የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 10/1 ገጽ 21
  • ረሃብ እንደሚሆን አስቀድሞ ተነግሮአል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ረሃብ እንደሚሆን አስቀድሞ ተነግሮአል
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “የባዕድ አገር ሰዎች” ይሖዋን ‘በደስታ እንዲያገለግሉት’ መርዳት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • የስደተኞች ቀውስ—በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ዩክሬንን ለቀው እየተሰደዱ ነው
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • መጽሐፍ ቅዱስ በዛሬው ጊዜ በዓለም ላይ ስላለው ረሃብ ምን ይላል?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 10/1 ገጽ 21

ረሃብ እንደሚሆን አስቀድሞ ተነግሮአል

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አሰቃቂው ረሃብ በዓለም የዜና ዘገባዎች ላይ መቅረቡ በጣም የተለመደ እየሆነ መጥቷል። በኢትዮጵያና በሌሎች ቦታዎች የማይረሳ ሠቆቃ ታይቷል። በ1992 የዓለም ትኩረት ድርቅና ጦርነት ላስከተለው አሠቃቂ የረሃብ ሰለባዎች ወደሆኑት ሶማሌያውያን ዘወር እንዲል ተደርጓል። ኢንተርናሽናል ሄራልድ ትሪቡን በመስከረም 1992 የሚከተለውን ዘግቧል:- “ምን ያህል ሶማሌያውያን እንደሞቱ በትክክል የሚያውቅ የለም፤ የቀይ መስቀል ማኅበር ግን ቁጥሩ በግምት ከ100,000 በላይ እንደሆነ ይናገራል። በየቀኑ በመቶዎች ምናልባትም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ይሞታሉ።”

ቁጥሮቹ የሚሠቃዩት ሰዎች ያሳለፏቸውን ሕመምና ሠቆቃ ሊገልጹት አይችሉም። ኤቬት ፓየርፓኦሊ የተባሉ የዓለም አቀፍ ስደተኞች ጉዳይ የአውሮፓ ወኪል ሬፊውጂስ በተባለው የተባበሩት መንግሥታት መጽሔት ላይ ሲጽፉ እንዲህ ብለዋል:- “በኒው ዮርክ ወይም በጄኔቫ የስደተኞቹ ጉዳይ ምንም አያሻማም፤ ቁጥሮች ይጠቀሳሉ፣ ቁጥሮቹን የሚከተሉት የዜሮዎች ብዛት ለመረዳት ያስቸግራሉ። ይሁን እንጂ ብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮች ርቃችሁ ማንም በማይቆጣጠራቸው የአገሮቻቸው ድንበር ብትሄዱ እንባ ይተናነቃችኋል እንዲሁም የሥቃያቸው ብዛት ያስለቅሳችኋል።”

ምንም እንኳ የቀይ መስቀል ማኅበር ሶማሊያን ለመርዳት ያደረገው ርብርብ እስከ አሁን ከተደረጉት ሁሉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊነት የተሞላው እርዳታ ነው ቢልም ብዙ ታዛቢዎች ግን አጠቃላይ ገጽታውን ሲመለከቱ በጣም ዘግይቶ የደረሰና በጣም ትንሽ እርዳታ ነው ይላሉ። ፓየርፓኦሊ “ለጋሽ አገሮች በመፈራረስ ላይ ያለችውን አፍሪካን መርዳት ታክቷቸው ቸልተኞች ሆነዋል። . . . ስለ ተበላሸ የነገሮች አያያዛቸው፣ ስለ ስግብግብ መሪዎቻቸውና የማያቋርጥ ስለሚመስለው የእርስ በርስ ግጭቶቻቸው አፍሪካውያንን ይወቅሳሉ።”

መጽሐፍ ቅዱስ “በልዩ ልዩ ስፍራ” ረሃብ የሚሆንበት ጊዜ እንደሚመጣ አስቀድሞ ተናግሯል። እንደ ጦርነት፣ የመሬት መንቀጥቀጥ እና ቸነፈር ካሉት ሌሎች ችግሮች ጋር ተዳምሮ ይህ ረሃብ የአምላክ መንግሥት መቅረቧን ያመለክታል። (ሉቃስ 21:​11, 31) በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ ጥሩ በሆነው በዚህ የአምላክ መንግሥት ግዛት ሥር ለሰው ዘሮች የተትረፈረፈ ምግብ እንደሚኖር ያሳያል። “በምድር ላይ ብዙ እህል ይኖራል፤ በተራሮች ራስ ላይም ይትረፈረፋል” በማለት መዝሙራዊው ጽፏል። — መዝሙር 72:​16 አዓት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ