የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 4/1 ገጽ 3-4
  • አጥምቁ! አጥምቁ! አጥምቁ! ግን ለምን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አጥምቁ! አጥምቁ! አጥምቁ! ግን ለምን?
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የጥምቀትህ ትርጉም
    እውነተኛው አንድ አምላክ ያስገኘው የአምልኮ አንድነት
  • መጠመቅ ለምን አስፈለገ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • ጥምቀት—ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ግብ!
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ጥምቀት
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
ለተጨማሪ መረጃ
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 4/1 ገጽ 3-4

አጥምቁ! አጥምቁ! አጥምቁ! ግን ለምን?

“በጥቂት ወራት ውስጥ ከአሥር ሺህ በላይ የሚሆኑ ወንዶችን፣ ሴቶችንና ልጆችን አጥምቄአለሁ።” ኢየሱሳዊው ሚስዮናዊ ፍራንሲስ ዛቪየር በሕንድ አገር በትራቫንኮር መንግሥታዊ ግዛት ውስጥ ያከናወነውን ሥራ በተመለከተ ከላይ የተጠቀሰውን ጽፏል። “ከመንደር ወደ መንደር በመሄድ ክርስቲያኖች አድርጌአቸዋለሁ። በሄድኩበት ሁሉ በአገሩ ቋንቋ የተጻፉትን ጸሎቶቻችንንና ትዕዛዞቻችንን የያዘ አንድ ቅጂ ትቼላቸዋለሁ።”

ፍራንሲስ ዛቪየር በጻፋቸው ደብዳቤዎች በከፍተኛ ሁኔታ ስሜታቸው የተመሰጠው የፖርቱጋሉ ንጉሥ ጆን ደብዳቤዎቹ በግዛታቸው በሙሉ በእያንዳንዱ የስብከት መድረክ ላይ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲነበቡ አዘዙ። ከላይ የተጠቀሰው በጥር 1545 የተጻፈው ደብዳቤ የመታተም ፈቃድም ጭምር አገኘ። ውጤቱ ምን ነበር? ዘ ጀስዊትስ — ሂስትሪ ኤንድ ሌጀንድ ኦቭ ዘ ሶሳይቲ ኦቭ ጂሰስ በተባለው መጽሐፋቸው ላይ ማንፍሬድ ባርትል እንዲህ በማለት ጽፈዋል:- “ወዲያው በአውሮፓ ውስጥ ከነበሩት ተማሪዎች ብዙዎቹ ‘ተንበርክከው በስሜት እያነቡ’ ወደ ሕንድ ሄደው የአረመኔያዊ እምነት ተከታዮችን ወደ ክርስትና ለመለወጥ እንደሚፈልጉ በጩኸት ይገልጹ ጀመር።” አክለውም እንዲህ አሉ:- “ጠበል በሚረጩ ጥቂት ቄሶችና አንድ ቦርሳ በሚሞሉ ትራክቶች ብቻ የአንድን አገር ሕዝብ በጠቅላላ ወደ ክርስትና መለወጥ አይቻልም የሚለው ሐሳብ በወቅቱ ለነበሩ ብዙ ሰዎች የታያቸው አይመስልም።”

ሰዎችን በጅምላ ወደ ክርስትና ለመለወጥ በተደረጉ እንዲህ ባሉት ድርጊቶች የተከናወነው ነገር በእርግጥ ምን ነበር? ኢየሱሳዊው ኒኮላስ ላንቺሎቶ ሁኔታውን ሳይሸሽጉ እንደሚከተለው በማለት ወደ ሮማ ሪፖርት አድርገዋል:- “ከተጠመቁት ውስጥ አብዛኞቹ አንድ የተሰወረ ዓላማ ነበራቸው። የአረብ ባሮችና ሂንዱዎች ነጻነታቸውን ለማግኘት ወይም ጨቋኝ ከሆነ ጌታ ከለላ ለማግኘት አለበለዚያም አዲስ ልብስ ወይም ጥምጥም ለማግኘት ተስፋ በማድረግ ይጠመቁ ነበር። ብዙዎች የተጠመቁት ከአንድ ዓይነት ቅጣት ለማምለጥ ሲሉ ነው። . . . በትምህርቶቻችን አማካኝነት መዳን እንደሚገኝ አምነው የተጠመቁ ሰዎች ሁሉ እንደ እብዶች ይቆጠሩ ነበር። ብዙዎች ከተጠመቁ በኋላ ምንም ያህል ሳይቆዩ ክርስትናን በመካድ ወደ በፊቶቹ አረመኔያዊ ልማዶቻቸው ተመልሰዋል።”

በዚያ ዘመን የነበሩት ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወሩ ጥናት የሚያደርጉ አውሮፓውያንም አረመኔዎችን ወደ ክርስትና ለመለወጥና ለማጥመቅ ይፈልጉ ነበር። ክርስቶፈር ኮሎምበስ ለመጀመሪያ ጊዜ በካሪቢያን ያገኛቸውን “ሕንዶች” አጥምቋቸዋል ይባላል። ዘ ኦክስፎርድ ኢለስትሬትድ ሂስትሪ ኦቭ ክርስቲያኒቲ የተባለው መጽሐፍ “የስፓኝ ንጉሠ ነገሥት ፖሊሲ የአገሩን ተወላጆች ወደ ክርስትና መቀየርን ተቀዳሚ ዓላማው አድርጎታል” ይላል። “በአሥራ ስድስተኛው መቶ ዘመን መጨረሻ ላይ በስፓኝ ግዛት የሚገኙት 7,000,000 የሚሆኑ ሕንዶች ቢያንስ በስም ክርስቲያኖች ነበሩ። ወደ ክርስትና የተለወጡ ሰዎች ቁጥር ሪፖርት በተደረገበት ቦታ ሁሉ ምንም ዓይነት ጠለቅ ያለ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት እንዳልተሰጠ ከሁኔታዎቹ ለመረዳት ይቻላል። (የንጉሠ ነገሥት ቻርለስ አምስተኛ ዘመድ የሆኑት ሚስዮናዊው ፔትሮ ዴ ጋንቴ እንደተናገሩት ከአንድ ረዳታቸው ጋር ብቻ በመሆን በአንድ ቀን 14,000 ሰዎችን አጥምቀዋል።)” ጥልቀት በሌለው ሁኔታ ሰዎችን ወደ ክርስትና ለመለወጥ የሚደረጉ እንደነዚህ ያሉ ድርጊቶች አብዛኛውን ጊዜ የአገሩን ተወላጆች በኃይል፣ በጭካኔና በጭቆና በማስገደድ የሚከናወኑ እርምጃዎች ነበሩ።

ለጥምቀት የተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት አዲስ ምድር ለማጥናት የሚጓዙ ሰዎችና ሚስዮናውያን በነገሩ በርትተው እንዲገፉበት አድርጓቸዋል። በ1439 ጳጳስ ዮጂንየስ አራተኛ በፍሎሬንስ ጉባኤ ላይ እንዲህ የሚል ድንጋጌ አውጥተው ነበር:- “ቅዱስ ጥምቀት ከቅዱሳን ነገሮች ውስጥ ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛል፤ ምክንያቱም ጥምቀት የመንፈሳዊ ሕይወት በር ነው። በተጨማሪም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋር የተሳሰረ ነገር ነው። በመጀመሪያው ሰው በኩል ሞት ለሁሉም የደረሰ በመሆኑ ከውኃና ከቅዱስ መንፈስ ዳግመኛ ካልተወለድን በቀር ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ ልንገባ አንችልም።”

ነገር ግን ተቀባይነት ያለው ጥምቀት የማንኛቸው ነው የሚለው ጥያቄ አወዛጋቢ ሆነ። ዘ ኢንሳይክሎፔድያ ኦቭ ሪሊጅን እንዲህ በማለት ይጠቅሳል:- “ጥምቀት የቤተ ክርስቲያኑ ማኅበረሰብ አባል ለመሆን የሚያስፈልግ መሠረታዊ ሥርዓት በመሆኑ በርካታ ተቀናቃኝ አብያተ ክርስቲያናት ለማጥመቅ መብት ያለኝ እኔ ነኝ በማለት ወዲያው ፍትጊያ ጀመሩ። እነዚህም አብያተ ክርስቲያናት እያንዳንዳቸው የየራሳቸው ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊ እንደሆነ በመግለጽ ሌሎችን ከሐድያን ወይም መናፍቃን እያሉ ይጠሩ ነበር። ይህም በመሆኑ የጥምቀት ስነ ሥርዓቶችን በሚፈልጉት መንገድ አሻሽሎ ማካሄድ በተለያዩ የእምነት ክፍሎች ዘንድ የማይቀር ነገር ሆነ።”

ይሁን እንጂ የማጥመቅ ልማድ ከክርስትና እምነት በፊት የነበረ ነገር ነው። በባቢሎንያና በጥንቷ ግብጽ ውስጥ ይሠራበት ነበር። በግብጽ ቀዝቃዛው የአባይ ውኃ ኃይልን እንደሚጨምርና ዘላለማዊነት እንደሚያላብስ ተደርጎ ይታሰብ ነበር። ግሪኮችም ጥምቀት ሃይማኖቱን መከታተል የጀመረውን ሰው ዳግም ልደት እንደሚያስገኝለት ወይም ያለመሞትን ባሕርይ እንደሚያላብሰው ያምኑ ነበር። በኩምራን የነበረው የአይሁድ እምነት ኑፋቄ ተከታዮች ለመጀመሪያ ጊዜ የማኅበራቸው አባል ለመሆን የሚፈልገውን ሰው ያጠምቁ ነበር። ወደ ይሁዲነት የተለወጡ አሕዛብ መገረዝና ከሰባት ቀን በኋላም በምስክሮች ፊት ሙሉ በሙሉ ውኃ ውስጥ በመጥለቅ መጠመቅ ይፈለግባቸው ነበር።

ጥምቀት በዘመናት ሁሉ ትልቅ ቦታ ይሰጠው እንደነበር ግልጽ ነው። ዛሬስ ሁኔታው እንዴት ነው? በዘመናችን ጥምቀት አስፈላጊ ነውን? ከሆነስ ለምን? በእርግጥ መጠመቅ ይኖርብሃልን?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ