የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 8/15 ገጽ 31
  • ለመመለስ የሚያስችል እርምጃ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለመመለስ የሚያስችል እርምጃ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 8/15 ገጽ 31

ለመመለስ የሚያስችል እርምጃ

‘በምሳሌ ተናገራቸው።’ በእነዚህ ቃላት ነው መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጠፋው በግ፣ ስለ ጠፋው ድሪምና ስለ አባካኙ ልጅ ምህረትን የሚመለከቱ የኢየሱስን ሦስት ምሳሌዎች የጀመረው።—ሉቃስ 15:3-32

በሚያዝያ 15/1991 መጠበቂያ ግንብ ላይ የወጡ ሁለት ርዕሰ ትምህርቶች እነዚህን ሦስት የኢየሱስ ምሳሌዎች በመተንተን ዛሬም ምህረት እንዴት ሊሠፋ እንደሚችል እንዲያዩ በማድረግ ብዙ አንባቢዎችን ረድተዋል። ቀዳሚ ትኩረት የተደረገው በመንፈሳዊ እረኞች ላይ ሲሆን የተወገዱና ለሚደረግላቸው የደግነት ጥየቃ አዎንታዊ ምላሽ ሊሰጡ የሚችሉ ሰዎችን በራሳቸው አነሳሽነት ሄደው እንዲያነጋግሩ ነበር። የእነዚህ ርዕሰ ትምህርቶችና የአዲሱ አሠራር ውጤት ምን ሆነ?

መጽሔቱ እንደታተመ ወዲያውኑ በዩናይትድ ስቴትስ በዋሽንግተን ግዛት የሚኖር አንድ ሰው እንደሚከተለው ሲል ጻፈ፦ “ዛሬ የተትረፈረፈው የይሖዋ ደግነት ማስረጃ በፖስታ ቤት ደረሰኝ። በልዑሉ አምላክ በኩል በቀረቡት ዝግጅቶችና የአሠራር መስተካከል ዓይኔ በእንባ፣ ልቤ ደግሞ በደስታ ተሞልቶ እዚህ ቁጭ ብያለሁ። ለጠፉት በግ መሰል ሰዎች እርዳታ ሊያቀርብ የሚችለው በእርግጥ ፍትሕ ያለው አምላክ ብቻ ነው። . . . አዎን፣ ተወግጄ ነበር፣ አሁን ግን ለመመለስ በመንገድ ላይ ነኝ።” ይህ ሰው በጥቅምት ወር ከውገዳው ተመልሷል።

በሁለት የጉባኤ ሽማግሌዎች የተደረጉ ጉብኝቶች ውጤትስ ምን ነበር? አንዲት ክርስቲያን ሚስት እንደሚከተለው በማለት ጽፋለች፦ “ስሜቴን ቃላት ሊገልጹት አይችሉም። ባሌ ለ13 ዓመታት ተወግዶ ቆይቷል። በርዕሰ ትምህርቶቹ ላይ በተሰጠው ሐሳብ መሠረት ሽማግሌዎቹ ጠየቁት። ከብዙ ዓመታት በኋላ ትናንትና ማታ ለመጀመሪያ ጊዜ ከስብሰባዎቹ ወደ አንዱ ሄደ። አሁን ሕይወቱን ለማስተካከልና ለመመለስ እየጣረ ነው።”

ተጓዥ የበላይ ተመልካቾች የተለያዩ ጉባኤዎችን ሲጎበኙ ውጤቱን ተመልክተዋል። አንድ የክልል የበላይ ተመልካች በቅርቡ የሚከተለውን ጽፎ ነበር፦

“የሚያዝያ 15/1991 መጠበቂያ ግንብ ሲታተም ሽማግሌዎቹ የተወገዱትን ሰዎች ሄደው ሲያነጋግሩ ውጤቱ ምን ይሆን ብለው ብዙ ሰዎች አስበው ነበር። አሁን መልሱ በጣም ግልጽ ሆኗል።

“በክልላችን ከጎበኘኋቸው አራት ጉባኤዎች ዘጠኝ የተወገዱ ሰዎች ወደ መንግሥት አዳራሾች መመለሳቸውን አይተዋል። እስካሁን ከውገዳው የተመለሰው አንድ ብቻ ቢሆንም የተቀሩት ስምንት ሰዎች መልካም መሻሻል እያደረጉ ናቸው። ሽማግሌዎቹና ጉባኤዎቹ የድካማቸውን ፍሬና ቲኦክራቲካዊ መመሪያዎችን በሥራ ላይ የማዋልን ጥበብ በማየታቸው በጣም ተደስተዋል።

“በዚህ መልካም በሆነ የምህረት ዝግጅት ተደስተናል። አንዲት ከውገዳ የተመለሰች እህት ‘በይሖዋ ፊት የተወገዝኩ ሆኖ ይሰማኝ ስለነበረ በራሴ አነሳሽነት ለመመለስ ድፍረት አልነበረኝም። ሽማግሌዎቹ ሲጠይቁኝ ግን ለመመለስ የሚያስፈልገኝን ብርታት አገኘሁ’ በማለት እንደተናገረችው ነው። አድናቆቷ ጉባኤውን በጣም አበረታቶታል።”

ጉብኝት የተደረገላቸው ብዙ ሰዎች ምላሽ ባይሰጡም እንኳን ይህ ምህረት የተሞላበት ዝግጅት የሚያከናውነው ብዙ መልካም ነገር አለ። ስለዚህ ከመስከረም ጀምሮ በእያንዳንዱ ጉባኤ ያሉ ሽማግሌዎች በክልላቸው ያሉትን የተወገዱ ሰዎች ስም እንደገና በመመርመር ለተዘረጋላቸው ምህረት ምላሽ ይሰጣሉ ብለው የሚያስቧቸውን ሰዎች ለመጎብኘት ዝግጅት ያደርጋሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ