የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 8/15 ገጽ 32
  • ጳጳሳቱ ሊቋቋሟቸው አልቻሉም!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጳጳሳቱ ሊቋቋሟቸው አልቻሉም!
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 8/15 ገጽ 32

ጳጳሳቱ ሊቋቋሟቸው አልቻሉም!

ባለፈው ዓመት ለካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በጣም አሳሳቢ በሆኑ አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት የሊቃነ ጳጳሳት ከፍተኛ ስብሰባ ተደርጎ ነበር። ኢል ሳቶ በተሰኘው ጋዜጣ መሠረት ከእነዚህ አሳሳቢ ጉዳዮች መካከል አንዱ “የሃይማኖታዊ ኑፋቄዎች ተስፋፊነት” ነው። ይሁን እንጂ ጋዜጣው “ጳጳሳቱ በዚህ ጉዳይ ላይ ወደ ስምምነት ለመድረስ ችግር ሊኖርባቸው አይገባም። በአዳዲስ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ክስተት ላይና በተቻለ መጠን መስፋፋታቸውን በመከልከል አስፈላጊነት ላይ ጥልቅ ጥናት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ሁሉም ተስማምተውበታል” ብሏል።

በግልጽ እንደሚታየው “የሃይማኖታዊ ኑፋቄዎች ተስፋፊነት” ችግር የሆነው በኢጣሊያ ብቻ አይደለም። ኢል ሳቶ እንደዘገበው “ኪሪል የሚባሉ የስሞሌንስክ [ከሩሲያ የቀድሞ ከተሞች አንዷ] ጳጳስ በቅርቡ ቫቲካንን በጎበኙበት ጊዜ . . . በሶቪየት ህብረት የይሖዋ ምስክሮችንና የተመሳሳይ ሃይማኖታዊ ወገኖችን ኃይል ሰባሪ ዕድገት ለመቋቋም እንዲቻል ሃይማኖት ነክ እርዳታ እንዲሰጣቸው ፓፓውን ጠይቀው ነበር።”

በመጀመሪያው መቶ ዘመንም ክርስትና በተከታዮቹ አማካኝነት በኃይል ሲስፋፋ የተደራጀ ሃይማኖት መሪዎች ተመሳሳይ እሮሮ አሰምተው ነበር። በአንድ ወቅት ቁጣ የተሞሉ አይሁዳውያን ለከተማው ገዢዎች “ዓለምን ያወኩ እነዚህ ወደዚህ ደግሞ መጥተዋል” በማለት አቤቱታ አቅርበው ነበር። (ሥራ 17:6) በዚያ ዘመን የሃይማኖት መሪዎች የክርስትናን መስፋፋት ለማስቆም ብዙ ጥረው ሳይሳካላቸው ቀርቷል። ዛሬም የእውነተኛ ክርስትናን መሠረተ ትምህርት ስርጭት ለማስቆም የሚደረግ ማንኛውም ጥረት አይሳካም። አምላክ ራሱ “በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፤ በፍርድም በሚነሣብሽ ምላስ ሁሉ ላይ ትፈርጂበታለሽ። የእግዚአብሔር [ይሖዋ አዓት] ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፣ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው” በማለት ቃል ገብቷል።—ኢሳይያስ 54:17

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ