የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lmd ትምህርት 9
  • ስሜትን መረዳት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ስሜትን መረዳት
  • ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ ምን አድርጓል?
  • ከኢየሱስ ምን እንማራለን?
  • ኢየሱስን ምሰል
  • የሌላውን ችግር እንደራስ መመልከት—ደግና ሩኅሩኅ ለመሆን የሚረዳ ባሕርይ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • የሌሎችን ስሜት መረዳት
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • የሌሎችን ስሜት የምትረዳ ሁን
    ንቁ!—2020
  • “በጣም አዘነላቸው”
    “ተከታዬ ሁን”
ለተጨማሪ መረጃ
ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
lmd ትምህርት 9

ተመላልሶ መጠየቅ

ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ከጀልባቸው ወርደው ወደ ባሕሩ ዳርቻ ሲሄዱ፤ ዳርቻው ላይ ሕዝቡ ተሰብስቦ እየጠበቃቸው ነው።

ማር. 6:30-34

ምዕራፍ 9

ስሜትን መረዳት

መሠረታዊ ሥርዓት፦ “ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ።”—ሮም 12:15

ኢየሱስ ምን አድርጓል?

ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ከጀልባቸው ወርደው ወደ ባሕሩ ዳርቻ ሲሄዱ፤ ዳርቻው ላይ ሕዝቡ ተሰብስቦ እየጠበቃቸው ነው።

ቪዲዮ፦ ኢየሱስ ለሕዝቡ አዘነላቸው

1. ቪዲዮውን ተመልከት፤ ወይም ማርቆስ 6:30-34ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦

  1. ሀ. ኢየሱስና ሐዋርያቱ ‘ብቻቸውን መሆን’ የፈለጉት ለምንድን ነው?

  2. ለ. ኢየሱስ ሕዝቡን እንዲያስተምር ያነሳሳው ምንድን ነው?

ከኢየሱስ ምን እንማራለን?

2. የሰዎችን ስሜት ለመረዳት ጥረት ማድረጋችን መልእክታችንን ስለማድረስ ብቻ ሳይሆን ስለ ሰዎቹም እንድናስብ ያነሳሳናል።

ኢየሱስን ምሰል

3. በጥሞና አዳምጥ። ግለሰቡ ሐሳቡን እንዲገልጽ ፍቀድለት። አታቋርጠው፤ ስሜቱን፣ የሚያሳስበውን ነገር ወይም ተቃውሞውን ሲገልጽ ወዲያውኑ ውድቅ ለማድረግ አትቸኩል። ትኩረት ሰጥተህ የምታዳምጠው ከሆነ ለአመለካከቱ አክብሮት እንዳለህ መረዳት ይችላል።

4. ስለ ግለሰቡ አስብ። ካደረጋችሁት ውይይት ተነስተህ ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦

  1. ሀ. ‘እውነት የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?’

  2. ለ. ‘መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናቱ የዛሬንም ሆነ የወደፊት ሕይወቱን የሚያሻሽልለት እንዴት ነው?’

5. ስለሚያስፈልገው ነገር አወያየው። መጽሐፍ ቅዱስን ቢያጠና ለጥያቄዎቹ መልስ የሚያገኘው እንዴት እንደሆነ እንዲሁም ለሕይወቱ የሚጠቅሙ ምን ምክሮች እንደሚያገኝ ሳትዘገይ አንሳለት።

ተጨማሪ ጥቅሶች

ሮም 10:13, 14፤ ፊልጵ. 2:3, 4፤ 1 ጴጥ. 3:8

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ