የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 12/1 ገጽ 30
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የኢየሱስ ትንሣኤ በእርግጥ ተፈጽሟል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ኢየሱስ ከሞት የተነሳው ምን ዓይነት አካል ይዞ ነው? ሥጋዊ ወይስ መንፈሳዊ?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ከጴንጤቆስጤ በፊት በርካቶች አዩት
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ‘ከልብ ለሚፈልጉት ወሮታ ከፋይ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 12/1 ገጽ 30

የአንባብያን ጥያቄዎች

ማቴዎስ 28:17 አንዳንድ ሐዋርያት ከሙታን የተነሳው ኢየሱስ ከተገለጠላቸው ከረጅም ጊዜም በኋላ መጠራጠራቸውን ቀጥለው ነበር ማለቱ ነውን?

“አሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት ግን ኢየሱስ ወዳዘዛቸው ተራራ ወደ ገሊላ ሄዱ፣ ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት የተጠራጠሩ ግን ነበሩ” በማለት ከሚነበበው ከማቴዎስ 28:16, 17 ከላይ እንደተገለጸው ብለን መደምደም አያስፈልገንም።

ኢየሱስ “ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሳ ዘንድ እንዲገባው” ደቀ መዛሙርቱ በቅድሚያ እንዲገነዘቡ ለመርዳት ጥሮ ነበር። (ማቴዎስ 16:21) ሆኖም መያዙና ሞት ተፈርዶበት መሰቀሉ ደቀ መዛሙርቱን ተስፋ አስቆርጦአቸውና ግራ አጋብቶአቸው ነበር። ትንሳኤው ሳይታሰብ የመጣ አስደሳች ነገር የሆነባቸው ይመስላል። ራሱን በሰው መልክ በገለጸ ጊዜ አንዳንዶቹ መጀመሪያ ላይ “ከደስታ የተነሳ ገና አላመኑም ነበር።” (ሉቃስ 24:36-41) ይሁንና ከትንሳኤው በኋላ በተደጋጋሚ መታየቱ የቅርብ ተከታዮቹ የትንሳኤውን እውንነት እንዲቀበሉ ረድቷቸዋል፤ ሐዋርያው ቶማስም እንኳን ሳይቀር ኢየሱስ ከሞት እንደተነሳ አምኗል።—ዮሐንስ 20:24-29

ከዚያ በኋላ አሥራ አንዱ ሐዋርያት “ወደ ገሊላ ሄዱ።” (ማቴዎስ 28:16፤ ዮሐንስ 21:1) እዚያ ሳሉም ኢየሱስ “ከአምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ።” (1 ቆሮንቶስ 15:6) በዚህ ቦታ ላይ ነው ማቴዎስ 28:17 “የተጠራጠሩ ግን ነበሩ” በማለት የሚጠቅሰው። ስለዚህ የተጠራጠሩት ከ500 ተከታዮቹ መካከል ሊሆኑ ይችላሉ።

በዚህ ጉዳይ ላይ የመጀመሪያው የመጠበቂያ ግንብ ፕሬዚዳንት ሲ ቲ ራስል የሰጠውን ትኩረት የሚስብ አስተያየት ተመልከቱ፦

“የተጠራጠሩት ከአሥራ አንዱ ሐዋርያት መካከል እንደነበሩ ብንገምት ምክንያታዊ አይደለንም፣ ምክንያቱም እነርሱ ሙሉ በሙሉ ረክተው፣ በአጥጋቢ ሁኔታ አምነውና ይህንኑም ቀደም ሲል ገልጸው ነበር። የተጠራጠሩት ከትንሳኤው ወዲህ ከኢየሱስ ጋር ተገናኝተው የማያውቁና ከእነርሱም አንዳንዶቹ ኢየሱስ ከትንሳኤው በኋላ ካነጋገራቸው ሐዋርያትና የቅርብ ወዳጆች ይልቅ በእምነት ደካሞች ነበሩ ብለን በምክንያታዊነት ልናስብ ከምንችላቸው ‘ከአምስት መቶ ወንድሞች’ መካከል መሆን ያለባቸው ይመስለናል። ‘አንዳንዶች ተጠራጠሩ’ የሚለው አባባል የወንጌላዊውን ሐቀኛነት የሚያሳይ ማስረጃ ነው። የጌታ ተከታዮች ተታላዮች እንዳልሆኑ፣ ከዚህ ይልቅ የቀረበላቸውን ማስረጃ አበጥረው ወደመመዘኑ የሚያዘነብሉ እንደነበሩና በውጤቱም በኢየሱስ ያመኑት ያሳዩት ቅንዓት፣ ብርታትና ራስን የመሰዋት መንፈስ የኢየሱስን ትንሳኤ በተመለከተ የያዙት ጽኑ እምነት በሙሉ ልብና በቅንነት ላይ የተመሠረተ ለመሆኑ ብዙ ማስረጃ ይሰጠናል፤ እኛም ሆንን እነርሱ በኢየሱስ ለማመን መሠረታችን እንደሆነ የምንገነዘበውም ይህንኑ ትንሳኤውን የሚመለከት ማስረጃ ነው። ክርስቶስ ያልተነሳ ከሆነ እምነታችን ከንቱ ነው እኛም ገና በኃጢአታችን አለን።—1 ቆሮንቶስ 15:17”—የጽዮን መጠበቂያ ግንብና የክርስቶስ መገኘት አብሣሪ ግንቦት 1, 1901, ገጽ 152

ማቴዎስ ይህን ሐሳብ የጠቀሰበት መንገድ ለመጽሐፍ ቅዱስ ተአማኒነትና ሐቀኛነት እግረ መንገዱን ማስረጃ እንደሚሰጠን ልንመለከት እንችላለን። አንድ ሰው አንድን ታሪክ ቢፈጥር የፈጠራ ታሪኩን የሚታመን እንዲመስል የሚያደርጉለትን ዝርዝሮች ወደማቅረቡ ያዘነብላል፤ አንዳንድ ዝርዝሮችን መተው በፈጠረው ታሪክ ላይ ጥርጣሬ የሚጥልበት ሊመስለው ይችላል። ማቴዎስስ እንዴት ነው?

“የተጠራጠሩ ግን ነበሩ” በማለት ለጻፈው አስተያየት ዝርዝር ማብራሪያ መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ አልተሰማውም። በማርቆስ፣ በሉቃስና በዮሐንስ የተጻፉት ወንጌሎች ስለዚህ ጉዳይ ምንም የጠቀሱት ነገር የለም። ስለዚህ የማቴዎስ አስተያየት ብቻውን ሲወሰድ እርሱን ራሱን ጨምሮ 11ዱን ሐዋርያት የሚያመለክት ሊመስል ይችላል። ሆኖም ማቴዎስ ያለምንም ማብራሪያ አጭር አስተያየት ብቻ ሰጥቷል። ወደ 14 ከሚጠጉ ዓመታት በኋላ ሐዋርያው ጳውሎስ የመጀመሪያውን የቆሮንቶስ መልእክት ጻፈ። በ1 ቆሮንቶስ 15:6 ላይ በሰጠው ዝርዝር መግለጫ መሠረት የተጠራጠሩት ሐዋርያት ሳይሆኑ ኢየሱስ ከዚያ በፊት ያልተገለጠላቸው በገሊላ ያገኛቸው ደቀ መዛሙርት ነበሩ ወደሚል የቀረበ መደምደሚያ ልንደርስ እንችላለን። ስለዚህ “የተጠራጠሩ ግን ነበሩ” የሚለው የማቴዎስ አስተያየት የእውነትነት ማስረጃ ያለው ነው፤ በእርግጥም እያንዳንዷን ጥቃቅን ዝርዝር ለመግለጽ ሳይሞክር እውነተኛ ትረካ ያቀረበ የሐቀኛ ጸሐፊን ጠባይ የሚያንጸባርቅ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ