የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 7/15 ገጽ 31
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘ይህ ለመታሰቢያ ይሁናችሁ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ፋሲካ ምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
  • የጌታ እራት—አምላክን የሚያስከብር በዓል
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 7/15 ገጽ 31

የአንባብያን ጥያቄዎች

◼ ኢየሱስን መታሰቢያውን በዓል ሐዋርያት ብቻ በተገኙበት ያቋቋመውና ወደ አዲሱ ኪዳን የሚገቡ ሌሎች ደቀ መዛሙርት በወቅቱ ያልተገኙት ለምንድን ነው?

ይህ ጥያቄ የተመሠረተው ኢየሱስ ቀደም ብሎ በአዲሱ ኪዳን ውስጥ ከገባው የቅቡዓን ክርስቲያን ጉባኤ ጋር የጌታን እራት ለማቋቋም ብሎ በዚያ ምሽት ከሐዋርያቱ ጋር ተሰበሰበ በሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ ላይ ነው። ከዚህ ይልቅ ኒሳን 14፣ 33 እዘአ የክርስቲያን ጉባኤ ገና አልተቋቋመም ነበር፤ ኢየሱስም ከሐዋርያቱ ጋር የተሰበሰበው ዓመታዊውን የማለፍ በዓል ለማክበር ነው።

እርግጥ ኢየሱስ ሐዋርያት ተብለው ከሚታወቁት ከ12ቱ በቀር ሌሎች ደቀ መዛሙርትም ነበሩት። ከመሞቱ ከአንድ ዓመት በፊት ሰባ ደቀ መዛሙርቱን ዞረው እንዲሰብኩ ልኳቸው ነበር። ከትንሣኤው በኋላ “ከአምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ።” እንደገናም በጴንጠቆስጤ ዕለት የተሰበሰቡ “መቶ ሃያ የሚያህሉ” ነበሩ። (1 ቆሮንቶስ 15:6፤ ሥራ 1:15, 16, 23፤ ሉቃስ 10:1-24) ይሁን እንጂ ኢየሱስ የጌታ እራት የተሰኘውን ዓመታዊ በዓል በደነገገበት ጊዜ ከኢየሱስ ጋር የነበረውን ቡድን እስቲ እንመልከት።

ሉቃስ 22:7, 8 “ፋሲካንም ሊያርዱበት የሚገባው የቂጣ በዓል ደረሰ። ጴጥሮስንና ዮሐንስንም፦ ፋሲካን እንድንበላ ሄዳችሁ አዘጋጁልን ብሎ ላካቸው” በማለት ወቅቱን ይነግረናል። ታሪኩ በመቀጠልም “ለባለቤቱም፣ መምህሩ፦ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ቤት ክፍል ወዴት ነው ይልሃል በሉት” በማለት ይነግረናል። ስለዚህ በዚያ ምሽት ኢየሱስ ከ12ቱ ጋር የተሰበሰበው ለአይሁዳዊው በዓል ነበር። “ከመከራዬ በፊት ከእናንተ ጋር ይህን ፋሲካ ልበላ እጅግ እመኝ ነበር” ብሎ ነገራቸው።​—ሉቃስ 22:11, 15

የማለፍ በዓል በግብፅ መከበር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በቤተሰብ መልክ የሚከበር በዓል ነበር። የማለፍ በዓልን ሲያቋቁም አምላክ ለየእያንዳንዱ ቤተሰብ አንድ የበግ ጠቦት መታረድ እንዳለበት ለሙሴ ነግሮታል። አንድ ሙሉ በግ በልቶ ለመጨረስ ቤተሰቡ በጣም አነስተኛ ከሆነ በእራቱ እንዲካፈል የጎረቤት ቤተሰብ ሊጋበዝ ይችል ነበር። ስለዚህ ከኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አብዛኞቹ ለ33 እዘአ የማለፍ እራት ከየራሳቸው ቤተሰቦች ጋር ይሰበሰቡ እንደነበረ ግልጽ ነው።

ይሁን እንጂ ኢየሱስ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት የነበረውን የመጨረሻ የማለፍ በዓልና ከሞቱ በፊት የመጨረሻው ምሽት የሆነውን ዕለት በአገልግሎቱ ብዙውን ጊዜ አብረውት ከተጓዙት ከተከታዮቹ መሃል በጣም ከቀረቡት ጋር ለማሳለፍ “እጅግ ተመኝቶ” ነበር። በዚያ የማለፍ እራት ፍጻሜ ላይ ኢየሱስ ወደፊት በሁሉም ተከታዮቹ ሊከበር ስለሚገባው አዲስ በዓል ነገራቸው። የዚያ ገና ወደፊት የሚከበረው ክርስቲያናዊ በዓል ወይን ጠጅ የሕጉን ቃል ኪዳን የሚተካውን “የአዲሱን ኪዳን” ደም የሚያመለክት ነበር።​—ሉቃስ 22:20

ሆኖም ኒሳን 14 ቀን 33 እዘአ ማታ አዲሱን ኪዳን የሚያጸድቀው መሥዋዕት ማለት ኢየሱስ ገና መስዋዕት ሆኖ ባለመቅረቡ አዲሱ ኪዳን ያን ዕለት ገና አልተቋቋመም ነበር። የሕጉ ቃል ኪዳን ገና በሥራ ላይ ነበር። ገና በእንጨት ላይ አልተቸነከረም ነበር። ከዚህም ሌላ ከሥጋውያን እስራኤል ጋር የተደረገው አሮጌው ኪዳን ከመንፈሳውያን እስራኤላውያን ጋር በተገባው አዲስ ኪዳን መተካቱ እስከ ጴንጠቆስጤ ዕለት ድረስ በግልጽ አይታይም ነበር።​—ገላትያ 6:16፤ ቆላስይስ 2:14

ስለዚህ በዚያ ምሽት አሥራ አንዱ ታማኝ ሐዋርያትም ሆኑ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት በአዲሱ ቃል ኪዳን ውስጥ አልገቡም ነበር። በመሆኑም ኢየሱስ ሌሎቹ አይሁዳውያን ደቀ መዛሙርቱ የማለፍን በዓል ከየቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲያከብሩ መፍቀዱ ስላልተቀበላቸው አይደለም።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ