የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w94 2/1 ገጽ 31
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የቃየን ሚስት ማን ነበረች?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የተለያየ አመለካከት ያዳበሩ ወንድማማቾች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት ማቅረብ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ቃየን ሚስቱን ያገኘው ከየት ነበር?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
w94 2/1 ገጽ 31

የአንባብያን ጥያቄዎች

አምላክ ቃየንን “ኃጢአት በደጅ ታደባለች፤ ፈቃድዋም ወደ አንተ ነው” በማለት አስጠንቅቆታል። ይህም የሚበላውን እንስሳ ለመያዝ የሚያደባን አውሬ የሚያመለክት አነጋገር ይመስላል። (ዘፍጥረት 4:7) ከጥፋት ውኃ በፊት እንስሳት የሚመገቡት ዕፀዋትን ብቻ ከነበረ እንዲህ ዓይነት አነጋገር የተጠቀመው ለምንድን ነው?

በሙሴ በተጻፉት መጻሕፍት ውስጥ በጊዜው ከተፈጸሙት ነገሮች ወይም ታሪካዊ ክስተቶች መካከል ያለቦታቸው የገቡ የሚመስሉ መግለጫዎች የሚገኙባቸው ብዙ ጥቅሶች እናገኛለን።

ለምሳሌ በዘፍጥረት 2:10–14 ላይ ያለው ታሪክ የዔደን አትክልት ቦታ ትገኝ ስለነበረበት ቦታ ጂኦግራፊያዊ መግለጫ ይሰጣል። ሙሴ አንደኛው ወንዝ “በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነው” ብሎ ጽፏል። ይሁን እንጂ አሦር የሚባለው አገር ስሙን ያገኘው ከጥፋት ውኃ በኋላ ከተወለደው አሦር የተባለ የሴም ልጅ ነው። (ዘፍጥረት 10:8–11, 22፤ ሕዝቅኤል 27:23፤ ሚክያስ 5:6) ሙሴ ትክክለኛ በሆነውና በመንፈስ አነሳሽነት በጻፈው ታሪክ ውስጥ ቦታውን “አሦር” ብሎ የጠራው አንባቢዎቹ ያውቁት የነበረውን አካባቢ ለማመልከት ፈልጎ እንደሆነ ማስረጃዎቹ ያሳያሉ።

ከመጀመሪያዎቹ የዘፍጥረት ምዕራፎች ውስጥ ሌላ ምሳሌ ተመልከት። አዳምና ሔዋን ኃጢአት ከሠሩና ከአትክልት ቦታው ከተባረሩ በኋላ ይሖዋ ወደዚያ ቦታ እንዳይመለሱ ከለከላቸው። እንዴት? ዘፍጥረት 3:24 እንዲህ ይላል፦ “አዳምንም አስወጣው፣ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ።” “የነበልባል ሰይፍ” የሚለውን ልብ በል። ለመጀመሪያ ጊዜ ሰይፍ የሠራው አምላክ ነውን?

የምናውቀውን ሰይፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የሠራው አፍቃሪው ፈጣሪያችን ነው ብለን መደምደም አይኖርብንም። አዳምና ሔዋን ከመላእክቶቹ ፊት አንድ የሚነድድ ነገር ሲገለባበጥ ተመልክተዋል። ያ የሚገለባበጥ ነገር ምንድን ነው? ሙሴ የዘፍጥረትን መጽሐፍ በጻፈበት ዘመን ሰይፍ በደንብ የታወቀና ለጦርነትም የሚያገለግል መሣሪያ ነበር። (ዘፍጥረት 31:26፤ 34:26፤ 48:22፤ ዘጸአት 5:21፤ 17:13) ስለዚህ “የነበልባል ሰይፍ” የሚለው የሙሴ አባባል አንባቢዎቹ በዔደን መግቢያ ላይ የነበረው ነገር መጠን ምን እንደነበረ በዓይነ ኅሊናቸው እንዲያዩ የሚያስችላቸው ነበር። በሙሴ ዘመን የነበረው ዕውቀት እንዲህ ያሉትን ነገሮች እንዲረዱ አስችሎ ነበር። ሙሴ የተጠቀመበትም አነጋገር ይሖዋ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲጨመር ስላደረገ ትክክለኛ አነጋገር መሆን አለበት።—2 ጢሞቴዎስ 3:16

ዘፍጥረት 4:7ስ? እዚህ ላይ አምላክ ቃየንን እንዲህ ሲል አስጠንቅቆታል፦ “መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚያበራ አይደለምን? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በደጅ ታደባለች፤ ፈቃድዋም ወደ አንተ ነው፣ አንተ ግን በእርስዋ ንገሥባት።” ቀደም ሲል እንደተገለጸው አነጋገሩ አንድ የተራበ አውሬ የሚበላውን እንስሳ በድንገት ዘልሎ ለመያዝ ሲያደባ የሚኖረውን ሁኔታ የሚገልጽ ይመስላል።

ዳሩ ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉት ማስረጃዎች አዳምና ሔዋን ከሁሉም እንስሶች ጋር ሰላም እንደነበራቸው ይጠቁማሉ። አንዳንድ እንስሳት ከሰዎች ጋር በጣም ተላምደው ነበር። እንዲያውም ከሰዎች ጋር በመኖራቸው ሳይጠቀሙ አይቀሩም። ሌሎቹ ደግሞ በተፈጥሯቸው ከሰዎች የራቀ መኖሪያ የሚፈልጉ አራዊት ነበሩ። (ዘፍጥረት 1:25, 30፤ 2:19) ሆኖም ከነዚህ እንስሶች አንዱም ቢሆን ሌሎችን እንስሳት ወይም ሰዎች የሚበላ እንደነበረ አያመለክትም። ገና ከመጀመሪያው አምላክ እንስሳትም ሆኑ ሰዎች ዕፀዋትን እንዲመገቡ ወስኖላቸው ነበር። (ዘፍጥረት 1:29, 30፤ 7:14–16) ዘፍጥረት 9:2–5 እንደሚያመለክተው ይህ ሁኔታ የተለወጠው ከጥፋት ውኃ በኋላ ነው።

ታዲያ በዘፍጥረት 4:7 ላይ የምናነበው አምላክ ለቃየን የሰጠው ማስጠንቀቂያስ? አንድ ክፉ አውሬ የሚበላውን እንስሳ ዘልሎ ለመያዝ እንደሚያደባ የሚያሳየውን አገላለጽ በሙሴ ዘመን የነበሩት አንባቢዎች በቀላሉ ሊረዱ ይችሉ ነበር፤ እኛም መረዳት እንችላለን። ስለዚህ እዚህም ላይ ሙሴ ከጥፋት ውኃው በኋላ በነበረው ዓለም የነበሩት አንባቢዎች በሚያውቁትና በለመዱት አነጋገር መጠቀሙ ሊሆን ይችላል። ቃየንም እንዲህ ዓይነት እንስሳ በፍጹም አይቶ የማያውቅ ቢሆንም ያለውን ኃጢአተኛ ዝንባሌ ከተራበና ስግብግብ ከሆነ አውሬ ጋር በማመሳሰል የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ ፍሬ ነገር ሳይረዳው አልቀረም።

ይበልጥ ልናተኩር የሚገባን አምላክ ለቃየን ማስጠንቀቂያ በመስጠቱ ባሳየው ደግነት፣ ምክርን በትሕትና መቀበል ባለው ጠቃሚነት፣ ምቀኝነት አንድን ሰው እንዴት በቀላሉ ሊያበላሸው እንደሚችል እንዲሁም አምላክ በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ያሰፈረልንን ሌሎች መለኰታዊ ማስጠንቀቂያዎች ምን ያህል አክብደን ልንመለከታቸው እንደሚገባን በሚገልጸው ክፍል ላይ መሆን አለበት።—ዘጸአት 18:20፤ መክብብ 12:12፤ ሕዝቅኤል 3:17–21፤ 1 ቆሮንቶስ 10:11፤ ዕብራውያን 12:11፤ ያዕቆብ 1:14, 15፤ ይሁዳ 7, 11

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ