የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 9/15 ገጽ 31
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘የመዳን ተስፋችሁ’ ብሩህ ሆኖ እንዲቀጥል አድርጉ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • ለኢየሱስ ፍቅር አጸፋውን ትመልሳለህን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ይህ የመዳን ቀን ነው!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • ክርስቲያኖችና የሰው ዘር ዓለም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
ለተጨማሪ መረጃ
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 9/15 ገጽ 31

የአንባብያን ጥያቄዎች

ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ 9:​3 ላይ:- “በሥጋ ዘመዶቼ ስለሆኑ ስለ ወንድሞቼ ከክርስቶስ ተለይቼ እኔ ራሴ የተረገምሁ እንድሆን እጸልይ ነበርና” ሲል ጽፏል። መሰል አይሁዳውያንን ለማዳን ሕይወቱን ለመሰዋት ፈቃደኛ ይሆን ነበር ማለቱ ነውን?

ኢየሱስ ከሁሉ የላቀውን የፍቅር ምሳሌ ትቶልናል። ለኃጢአተኛው የሰው ዘር ነፍሱን ወይም ሕይወቱን አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ ነበር። ለሕዝብ ባደረገው አገልግሎቱ ብዙዎቹ ከእርሱ ቤዛዊ መሥዋዕት እንዲጠቀሙ ሲል የአገሩ ሰዎች ለሆኑት አይሁዳውያን በጣም ደክሟል። (ማርቆስ 6:​30–34) መዳንን ለሚያስገኘው መልዕክት ያሳዩት ቸልተኝነትና ተቃውሞ ኢየሱስ ለአይሁዶች ያለውን ፍቅራዊ አሳቢነት አልቀነሰበትም። (ማቴዎስ 23:​37) ‘ፍለጋውንም እንድንከተል ምሳሌ ትቶልናል።’ — 1 ጴጥሮስ 2:⁠21

ፍጹማን ያልሆኑ ሰዎች የኢየሱስን የፍቅር ምሳሌ መከተል ይችላሉን? አዎን፤ የሐዋርያው ጳውሎስን ሁኔታ እንደ ማስረጃ አድርገን መጥቀስ እንችላለን። ለመሰል አይሁዳውያን በጣም ያስብላቸው ስለነበር ለእነርሱ ካለው ፍቅር የተነሳ ስለ እነርሱ “ከክርስቶስ ተለይቼ እኔ ራሴ የተረገምሁ እንድሆን” እፈልጋለሁ ሲል ተናግሯል።

ጳውሎስ እዚህ ቦታ ላይ ነጥቡን በግልጽ ለማስቀመጥ በአድናቆት ወይም በማጋነን አነጋገር ተጠቅሟል። ኢየሱስ ተመሳሳይ በሆነ የማጋነን አነጋገር ተጠቅሞ በማቴዎስ 5:​18 ላይ:- “እውነት እላችኋለሁ፣ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፣ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፣ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ” ብሏል። ኢየሱስ ሰማይና ምድር እንደማያልፉ ያውቅ ነበር። ጳውሎስም የተረገመ አይሆንም፤ ሁሉም አይሁዳውያንም ክርስትናን እንደማይቀበሉ የታወቀ ነው። ይሁን እንጂ ጳውሎስ ለመግለጽ የፈለገው ነጥብ አይሁዳውያን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በአምላክ በሚገኘው መዳን እንዲጠቀሙ ለመርዳት ማንኛውንም ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አልልም የሚል ነው። ሐዋርያው መሰል ክርስቲያኖችን:- “እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ” በማለት ሊያበረታታቸው መቻሉ ምንም አያስደንቅም። — 1 ቆሮንቶስ 11:1

ዛሬም ክርስቲያኖች ኢየሱስና ጳውሎስ ለማያምኑ ሰዎች የነበራቸው ዓይነት አሳቢነት ሊኖራቸው ይገባል። ምስክርነት በምንሰጥበት የአገልግሎት ክልላችን ውስጥ ያሉት ሰዎች ፍላጎት የሌላቸው መሆኑ ወይም ቀጥተኛ ተቃውሞ ማሳየታቸው ለጎረቤቶቻቸን ያለንን ፍቅርና የመዳንን መንገድ እንዲያውቁ ለመርዳት ያለንን ቅንዓት እንዲቀንስብን በፍጹም መፍቀድ አይገባንም። — ማቴዎስ 22:39

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ