ገባኦናውያን ሰላምን ፈልገው ነበር
ከዚህ በላይ ያለው ከኢየሩሳሌም በስተ ሰሜን 9 ኪሎሜትር ርቆ በሚገኘው ኮረብታ ላይ የምትገኘው ከተማ የጥንቷ ገባኦን ነች ተብሎአል።
ገባኦን እውቅ ከተማ የሆነችው ኢያሱ እሥራኤላውያንን መርቶ ወደ ተስፋይቱ ምድር ካገባና ኢያሪኮን ድል ካደረገ በኋላ እንደሆነ ታውቅ ይሆናል። በገባኦን ይኖሩ የነበሩት ከነዓናውያን መለኮታዊ ድጋፍ እንዳላቸው በግልጽ የታየባቸውን እሥራኤላውያንን ለመቋቋም እንደማይችሉ ተገንዝበዋል። ታዲያ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ? ገባኦናውያን ዘዴ በመጠቀም ከሩቅ አገር ተጉዘው የመጡ የሚመስሉ መልእክተኞችን ላኩ። ለሰላም ያደረጉት ይህ ጥረት ተሳካ። እሥራኤላውያንም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረጉ። ዘዴአቸው በታወቀባቸው ጊዜ ግን ገባኦናውያን እንጨት ለቃሚዎችና ውኃ ቀጂዎች ሆኑ።
አምላክ ሰላምን በፈለጉበት በእነዚህ ሕዝቦች አልተከፋም። ገባኦናውያን በአምስት ነገሥታት በተወረሩ ጊዜ ኢያሱ እነርሱን ለመከላከል ባደረገው ውጊያ አምላክ ረድቶታል። እንዲያውም ይሖዋ በዚያ ጦርነት ላይ ቀኑን በማርዘም ተአምር አድርጓል።—ኢያሱ 9:3-27፤ 10:1-14
የመሬት ቁፋሮ አጥኚዎች በዚህ ጉብታ ጠንካራ ዓለት ላይ የተቆፈረ ጥልቅ ጉድጓድ ወይም ኩሬ አግኝተዋል። ገባኦናውያን ወደ እዚህ ጉድጓድ በደረጃዎች ላይ ተረማምደው ሊወርዱና ከመሬት ስር ከሚገኘው ኩሬ ውኃ ሊቀዱ ይችሉ ነበር። በ2 ሳሙኤል 2:13 ላይ የተጠቀሰው “የገባኦን ውኃ” ይህ ጉድጓድ ይሆንን? የመሬት ቁፋሮ ጥናት ተመራማሪዎች ከአለት የተቦረቦረ የወይን ጠጅ ማከማቻና የተለያዩ የወይን ጠጅ መስሪያ መሳሪያዎች አግኝተዋል። አዎን ገባኦን የወይን ጠጅ ማምረቻ ማዕከል የነበረች ይመስላል።
በዳዊት ጊዜ የእውነተኛው አምላክ የመገናኛ ድንኳን ይገኝ የነበረው እዚህ ነው። ንጉሥ ሰለሞን መስዋዕት ለማቅረብ ወደዚህ መጥቶ ነበር። ይሖዋ ለሰለሞን በህልም ተገለጠለትና “ጥበብና አስተዋይ ልብና” እንዲሁም ሀብት እንደሚሰጠው ቃል ገባለት። (1 ነገሥት 3:4-14፤ 2 ዜና 1:3) በዚህ እትም በገጽ 12-17 ላይ የወጣው ርዕሰ ትምህርት በገባኦን ይኖሩ የነበሩት ሰዎች ተወላጆች ከጊዜ በኋላ በአምላክ ሕዝቦች መካከል የተለየ መብት እንዳገኙ ይገልጻል። እንዴት ያለ መብት እንዳገኙ ታውቃለህን?
[በገጽ 32 ላይ የሚገኘው ሥዕል ምንጭ]
Pictorial Archive (Near Eastern History) Est.