የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 1/15 ገጽ 3-4
  • ወደ ሰማይ ትነጠቃለህን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ወደ ሰማይ ትነጠቃለህን?
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ስለ መነጠቅ የሚነሱ የተለያዩ አመለካከቶች
  • በአካል መነጠቅ
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
  • ‘ክርስቶስን ለመቀበል መነጠቅ’ — እንዴት?
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ‘መዳናችሁ እየቀረበ ነው’!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • የክርስቶስ መመለስ
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
ለተጨማሪ መረጃ
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 1/15 ገጽ 3-4

ወደ ሰማይ ትነጠቃለህን?

ብዙ ሰዎች ሲሞቱ ወደ ሰማይ እንደሚሄዱ ያምናሉ። ይሁን እንጂ አንዳንዶች ወደ ሰማይ እንደሚነጠቁ ያስባሉ። አንተም ተስፋ የምታደርገው ይህን ነውን?

መነጠቅ ማለት “በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የደረሱበት ሳይታወቅ በድንገት ይሰወራሉ ማለት ነው” በማለት አንድ የፕሮቴስታንት ወንጌላዊ ተናግሯል። ኤቫንጄሊካል ዲክሽኔሪ ኦፍ ቲኦሎጂ እንደሚለው ደግሞ “መነጠቅ ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ከክርስቶስ ጋር የምትተባበርበትን ጊዜ ያመለክታል” ይላል።[1]

አንዳንዶች ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለመገናኘት ሲሉ ወዳጆቻውንና ቤተ ሰቦቻቸውን ጥለው መሄድን ሲያስቡ የሚረብሽ ሆኖ አግኝተውታል። ቢሆንም ብዙዎች መነጠቅ የግድ መሆን እንደሚገባው ያምናሉ። መነጠቅ ይኖራልን? ከኖረስ መቼ?

ስለ መነጠቅ የሚነሱ የተለያዩ አመለካከቶች

በተስፋ የሚጠበቀው የክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛት ከመጀመሩ በፊት “ታላቅ መከራ” የሚባል ጊዜ እንደሚኖር መጽሐፍ ቅዱስ ያመለክታል። ኢየሱስ:- “በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ ከእንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና” ብሎአል። (ማቴዎስ 24:21፤ ራእይ 20:⁠6) አንዳንዶች መነጠቅ የሚሆነው ከታላቁ መከራ በፊት ነው ይላሉ። ሌሎች ደግሞ በታላቁ መከራ ጊዜ የሚሆን ነው ይላሉ። አሁንም ሌሎች ደግሞ መነጠቅ የሚሆነው ይህ ተወዳዳሪ የሌለው የጭንቀት ጊዜ ካለፈ በኋላ ነው ብለው ያስባሉ።[3]

መነጠቅ የሚሆነው ከታላቁ መከራ በኋላ ነው የሚለው አመለካከት እስከ 19ኛው መቶ ዘመን መባቻ ድረስ በጣም ተስፋፍቶ ነበር። ከዚያ በኋላ ግን በእንግሊዝ አገር የአየርላንድ ቤተ ክርስቲያን ቄስ በነበረ ጆን ኔልሰን ዳርቢ በሚባል ሰው የሚመራ አንድ እንቅስቃሴ ተጀመረ። እርሱ እና እንደ እርሱ ያለ አስተሳሰብ የነበራቸው የአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን አባሎች ወንደማማቾች ተብለው መጠራት ጀመሩ። ይህ ሰው በፓሊመስ ከሚገኘው ቤተ ክርስቲያኑ ተነስቶ በስዊዘርላንድ እና በተለያዩ የአውሮፓ አገሮች እየተዘዋወረ ሰብኳል። የክርስቶስ መመለስ በሁለት ደረጃዎች የሚከናወን እንደሆነ ያስተምር ነበር። የክርስቶስ መመለስ የሚከናወነው ለሰባት ዓመታት የሚቆየው የመከራ ጊዜ ምድርን ከማውደሙ በፊት “ቅዱሳን” በምስጢር በሚነጠቁበት ወይም በሚወሰዱበት ጊዜ ይጀምራል በማለት ይናገር ነበር። ከዚያ በኋላ ክርስቶስ በእነዚህ “ቅዱሳን” ታጅቦ በሚታይ ሁኔታ ይመጣል፤ አብረውም ምድርን ለሺህ ዓመት ይገዛሉ የሚል አቋም ያዘ። [8]

ዳርቢ ከዓለም መለየት በጣም አስፈላጊ መሆኑን አበክሮ ይገልጽ ነበር። በዚህ ምክንያት የሱን አስተያየት የሚከተሉ ሰዎች ራሳቸውን የለዩ ወንድሞች ተብለው ይጠሩ ነበር። ቢ ደብሊው ኒውተን የተባለ ሰው ደግሞ አንድ የተለየ ኑፋቄ ይመራ ነበር። የሱ ኑፋቄ በመነጠቅ የሚያምን ቢሆንም መነጠቁ ከመከራው በፊት እንደማይሆን የሚያስተምር ነበር። መነጠቁ የሚሆነው ከመከራው በኋላ ነው ብሎ ይከራከር የነበረ አሌክሳንደር ሪስ የተባለ ሰው ደግሞ “ምስጢራዊ መነጠቅ የሚለው ንድፈ ሃሳብ የክርስቶስን የመምጣት ተስፋ የሚያጨልም ነው” ይል ነበር።

መነጠቅ የሚሆነው ከመከራው በፊት ነው ብለው የሚያምኑ ቡድኖች ይህ የአመለካከት መለያየት በክርስቶስ “መመለስ ረገድ [ያላቸውን] ተስፋ ሊያበላሽባቸው የሚችል ከባድ ጉዳይ እንደሆነ ያምኑ ነበር። ሌሎች ደግሞ “ከፊል መነጠቅ” ይኖራል ብለው ያምኑ ነበር።” እነዚህ ቡድኖች ለክርስቶስ በጣም ታማኝ የሆኑት በመጀመሪያ ሲነጠቁ ይበልጥ ዓለማውያን የሆኑት ደግሞ በኋላ እንደሚነጠቁ ያምናሉ።[14]

ብዙ የወንጌላውያን ቡድኖች ታማኝ ክርስቲያኖች የሚነጠቁበት ጊዜ እንደቀረበ ሲሰብኩ ቆይተዋል። ይሁን እንጂ የተለያዩ አስተያየቶች በመኖራቸው ምክንያት በብሪታኒያ ኤሊም በጰንጠቆስጤ ቤተ ክርስቲያን የሚታተም አንድ ንዑስ መጽሐፍ እንዲህ ብሏል:- “ጌታ ኢየሱስ በሚመለስበት ጊዜ ስለሚከናወኑት ሁኔታዎች ሰፋ ያለ የተለያየ እምነት ቢኖረንም እያንዳንዱ ግለሰብ በመሰለው እምነት ትንቢቶችን የመተርጎም ነፃነት አለው። ብዙዎች ቀኖናዊ ያልሆነ አቋም በመያዝ ትንቢታዊው ፕሮግራም ራሱ ሲፈጸም ለማየት በትዕግሥት ይጠባበቃሉ።”[15]

የማንኛውም እምነት እውነተኛነት የሚመዘነው በአምላክ መንፈስ አንቀሳቃሽነት በተጻፈው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ የአቋም ደረጃዎች መሠረት ሊሆን ይገባዋል። (2 ጢሞቴዎስ 1:⁠13፤ 3:​16, 17) ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መነጠቅ ምን ይናገራል?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ