የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 10/15 ገጽ 19
  • “ወደ . . . ስም ውስጥ” መጠመቅ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ወደ . . . ስም ውስጥ” መጠመቅ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የጥምቀትህ ትርጉም
    እውነተኛውን አንድ አምላክ አምልክ
  • “በመንፈስ ቅዱስ ስም”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • መጠመቅ ለምን አስፈለገ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • አምላክን ለዘላለም ማገልገልን ዓላማህ አድርግ
    ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 10/15 ገጽ 19

“ወደ . . . ስም ውስጥ” መጠመቅ

በዚህ መቶ ዘመን መጀመሪያ ላይ በግብጽ አሸዋዎች ውስጥ ተቀብረው የተገኙት በሺህ የሚቆጠሩ የጥንት ዓለማዊ የፓፒረስ ጽሑፎች ጥናት አብዛኛውን ጊዜ በክርስቲያን የግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች ላይ ብርሃን አብርተዋል። እንዴት? የአንዳንድ ቃላትን አጠቃቀም በመመልከት እነዚህ ቃላት በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ያላቸውን አገባብ ይበልጥ ትክክለኛ በሆነ ሁኔታ እንድንረዳ ይመሩናል።

አንዱ ምሳሌ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት ደቀ መዛሙርቱን “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው . . . ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው” ብሎ ሲያዛቸው ‘በ . . . ስም መጠመቅ’ ብሎ የተጠቀመበት አነጋገር ነው። ኢየሱስ ምን ማለቱ ነበር?—ማቴዎስ 28:19

ዓለማዊ ጽሑፎች “በ . . . ስም” ወይም “ወደ . . . ስም ውስጥ” (ኪንግደም ኢንተርሊኒየር) የሚለውን አገላለጽ “ለማንኛውም ሰው ዕዳ መክፈልን” ለማመልከት እንደተጠቀመበት ምሑራን አውቀዋል። በሃይማኖት ትምህርት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር ጂ አዶልፍ ዲስማን ከፓፒሪው ከተገኘው ማስረጃ አንፃር ሲታይ “ወደ ጌታ ስም ውስጥ መጠመቅ ወይም በአምላክ ልጅ ስም ላይ ማመን ከሚለው አነጋገር ጀርባ ያለው ሐሳብ ጥምቀት ወይም እምነት የአምላክ ወይም የአምላክ ልጅ ንብረት ሆኖ መቆጠርን ያመለክታል የሚል ነው” ብለው ያምናሉ።—በኢታሊክስ የጻፉት ዲስማን ናቸው

በኢየሱስ ዘመን የነበሩ አይሁዶችም ተመሳሳይ በሆነ አነጋገር ይጠቀሙ ነበር። ቲኦሎጂካል ዲክሽነሪ ኦቭ ዘ ኒው ቴስታመንት እንደሚያብራራው “በአይሁድ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ተቀባይነት እንዲያገኝ ወደ ይሁዲነት የተለወጠው ሰው የሚገረዘው . . . ‘ወደ ይሁዲነት በተለወጠው ሰው ስም’ ነበር። በቃል ኪዳኑ ተቀባይነት እንዲያገኝ ደግሞ ይህ ግዝረት የሚከናወነው . . . ‘በቃል ኪዳኑ ስም’ ነበር።” በዚህ ሁኔታ አዲስ ዝምድና ይመሠረታል፤ አይሁዳዊ ያልነበረውም ሰው በቃል ኪዳኑ ሥልጣን ሥር የሆነ የአይሁድ ሃይማኖት ተከታይ ይሆናል።

ስለዚህ ለክርስቲያኖች ራስን ከመወሰን በመቀጠል የሚከናወነው ጥምቀት ከይሖዋ አምላክ፣ ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተቀራረበ ዝምድና ይመሠርትላቸዋል። አዲሱን ሃይማኖት የተቀበለው ሰው በአዲሱ የሕይወት ጎዳናው ትክክለኛውን ሥልጣናቸውን አምኖ ይቀበላል። ለተጠቀሱት ለሦስቱም ይህ አባባል እንዴት እውነት እንደሆነ እንመልከት።

የአምላክን ሥልጣን አምነን በመቀበል ወደ እርሱ ቀርበን ከእርሱ ጋር ዝምድና እንመሠርታለን። (ዕብራውያን 12:9፤ ያዕቆብ 4:7, 8) በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት ዋጋ ተገዝተን እንደ ባሪያዎቹ በመሆን የአምላክ ንብረቶች እንሆናለን። (1 ቆሮንቶስ 3:23፤ 6:20) ሐዋርያው ጳውሎስ ለመጀመሪያ መቶ ዘመን ክርስቲያኖች የክርስቶስ ንብረት እንጂ የማንም ሌላ ሰው፣ እውነትንም ያመጣላቸው ሰው ንብረት እንዳልሆኑ ገልጾላቸዋል። (1 ቆሮንቶስ 1:12, 13፤ 7:23፤ ከማቴዎስ 16:24 ጋር አወዳድር።) በወልድ ስም መጠመቅ የሚያመለክተው ኢየሱስ “መንገድ፣ እውነትና ሕይወት” የመሆኑን ሐቅ አምኖ መቀበልን ነው።—ዮሐንስ 14:6

መንፈስ ቅዱስም ከይሖዋና ከኢየሱስ ጋር ላለን ትክክለኛ ዝምድና አስፈላጊ ነገር ነው። በመንፈስ ቅዱስ ስም መጠመቅ አምላክ ከኛ ጋር ባለው ግንኙነት የመንፈስ ቅዱስን ሚና እንደተቀበልን ያሳያል። መንፈሱን ችላ አንለውም፤ ከእርሱ ተቃራኒ የሆነ ነገርም አናደርግም፤ በእኛ በኩል የሚሠራውን ሥራ ባለማገድ መመሪያውን ለመከተል በዓላማ እንጥራለን። (ኤፌሶን 4:30፤ 1 ተሰሎንቄ 5:19) የመንፈስ አካል አለመሆን በአጠቃቀሙ ወይም በትርጉሙ በኩል ምንም ችግር አይፈጥርም። በይሁዲነት ሃይማኖት ውስጥ ከነበረው “በቃል ኪዳኑ ስም” ከሚለው አጠቃቀም ምንም አይለይም።

ስለዚህ ራሳችንን በምንወስንበትና በምንጠመቅበት ጊዜ በአዲሱ ዝምድናችን ውስጥ ምን ነገሮች እንደሚጠቃለሉ በጥንቃቄና በጸሎት ማሰብ ያስፈልገናል። የኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌና ቤዛ በመስጠቱ ለተገለጸው እንዲሁም ሁሉንም የአምላክ አገልጋዮች በፍቅርና በዓለም አቀፍ አንድነት እየመራቸው ባለው በቅዱስ መንፈሱ በኩል ለሚፈጸመው የአምላክ ፈቃድ መገዛትን ይጠይቃል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ