የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 7/15 ገጽ 32
  • “ከሰማይ ምልክት”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ከሰማይ ምልክት”
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 7/15 ገጽ 32

“ከሰማይ ምልክት”

አንድ የቆየ የእንግሊዝኛ ግጥም እንዲህ ይላል:- “ሰማዩ ሲቀላ በማታ ለመርከበኞች ደስታ፤ ሰማዩ ሲቀላ በጠዋት ለመርከበኞች ፍርሃት።” ዛሬ የአየርን ሁኔታ ለመተንበይ በሳተላይቶች፣ በኮምፒውተር የተጠናከሩ ስለ አየር የሙቀት መጠን የተደረጉ ጥናቶች፣ ዶፕለር የተባሉ ራዳሮች እና ሌሎችም ሳይንሳዊ ዘዴዎች ተግባራዊ ሆነዋል። ትንበያዎች ብዙውን ጊዜ ከላይ ከተጠቀሰው ግጥም ጋር ይስማማሉ።

የኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖታዊ ጠላቶች “ከሰማይ ምልክት” እንዲሰ ጣቸው ማለትም እንግዳ የሆነ ነገር በማሳየት መሲሕ መሆኑን እንዲያ ረጋግጥላቸው ፈልገው ነበር። “እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው:- በመሸ ጊዜ:- ሰማዩ ቀልቶአልና ብራ ይሆናል ትላላችሁ፤ ማለዳም:- ሰማዩ ደምኖ ቀልቶአልና ዛሬ ይዘንባል ትላላችሁ። የሰማዩን ፊትማ መለየት ታውቃላችሁ፣ የዘመኑንስ ምልክት መለየት አትችሉምን? ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፣ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።” — ማቴዎስ 16:​1–4

የኢየሱስ ጠላቶች የአየሩን ሁኔታ መተንበይ ችለው ነበር። መንፈሳዊ ነገሮችን ግን መረዳት አልቻሉም። ለምሳሌ ስለ “ዮናስ ምልክት” ምን ማለት ይቻላል? የአምላክ ነቢይ የነበረው ዮናስ ለሦስት ቀን ያህል በትልቅ ዓሣ ሆድ ውስጥ ከቆየ በኋላ በነነዌ በመስበክ ለዚህች ለአሦር ዋና ከተማ ምልክት ሆኗል። ክርስቶስ ሦስት ቀን በመቃብር ቆይቶ ሲነሣ በኢየሱስ ዘመን የነበረው ትውልድ “የዮናስን ምልክት” አግኝቷል። ደቀ መዛሙርቱ ያንን የተፈጸመውን ነገር ማስረጃ ስላወጁ ኢየሱስ ለዚያ ትውልድ ምልክት ሆኖ ነበር። — ማቴዎስ 12:​39–41

በሌላ አጋጣሚ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ወደፊት በመንግሥቱ ሥልጣን ‘የሚገኝበትን’ “ምልክት” ጠይቀውት ነበር። ሲመልስላቸውም የተለያዩ ገጽታዎች ያሉትን ምልክት ሰጣቸው። ይህም ተወዳዳሪ የሌላቸው ጦርነቶች፣ ታላላቅ የምድር መናወጦች፣ የምግብ እጥረቶችና ስለተቋቋመችው የአምላክ ሰማያዊ መንግሥት የሚደረገውን ምድር አቀፍ ስብከት ይጨምራል። — ማቴዎስ 24:​3–14

ኢየሱስ የማይታይ ሰማያዊ ንጉሥ በመሆን የሚገኝበትን ጊዜ ምልክቶች ታውቃቸዋለህን? የምልክቱ ገጽታዎች በዚህ ትውልድ ላይ እየተፈጸሙ ናቸው። (ማቴዎስ 24:​34) ስለ ወደፊቱስ ጊዜ? መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው የነገሮች ሥርዓት መጨረሻ እንደቀረበ ብቻ ሳይሆን አምላክ ቃል የገባለት አዲስ ቀን ለሰው ዘር ግልጽ እና ብሩኅ ሆኖ በቅርቡ እንደሚመጣም ጭምር ነው። — 2 ጴጥሮስ 3:​13

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ