የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 7/1 ገጽ 31
  • በይሖዋ ተማመኑ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በይሖዋ ተማመኑ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አቅኚ ሆነህ ይሖዋን ልታገለግለው ትችላለህን?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 7/1 ገጽ 31

የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት

በይሖዋ ተማመኑ

የይሖዋ ምሥክሮች የሁሉም ብሔራት ሕዝቦች ስለ አዲሱ የአምላክ ዓለም ለማወቅ አጋጣሚ እንዲያገኙ የመንግሥቱን ምሥራች እንዲሰብኩ በይሖዋ ታዘዋል። በአንዳንድ አገሮች ብዙውን ጊዜ በሕዝበ ክርስትና ቄሶች ገፋፊነት ሥራችን ይታገዳል። የአንዲት አፍሪቃዊት ሀገር ሁኔታ እንደዚያ ነበር። ሆኖም እዚያ ያሉት የይሖዋ ምሥክሮች ልክ እንደ ዳዊት “በእግዚአብሔር ታመንሁ፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል?” የሚል አቋም አላቸው። (መዝሙር 56:11) በዚያች አገር ያሉት ወንድሞች ተሞክሮዎች በይሖዋ እንደሚተማመኑና እርሱ የሰጣቸውን በጣም አስፈላጊ የሆነ ሥራ እንደገፉበት ያሳያሉ።

የአንድ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የነበረ አንድ ምሥክር ‘ከሰው ይልቅ አምላክን እንደ ገዥው ቆጥሮ እርሱን ለመታዘዝ’ በመምረጥ በመንግሥት ጉዳዮች ገለልተኛ አቋሜን አልለውጥም አለ። (ሥራ 5:29) ክፉኛ ከተደበደበ በኋላ እንደ ከሃዲ ተቆጥሮ ይፈረድበታል ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ምሥክሩ ግን በይሖዋ ተማመነ። በታማኝነቱ ጸናና ኅሊናው ለምን እንደዚህ ያለ አቋም እንዲወስድ እንደሚያስገድደው አስረዳ። ውጤቱስ ምን ሆነ? ከክሱ ነፃ እንደሆነ ተፈረደለትና ወደነበረበት ከተማ ተመለሰ። የደበደቡት ባለሥልጣኖችም ይቅርታ ጠየቁት። ይህ ታማኝ ምሥክር ወደ መምህርነት ሥራው ተመለሰና የሥራ ዕድገት አግኝቶ የትምህርት ቤቶች ኢንስፔክተር ሆነ!

የአንድ ትምህርት ቤት አስተባባሪ ምሥክር የሆነውን መምህር ከሥራ አስወጣው። ከአንድ ወር በኋላ ይህ የትምህርት ቤት አስተባባሪ ከአንድ ልዩ አቅኚ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ የተባለውን መጽሐፍ አገኘና መጽሐፍ ቅዱስን አብሮት ለማጥናት ተስማማ። 6ኛውን ምዕራፍ ከጨረሰ በኋላ የትምህርት ቤት አስተባባሪነት ቦታውን ለቀቀና ከሚስቱ ጋር በስብሰባ መገኘት ጀመረ። አንድ ቀን እሑድ ጠዋት ያ ከሥራ የተባረረው ወንድም ከሥራ ያስወጣው ሰውዬ ምንም ሳያስበው በስብሰባ ላይ ሲያገኘውና መንፈሣዊ ወንድም ለመሆን መንገድ እንደጀመረ ሲያውቅ በጣም ተደነቀ፤ ተደሰተም።

ከዚሁ አገር የተገኘው ሌላው ተሞክሮ የይሖዋ ምሥክሮች ለይሖዋ ሥርዓት እንዴት አክብሮትን በሌሎች እንደሚቀርጹና ድርጅቱን ንጹሕ አድርገው እንደሚጠብቁ ያሳያል። ከጉባኤ ራቅ ብሎ በሚገኝ አንድ ገለልተኛ ስፍራ ያገለግል የነበረ አንድ ልዩ አቅኚ ብዙ ተቃውሞ አጋጠመው። ከሌላ ጐሣና አካባቢ የመጣ ስለነበረ የእውነት ተቃዋሚዎች ከመንደሩ ሊያባርሩት ፈለጉ። ነገር ግን የመንደሩ ሹም ጥሩ ጠባዮቹንና የአገልግሎቱን ውጤቶች እየጠቀሱ እርሱን ለማባረር ሳይስማሙ ቀሩ። ልዩ አቅኚው ከመጣ ጀምሮ ሕዝቡ ግብር በመክፈልና በሣምንት አንድ ጊዜ ኅብረተሰቡ በሚያደርገው የመንገድ ሥራ በመሳተፍ ለባለሥልጣኖች መታዘዝ እንደጀመሩ ሹሙ ልብ ብለውት ነበር።​—ሮሜ 13:1, 7

ከዚያም አንድ ምሽት ላይ ሌላ ምሥክር የይሖዋ ምሥክር ካልሆነች ሴት ጋር ምንዝር ሲፈጽም ተያዘ። የድርጊቱ ወሬ በጣም ተዛመተ። ልዩ አቅኚው በሹሙ ፊት እንዲቀርብ ተጠየቀና “ይኸው ወንድምህ ምንዝር ሲፈጽም ተይዟል። እናንተ የይሖዋ ምሥክሮች ከሌሎች ሰዎች የተለያችሁ አይደላችሁም” በማለት ተቆጡት። ልዩ አቅኚው ግን “ምንም እንኳ ፍጽምና የሌለን ብንሆንም ከሌሎች ሃይማኖቶች እንለያለን፤ ምክንያቱም ከባድ ኃጢአት በሚሠራበት ጊዜ አይተን እንዳላየን አናልፈውም” በማለት መለሰላቸው።

ምንዝር የፈጸመው ምሥክር እሥራትና የገንዘብ ቅጣት ተፈረደበት። ከዚህም በላይ ንስሐ ያልገባ በደለኛ በመሆኑ ከጉባኤው ተወገደ። ይህ እርምጃ ሹሙን በጣም ስላስገረማቸው በይሖዋ ምሥክሮች ላይ ይቀልዱ የነበሩትን ሰዎች አፍ አስዘጉ። “ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ክፉ አታውሩ። እውነት አላቸው። ሌሎች ሃይማኖቶች እንደዚህ ያለ እርምጃ አይወስዱም” በማለት ተናገሩ።

በዚያ አገር ያሉት ታማኝ ምሥክሮች በመዝሙር 37:3 ላይ ያለውን ምክር ይሠሩበታል፦ “[በይሖዋ ](አዓት) ታመን፤ መልካምንም አድርግ፤ በምድርም ተቀመጥ፤ ታምነህም ተሠማራ።” እኛስ እንደነዚህ ክርስቲያኖች በይሖዋ እንተማመናለንን?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ