የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 2/1 ገጽ 30
  • ትንባሆና ቀሳውስት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትንባሆና ቀሳውስት
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ትንባሆ ማጨስ ከአምላክ ጋር ያለኝን ግንኙነት ይነካብኛል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ትንባሆና ሳንሱር
    ንቁ!—1994
  • የትምባሆ ጠበቆች በሞቃት አየር የተሞሉ ባሉኖቻቸውን መተኮስ ጀምረዋል
    ንቁ!—1999
  • ማጨስ ኃጢአት ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ለተጨማሪ መረጃ
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 2/1 ገጽ 30

ትንባሆና ቀሳውስት

ከ115 ዓመታት በፊት ጆን ካወን የተባሉ የሕክምና ዶክተር ትንባሆ ማጨስ ከንጽሕና፣ ከጥራትና ከጥሩ ጤንነት አንፃር በሚል ርዕስ አንድ መጽሐፍ ደርሰው ነበር። በቅርብ ዓመታት ስለ ትንባሆ ጎጂ ውጤት ሊታወቅ ከተቻለው አንፃር ሲታይ ቀሳውስት በትንባሆ መጠቀማቸውን አስመልክቶ ዶክተሩ የሰጡት አስተያየት አርቆ አስተዋይነታቸውን የሚያመለክትና በአሁኑ ጊዜ አምላክን ለማገልገል ለሚፈልግ ለማንኛውም ሰው አስፈላጊ ነው። ዶክተር ካወን በትንባሆ መጠቀም የሚያስከትለውን ሥነ ምግባራዊ ውጤት አስመልክተው በምዕራፍ 4 ላይ የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተው ነበር:-

“በትንባሆ መጠቀም በግልጽ እንደታየው ለሰውነት መጥፎ ከሆነ ከሥነ ምግባር አንጻርም መጥፎ መሆኑ ግድ ነው፤ ምክንያቱም ‘ሰውነትን የሚያበላሽ ወይም የሚያስቆጣ ነገር እግረ መንገዱን የነርቭ አሠራር ሥርዓትንና በዚያውም አንጎልን፣ ብሎም አእምሮን የሚያበላሽ’ መሆኑ የሰው አካል ሕግ ነውና። የሰው አእምሮ ይኸውም አስተሳሰቡ፣ ንግግሩና ተግባሩ ሁሉ አካላዊ ተፈጥሮውን በሚጠቀምበት ወይም በሚያጎሳቁልበት መንገድ ይነካል። ትንባሆ በስሙ በራሱና ከአርሱ ጋር አብረው በሚመጡት ነገሮች ምክንያት ቆሻሻ ነው፤ ታዲያ አንድ ሰው በትንባሆ የሚጠቀም ከሆነ የሚያመጣውን ጉዳት እንኳ ሳናነሳ ንጹሕ፣ ጥሩና ተገቢ የሆኑ ሥነ ምግባራዊ ስሜቶችና ተግባሮች እንዴት አድርገው በአእምሮ ውስጥ ሊመነጩ ይችላሉ? በዓይነ ህሊናችን እንየውና ያውም እንዲህ ዓይነት ነገር ሊታሰበን የሚችል ከሆነ ክርስቶስ በምድር ላይ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ሕይወት ሲኖር ሳለ ንጽሕናን፣ ጥራትን፣ ፍቅርንና በጎ አድራጎትን ሲያስተምርና ሲሰብክ ትንባሆ ሲያጨስ፣ በአፍንጫው ሲስብና ሲያላምጥ እስቲ ይታየን። እንዲህ ያደርግ ነበር ብሎ ማሰቡ ራሱ የተቀደሱ ነገሮችን የሚያራክስ ርኩስ ተግባር አይደለምን? ሆኖም ቄሶች የኢየሱስን ሕግና ትምህርቶች የሚከተሉ፣ የሚሰብኩና የሚያብራሩ ሰዎች ሆነው እያለ በረከሰና መርዛማ በሆነ አረም የገዛ ሰውነታቸውንና የገዛ ነፍሳቸውን ያበላሻሉ። እንዲህ ዓይነቶቹ ሰዎች ወይም ተከታዮቻቸው የክርስቶስን የሚመስል ሕይወት ይኸውም ከፍ ያለ ሥነ ምግባራዊ ሕይወት ሊመሩ ይችላሉን? የሚችሉ አይመስለኝም።

“ከቻላችሁ አንድን ሆዳም በላተኛ፣ የመጠጥ ሱሰኛ ወይም ትንባሆ አጫሽ የሆነ ሰው ከልብ ቅድስና ጋር አያይዛችሁ አስቡ። እነዚህን ነገሮች ከልብ ቅድስና ጋር አያይዞ ማሰብ ራሱ ተገቢ ያልሆነ፣ የሚያንገሸግሽና የሚቀፍ ነገር ነው። በትንባሆ በመጠቀም የሰውነት ፍላጎቶችና ውጪያዊ የሆኑት ስሜቶች እንደሚበላሹ ሁሉ ውስጣዊው ሰውና ሥነ ምግባራዊው ባሕርይም ይረክሳል። ንጹሑ መንፈስ በቆሻሻ ቤት አይኖርም፣ ሊኖርም አይችልም። በሥጋዊና በመንፈሳዊ ነገሮች መካከል ተፈጥሮአዊ የሆነ ተመሳሳይነት አለ። ስለዚህ የአንዱ [የሥጋዊው ነገር] ባሕርይ የሌላውን [የመንፈሳዊውን ነገር] ጠባይ ያመለክታል። ሃይማኖተኛ ነኝ እያሉ የትንባሆ ባሪያ መሆን የማይጣጣሙ ነገሮች ናቸው። . . . በፍጹም ቅንነትና ሐቀኝነት በትንባሆ መጠቀም ጎጂ ልማድና ከሥነ ምግባር አንፃርም ስህተት መሆኑን አምኖ ይቀበል ይሆናል፤ ሆኖም በውስጡ አንድ ዓይነት ግፊት፣ በብልቶቹ ውስጥ ሰው ሠራሽ የሆነ ሕግ ልማዱን እንዲቀጥልበት የሚያነሳሳው የማይረካ ፍላጎት ሊኖረው ይችላል። ይህ አርቲፊሻል ሕግም የሰውየው የተፈጥሮ የማመዛዘን ችሎታና ህሊና አንድ ላይ ቢደመሩም ሊያሸንፉት የማይችሉት ኃይለኛ ሊሆን ይችላል። ታዲያ በትንባሆ መጠቀም በብልቶቻችን ውስጥ የተተከሉትን የአምላክ ሕጎች መጣስ መሆኑ ግልጽ አይደለምን? ከአምላክ ሕጎች ውስጥ አንዱን መጣስ ሕግ መተላለፍና ኃጢአት አይደለምን? አንድ ሰው የአምላክን ሕግ በመጣስ መኖርን ልማዱ አድርጎ ከያዘ ሌሎችን ሕጎች ወደመጣስ መሸጋገሩ የተለመደ ነገርና ቀላል አይሆንለትምን? በመጨረሻም አንድ ሰው ለሌሎች መሰል ሰዎች የገዛ ሕልውናውን ሕግ ባለማቋረጥ እየጣሰ መኖርን እንደሚደግፍ በአኗኗሩ የሚያሳያቸው ከሆነ የግብረ ገብነት አስተማሪ ሆኖ ሊቆጠር እንዴት ይችላል?”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ