የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 7/1 ገጽ 30
  • ችግርና አደጋ ቢኖርም መጡ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ችግርና አደጋ ቢኖርም መጡ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 7/1 ገጽ 30

ችግርና አደጋ ቢኖርም መጡ

ቀኑ ጥር 2, 1992 ነበር። ቦታው ኢንሀምቤን ክፍለ ሐገር፣ ማኪኬ ነው። ሬዲዮ ሲከፈት በሞዛምቢክ የሚሰሙት የአፍሪካ ምሽት ድምፆች ተቋረጡ። “የይሖዋ ምሥክሮች በክፍለ ሐገራችን ‘ነፃነት አፍቃሪዎች’ የተባለውን ስብሰባቸውን እያካሄዱ ናቸው” ሲል የሬድዮ አስተዋዋቂው ተናገረ። “ዓላማቸውም በዛሬው ዓለም ውስጥ እውነተኛ ነፃነት እንዴት ሊገኝ እንደሚችል ለሰዎች ማስተማር ነው። ሁላችሁም በስብሰባው ላይ እንድትገኙ ተጋብዛችኋል” አለ።

በዚህ በአፍሪካ አህጉር ጠርዝ ላይ በሚገኝ አካባቢ ታሪካዊ የሆነ ነገር በመከናወን ላይ ነው! የይሖዋ ምሥክሮች ለመጀመሪያ ጊዜ የወረዳ ስብሰባ ሊያደርጉ ነው። በዚህ ስብሰባ ላይ ለመገኘት 1,024 ሰዎች ከተለያዩ አካባቢዎች መጥተዋል። በሞዛምቢክ ውስጥ የይሖዋ ምሥክሮች ሥራ ታግዶ ስለነበረ ከጥቂት ዓመታት በፊት እንደዚህ ያለውን ስብሰባ ማድረግ ፈጽሞ ሊታሰብ የማይችል ነገር ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ሲባል ስለተከፈለው ድፍረት የተሞላበት መስዋዕትነት ለመስማት ትፈልጋላችሁን?

የኢንሀምቤን ክፍለ ሐገር እንደ ሌሎቹ የአፍሪካ ክፍሎች በጣም ውብ ነች። የሦስት ማዕዘን ቅርጽ ያላቸው ዓሣ አጥማጅ ጀልባዎች በባሕሩ ጠረፍ ላይ ሲቀዝፉ ይታያሉ። የኮኮነት ተክሎች በብዛት አሉ። ይሁን እንጂ በገጠሩ አካባቢ ትልቅ ስጋት አለ። እርሱም የእርስ በእርስ ጦርነት ነው!

ከዘንባባ ቅጠል በተሠራ ጎጆ ውስጥ የተኙ ሰዎች በጫካው ውስጥ በሚደረገው ውጊያ በሚተኮሱት የከባድ መሣሪያዎችና የጠመንጃ ተኩስ ድምፅ ባንነው መነሳታቸው ያልተለመደ ነገር አልነበረም። አብዛኛውን ጊዜ በጦርነቱ የሚጎዱት ንጹሐን ዜጎች ናቸው። አንዳንድ ጊዜ እጅና እግራቸውን ያጡ ልጆች እያነከሱ ሲሄዱ ይታያሉ። አንዳንድ የይሖዋ ምሥክሮችም እንኳን በደረሰባቸው ጭካኔ ምክንያት በፊታቸውና በሰውነታቸው ላይ ጠባሳ አለባቸው።

እነዚህ ሁኔታዎች ቢኖሩም በስብሰባው ላይ የተገኙት ሁሉ “በነፃነት አፍቃሪዎች” ስብሰባ በጣም ተደስተዋል። ወደ ስብሰባው በሚወስደው መንገድ ላይ ያደፈጡ ሽፍቶች ሊኖሩ ቢችሉም በገጠር ያሉ ብዙ ቤተሰቦች ወደ ስብሰባው ለመምጣት ቆርጠዋል። በተጨማሪም የሚገኘው የሕዝብ መጓጓዣ ክፍት የሆኑ የጭነት መኪናዎች ብቻ ስለሆኑ ወደ ስብሰባው የሚያደርሰው ጉዞ በጣም አስቸጋሪ ነበር። አንዳንድ ጊዜ በአንድ የጭነት መኪና ላይ እስከ 400 የሚደርሱ ተሳፋሪዎች ይታጨቁበታል! እነዚህ የጭነት መኪናዎች በታጠቁ ወታደራዊ አጃቢዎች እንዲታጀቡ ሲባል በሰልፍ ይቆማሉ።

ኖራ እና አንድ፣ ሦስትና ስድስት ዓመት የሆናቸው ሴቶች ልጆችዋ በዚህ አስቸጋሪ በሆነ መንገድ ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው ወደ ስብሰባው ከመጡት ቤተሰቦች መካከል ናቸው። ኖራ ለጉዞው የሚያስፈልጋትን ገንዘብ ማጠራቀም የጀመረችው ከብዙ ወራት በፊት ነበር። ስብሰባው በሚደረግበት ቦታ የማረፊያ ቦታ ሊገኝ አለመቻሉ ከስብሰባው አላስቀራትም። ኖራና ቤተሰቦቿ ከብዙ ሌሎች ሰዎች ጋር ሆነው እዚያው ስብሰባው በሚካሄድበት ሜዳ ላይ ምግብ ያበስላሉ፣ ይበላሉ፣ እዚያው ሜዳው ላይ ይተኛሉ።

ኃይለኛው የሐሩር ሙቀትና ከዚያ በኋላ የሚከተለው ከባድ ዝናብ ወንድሞች አንድ ላይ ሆነው መንፈሳዊ ድግስ ከመካፈል ያገኙትን ትልቅ ደስታ አላቀዘቀዘባቸውም። በዚያ ስብሰባ ላይ ከመገኘት የሚበልጥ ምንም ነገር እንደሌለ ተሰምቷቸዋል። በጠቅላላው 17 ሰዎች ሞቅ ባለው የህንድ ውቅያኖስ ውኃ ውስጥ በመጠመቅ ለአምላክ መወሰናቸውን አሳይተዋል። ጥምቀቱ በሚከናወንበት ወቅት ዙሪያውን ግጥም ብለው የነበሩት ደስተኛ ተመልካቾች ከልባቸው ይሖዋን በመዝሙር ለማመስገን ተገፋፍተው ነበር።

ይህ የአምላኪዎች ቡድን አምላካዊውን ነፃነት ማፍቀር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ተረድቷል። ከዋና ከተማዋ ከማፑቶ ተወክሎ የመጣው ሐንስ “በዚህኛው የአፍሪካ ክፍል የይሖዋ ምሥክሮች ሥራ አዲስ ምዕራፍ ሲከፈት ተመልክተናል” ብሏል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ