ነው?” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።) በዚህ መንገድ ከአምላክ ቃል ላይ የሚያስፈልግህን ጠቃሚ ምክር፣ መመሪያና ማጽናኛ ታገኛለህ። ለሌሎች የምታካፍላቸው መንፈሳዊ ዕንቁዎችም ታገኛለህ፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ተጠቅመህ መንፈሳቸውን ማደስ፣ ችግራቸውን እንዲወጡ መርዳት እንዲሁም ምክርና ማበረታቻ መስጠት ትችላለህ።

በዚህ ጽሑፍ መጠቀም የምትችለው እንዴት ነው?

አንድን ርዕሰ ጉዳይ ለማግኘት፣ “ፈልግ” በሚለው ሣጥን ውስጥ ርዕሰ ጉዳዩን መጻፍ አሊያም በምድቦቹ ሥር መፈለግ ትችላለህ። ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት በሰባት ምድቦች ተከፋፍሏል፦ ተፈታታኝ ሁኔታዎች፣ ምግባር፣ ጉባኤ፣ ዕለታዊ ሕይወት፣ ቤተሰብ፣ መንፈሳዊነት እና ባሕርያት። አብዛኞቹ ርዕሰ ጉዳዮች በእነዚህ ምድቦች ውስጥ ይካተታሉ። ርዕሰ ጉዳዩ ሊገኝበት ይችላል ብለህ ያሰብከውን ምድብ ምረጥና ከሥሩ የተዘረዘሩትን ርዕሰ ጉዳዮች ቃኝ። የምትፈልገውን ርዕሰ ጉዳይ በየትኛው ምድብ ሥር እንደምታገኘው ግራ ከገባህ፣ ሁሉም የሚለውን ምረጥና ያሰብከውን ርዕሰ ጉዳይ እስክታገኝ ድረስ ወደ ታች እየወረድክ ዝርዝሩን ቃኘው። በእያንዳንዱ ርዕሰ ጉዳይ ሥር ደመቅ ተደርገው የተጻፉ አርዕስቶች ታገኛለህ። አንዳንዶቹ በዓረፍተ ነገር ሌሎቹ ደግሞ በጥያቄ መልክ የቀረቡ ናቸው። ከአርዕስቱ በታች ያሉትን ደመቅ ተደርገው የተጻፉ ጥቅሶች ስታነብ፣ ዓረፍተ ነገሩን በቀጥታ የሚደግፉት ወይም ጥያቄውን የሚመልሱት እንዴት እንደሆነ አሰላስል። የምትፈልገውን አርዕስት ማግኘት ቀላል እንዲሆን ለመርዳት ሲባል፣ አንድ ርዕሰ ጉዳይ በንዑስ ርዕሶች ተከፋፍሎ የሚቀመጥበት ጊዜ አለ። “በተጨማሪም . . . ተመልከት” ተብለው የተቀመጡ ጥቅሶችም አሉ። እነዚህ ጥቅሶች ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር ተያያዥ የሆኑ ሐሳቦችን ለማግኘት ያስችሉሃል። አብዛኛውን ጊዜ “ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች” የሚል ክፍልም ታገኛለህ። የጥቅሱን ዋና ነጥብ ወይም የሚያስተላልፈውን ትምህርት የሚያጎላ ዓረፍተ ነገር ይዟል። ጥቅሱን ስታነብ ይህን ዓረፍተ ነገር ተጠቅመህ ተፈላጊው ነጥብ ምን እንደሆነ አስብበት።

ይህ ጽሑፍ ለአንድ ርዕሰ ጉዳይ የሚሠሩ ጥቅሶችን ሁሉ ይዟል ማለት አይደለም። ሆኖም ለምታደርገው ምርምር ጥሩ መነሻ ይሆንልሃል። (ምሳሌ 2:1-6) ጠለቅ ብለህ ማጥናት ከፈለግህ አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኙትን የኅዳግ ማጣቀሻዎች እና ለጥናት የሚረዱ መረጃዎች ተመልከት። ስለ አንድ ጥቅስ ትርጉም ወይም ተግባራዊ ስለሚሆንባቸው አቅጣጫዎች ይበልጥ የተሟላ ግንዛቤ ለማግኘት፣ የምርምር መርጃ መሣሪያ ለይሖዋ ምሥክሮች እና የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫ (እንግሊዝኛ) ተጠቀም። የምታገኘው መረጃ ወቅታዊ እንዲሆን ቅርብ ጊዜ የወጣውን ማመሣከሪያ ጽሑፍ ተመልከት።

ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ የሚገኘውን የጥበብ፣ የእውቀትና የማስተዋል በር እንዲከፍትልህ ምኞታችን ነው። ይህን ጽሑፍ በተጠቀምክበት ቁጥር “የአምላክ ቃል ሕያውና ኃይለኛ” እንደሆነ ያለህ እምነት እየጨመረ እንደሚሄድ እንተማመናለን። —ዕብ 4:12

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ