የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 4/15 ገጽ 31
  • ማስታወቂያ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለአስተዳደር አካል ኮሚቴዎች የቀረበ እርዳታ
  • የበላይ አካሉ አደረጃጀት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • “የተሰጡ” ሰዎች፣ የይሖዋ ዝግጅት ክፍል ናቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • በዛሬው ጊዜ የአምላክን ሕዝቦች የሚመራው ማን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • በዛሬው ጊዜ የበላይ አካሉ ሥራውን የሚያከናውነው እንዴት ነው?
    በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 4/15 ገጽ 31

ማስታወቂያ

ለአስተዳደር አካል ኮሚቴዎች የቀረበ እርዳታ

በአሁኑ ጊዜ በቁጥር 12 የሆኑት የይሖዋ ምሥክሮች የአስተዳደር አካል አባላት በተሰጣቸው የሥራ ምድብ በታማኝነት በማገልገል ላይ ናቸው። ሁልጊዜም በቁጥር እየጨመሩ የሄዱት “የእጅግ ብዙ ሰዎች” አባላት ለሚሰጡአቸው ቅንዓት የተሞላበት ድጋፍ በጣም አመስጋኞች ናቸው። (ራእይ 7:9, 15) በመላው ዓለም አጣም ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ በመገኘቱ የአስተዳደር ክፍሉ ተጨማሪ እርዳታ ማግኘት አስፈልጎታል። በዚህም ምክንያት በአብዛኛው የእጅግ ብዙ ሰዎች አባላት ከሆኑት ወንድሞች መካከል በርካታ ረዳቶች የአስተዳደር አካል ኮሚቴዎች በሚያደርጓቸው ስብሰባዎች እንዲካፈሉ ለመጋበዝ ተወስኖአል። እነዚህም ኮሚቴዎች የፐርሶኔል ኮሚቴ፣ የህትመት ኮሚቴ፣ የአገልግሎት ኮሚቴ፣ የትምህርት ኮሚቴና የጽሑፍ ኮሚቴ ናቸው። እነዚህ ረዳቶች የአስተዳደር አካል ኮሚቴ አባላት በሚሰጡአቸው አመራር ሥር ሆነው በስብሰባዎቹ ላይ በሚደረጉት ውይይቶች ይካፈላሉ። ኮሚቴው የሚሰጣቸውንም የተለያዩ ተግባራት ያከናውናሉ። ይህ አዲስ ዝግጅት የሚጀምረው ከግንቦት 1, 1992 ጀምሮ ነው።

ለበርካታ ዓመታት የተቀቡ ምሥክሮች ቀሪዎች ቁጥር እያነሰ ሲሄድ የእጅግ ብዙ ሰዎች ቁጥር ግን ከገመትነው በላይ በጣም አድጎአል። (ኢሳይያስ 60:22) ይህን የመሰለ ታላቅ መስፋፋት በማግኘታችን ይሖዋን እናመሰግነዋለን። የይሖዋ ምሥክሮች የሚለውን አዲስ ስም በታላቅ ምሥጋና በተቀበልንበት በ1931 የመንግሥት አስፋፊዎች ከፍተኛ ቁጥር 39,372 ነበር። ከእነዚህ መካከል አብዛኞቹ ቅቡዓን የክርስቶስ ወንድሞች ነን የሚሉ ነበሩ። (ኢሳይያስ 43:10-12፤ ዕብራውያን 2:11) ከ60 ዓመታት በኋላ ማለትም በ1991 በዓለም በሙሉ የሚገኙት አስፋፊዎች ከፍተኛ ቁጥር 4,278,820 ነበር። ከእነዚህ መካከል ከቅቡዓን ቀሪዎች ክፍል ነን ይሉ የነበሩት 8,850 ብቻ ነበሩ። ቅዱሳን ጽሑፎች አስቀድመው በተናገሩት ትንቢት መሠረት “እጅግ ብዙ ሰዎች” “የታናሹን መንጋ” ቀሪዎች 480 ጊዜ ይበልጣል። (ሉቃስ 12:32፤ ራእይ 7:4-9) ቀሪዎቹ በጣም እየሰፋ የሄደውን የመንግሥቱን ጉዳዮች ሲያስተዳድሩ የእጅግ ብዙ ሰዎች ትብብርና ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። ይህንንም ትብብርና ድጋፍ በአድናቆት ይቀበላሉ።

በዚህ መጠበቂያ ግንብ ላይ እንደተብራራው በአሁኑ ጊዜ ከአይሁዳውያን ቀሪዎች ጋር ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱት ናታኒምና የሰለሞን ባሪያዎች ልጆች ጋር የሚመሳሰሉ ከመንፈሳዊ እስራኤላውያን ጋር የሚያገለግሉ ሰዎች አሉ። እነዚህ እስራኤላውያን ያልነበሩ ሰዎች ከግዞት ከተመለሱት ሌዋውያን እንኳን በቁጥር ይበልጡ ነበር። (ዕዝራ 2:40-58፤ 8:15-20) በዛሬው ጊዜ ከሚገኙት እጅግ ብዙ ሰዎች መካከል የቅርንጫፍ የበላይ ተመልካቾች በመሆን፣ በተጓዥ የበላይ ተመልካችነትና በምድር በሙሉ በሚገኙት ከ66,000 የሚበልጡ ጉባኤዎች ውስጥ በማገልገል ብዙ ተሞክሮ ያካበቱ “የተሰጡ” ሰዎች አሉ።

በቅርቡ የበላይ ተመልካቾችንና ረዳቶቻቸው የሆኑትን ዲያቆናት ለማሠልጠን ሲባል የመንግሥት አገልግሎት ትምህርት ቤቶች በዓለም ዙሪያ ተደርገዋል። በዩናይትድ ስቴትስ ብቻ 59,420 የበላይ ተመልካቾች በትምህርት ቤቱ ተገኝተዋል። ስለዚህ እነዚህ ሽማግሌዎች የሥራ ኃላፊነታቸውን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማከናወን የሚያስችላቸውን ትጥቅ አግኝተዋል ማለት ነው።—1 ጴጥሮስ 5:1-3፤ ከኤፌሶን 4:8, 11 ጋር አወዳድር።

የይሖዋ ምሥክሮች ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኝበት በብሩክሊን ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉ “የተሰጡ” ወንድሞች አሉ። ከእነዚህም መካከል የእጅግ ብዙ ሰዎች አባላት የሆኑና ከፍተኛ ችሎታና ተሞክሮ ያካበቱ የጎለመሱ የበላይ ተመልካቾች ይገኛሉ። በዚህም ምክንያት የአስተዳደር አካሉ ከእነዚህ የበላይ ተመልካቾች መካከል ጥቂቶቹን መርጦ በአስተዳደር አካል ኮሚቴዎች ስብሰባዎች ላይ እርዳታቸውን እንዲያበረክቱ አድርጎአል። እነዚህ ወንድሞች የተመረጡት በአገልግሎት ዓመታቸው ብልጫ አይደለም። ከዚህ ይልቅ በተወሰኑ መስኮች እርዳታ ለመስጠት የሚያስችል ብቃት ያላቸው የጎለመሱና ተሞክሮ ያላቸው ወንድሞች ስለሆኑ ነው። የኮሚቴ አባላት ሆነው እንዲያገለግሉ መመደባቸው ልዩ የሆነ ደረጃ አያሰጣቸውም። ኢየሱስ ስለ ደቀ መዛሙርቱ እንደተናገረው “ሁላችሁም ወንድማማቾች ናችሁ”። (ማቴዎስ 23:8) ሆኖም እነዚህ ሰዎች ብዙ አደራ የሚጣልባቸው ናቸው። “ብዙም ይጠበቅባቸዋል።”—ሉቃስ 12:48

የይሖዋ ድርጅት በሚያደርገው ግስጋሴ በጣም እንደሰታለን። ባለፉት አሥርተ ዓመታት የመስክ አገልጋዮች ቁጥር መቶ በመቶ ጨምሮአል። ይህም ታላቁ ዳዊት ስለሆነው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተነገረው ትንቢት ጋር የሚስማማ ነው። “ለመንግሥቱና ለሰላሙ መስፋፋት ፍጻሜ አይኖርም።” (ኢሳይያስ 9:7 ኪንግ ጀምስ ትርጉም) የኢየሩሳሌም ቅጥር በሚጠገንበት ጊዜ ናታኒም ከሌዋውያን ጎን ተሰልፈው እንደሠሩ ዛሬም “መጻተኞች ቅጥርሽን ይሠራሉ” የሚለው ስለ ይሖዋ ድርጅት የተነገረ ትንቢት በተመሳሳይ ሁኔታ በመፈጸም ላይ ነው። (ኢሳይያስ 60:10፤ ነህምያ 3:22, 26) የዘመናችን ናታኒም እውነተኛውን አምልኮ ለመገንባት በሚያሳዩት ቅንዓት የሚመሰገኑ ናቸው። በዓለም አቀፉ የይሖዋ ድርጅት ውስጥ በሚሰጣቸው በማንኛውም ዓይነት ሥራ ወይም አገልግሎት “የይሖዋን ካህናት” ይረዳሉ።—ኢሳይያስ 61:5, 6

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ