የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w94 5/15 ገጽ 31
  • ከማላዊ የመጣ ምሥራች!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከማላዊ የመጣ ምሥራች!
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
w94 5/15 ገጽ 31

ከማላዊ የመጣ ምሥራች!

የፔንሲልቫንያው የመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስና ትራክት ማኅበር ኅዳር 15, 1993 በደቡብ ምሥራቅ አፍሪካ በምትገኘው አገር በማላዊ በይፋ ታውቆ ተመዝግቧል። ይህም የይሖዋ ምሥክሮች ሕጋዊ ዕውቅና እንዲያገኙና የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች በማላዊ ለሚገኙ ሰዎች በነጻነት እንዲሰብኩ ያስችላቸዋል።

ቀደም ሲል በ1948 በዚያች አገር የሚካሄደውን የይሖዋ ምሥክሮች ሥራ ለማደራጀት የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ቅርንጫፍ ቢሮ በማላዊ ተቋቁሞ ነበር። ጥር 8, 1957 የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር በዚያ አገር ለመጀመሪያ ጊዜ ዕውቅና አግኝቶ ተመዘገበ። በርከት ላሉ ዓመታት የይሖዋ ምሥክሮች ፈጣን እድገት በማድረግ ሲደሰቱ ቆዩ። ይሁን እንጂ በ1964 ጭካኔ የታከለበት ስደት ድንገት ተቀሰቀሰ። ለምን ይሆን?

የይሖዋ ምሥክሮች አምላክን በመታዘዝ ከፖለቲካ ገለልተኛ በመሆን የማያወላውል አቋም ወስደው ነበር። (ዮሐንስ 17:16) አንዳንዶች ይህን ቅዱስ ጽሑፋዊ አቋም አልተረዱትም ነበር፤ ምሥክሮቹንም ሥር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የሚታገል እምነት የሚከተሉና ለሕግ የማይገዙ ናቸው በማለት በእነሱ ላይ የተሳሳተ አመለካከት አደረባቸው። በዚህም የተነሣ አንዳንዶች በእነዚህ ሰላም ወዳድ ክርስቲያኖች ላይ ግፍ መፈጸሙ ትክክል እንደሆነ ተሰምቷቸዋል። ብዙ ምሥክሮች ከሥራቸው ተባረሩ፣ ተደበደቡ፤ አንዳንዶቹንም በሕዝብ ፊት አዋረዷቸው። አንዳንዶች በግድ ከልጆቻቸው ሲነጥሏቸው የተሰማቸውን ሐዘን ጸንተው ተቋቁመውታል።

በ1972 ከ30,000 በላይ የሚሆኑ ምሥክሮችና መጽሐፍ ቅዱስን ከእነሱ ጋር ያጠኑ የነበሩ አንዳንድ ሰዎች ለሕይወታቸው በመስጋት ከአገራቸው ለመውጣት ተገደዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ የጎረቤት አገር በሆነችው በሞዛምቢክ የስደተኞች ሠፈር ውስጥ ሰፈሩ። ይሁን እንጂ እነዚህ ስደተኞች በ1975 ወደ ማላዊ እንደገና እንዲመለሱ ተደረገ። በዚህም ሳቢያ ተጨማሪ ስደት ደረሰባቸው። ከእነዚህ መካከል ብዙዎቹ ወደ ማጎሪያ ካምፖች ተወሰዱ። ይህ አሠቃቂ መከራ ይደርስባቸው በነበረበት ወቅት የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር በማላዊ ውስጥ ሕጋዊ ዕውቅና ከነበራቸው ድርጅቶች ስም ዝርዝር ውስጥ ተሰረዘ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የይሖዋ ምሥክሮችና ሕጋዊ ድርጅቶቻቸው በዚያች አገር ውስጥ በእገዳ ሥር ቆይተዋል።

ይህ ሁሉ ግፍ ቢደርስባቸውም ምሥክሮቹ የበቀል እርምጃ አልወሰዱም። መንግሥቱን በመቃወም ረብሻ አላስነሱም፤ ወይም አምባጓሮ አልፈጠሩም። ከዚህ ይልቅ በጸሎት እየተጉ “ለበላይ ባለሥልጣኖች” ይኸውም ለመንግሥት ተገቢውን አክብሮት እንዲያሳዩ የሚያዛቸውን ክርስቲያናዊ ግዴታ ፈጽመዋል። (ሮሜ 13:1–7፤ 1 ጢሞቴዎስ 2:1, 2) በተጨማሪም ምሥክሮቹ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰፍረው የሚገኙትን ከፍተኛ ክርስቲያናዊ የአቋም ደረጃዎች ጠብቀዋል። እንዲህ በማድረግም ከሁሉ የላቀ የሥነ ምግባር ምሳሌ ሆነዋል።

በማላዊ የሚገኙት የይሖዋ ምሥክሮች ባገኙት አዲስ ነጻነት በመጠቀም የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን “አመቺ በሆነ ወቅት ላይ” በጥድፊያ ስሜት መስበካቸውን ለመቀጠል ቆርጠው ተነስተዋል።—2 ጢሞቴዎስ 4:2፤ አዓት

[በገጽ 31 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በ1960ዎቹ ወንድም ሄንሽል ከማላዊ ቤቴል ቤተሰብ ጋር

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ