የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w94 5/15 ገጽ 32
  • “የይሖዋ ምሥክሮች አዳኑኝ!”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “የይሖዋ ምሥክሮች አዳኑኝ!”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
w94 5/15 ገጽ 32

“የይሖዋ ምሥክሮች አዳኑኝ!”

በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ብዙዎች “ጨካኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወዱ” ሆነዋል። (2 ጢሞቴዎስ 3:1, 3) አይዛክ የተባለ ምዕራብ አፍሪካ ውስጥ በሚገኝ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ቅርንጫፍ ቢሮ በፈቃደኝነት የሚሠራ አንድ አገልጋይ ይህ አባባል እውነት ሆኖ አግኝቶታል። እንዲህ በማለት ይናገራል፦

“በጥር ወር 1992 ከአምስት ሌሎች ተሳፋሪዎች ጋር ታክሲ ውስጥ ሆኜ ጭር ባለ አካባቢ በአንድ ረጅም መንገድ ላይ እጓዝ ነበር። ከእኔ ጎን ተቀምጣ ከነበረችው ሴት ጋር ውይይት ከፈትኩና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ አንድ ብሮሹር ሳቀርብላት በደስታ ተቀበለችኝ።

“ከቀኑ አሥር ሰዓት ገደማ ሲሆን ድንገት የሰሌዳ ቁጥር የሌላት አንዲት አዲስ መኪና መጥታ ከፊታችን ድቅን አለች። እኛ ያለንባት መኪናም ሲጢጥ የሚል ኃይለኛ ድምጽ አሰምታ ቆመች። እያንዳንዳቸው ጠመንጃ የያዙ ሦስት ግዙፍ ሰዎች ከመኪናዋ ዱብ ብለው ወረዱና እኛ ያለንበትን መኪና በሮች በኃይል ከፈቱ። ከመካከላቸው አንዱ ‘ሁላችሁም ውረዱ’ ሲል ጮኸ።

“ሌላው ሰው የመጽሐፍ ቦርሳዬን ነጠቀኝ። ቦርሳው የያዘው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን ብቻ እንደሆነ ሲመለከት ቦርሳውን ወርውሮ ጣለው። ጠመንጃውን በኔ ላይ ደግኖ ‘ሌላ ምን አለህ?’ ሲል ጠየቀኝ። ወዲያውኑ ቦርሳዬ ውስጥ ያለውን ገንዘብ ሰጠሁት። ‘ያለህ ይህ ብቻ ነው?’ ሲል ጠየቀኝ። ከይሖዋ ምሥክሮች አንዱ መሆኔንና ምሥክሮቹም ውሸት እንደማይናገሩ ነገርኩት። የገንዘብ ቦርሳዬን ቀማኝና ከመጠበቂያ ግንብ ማኅበር የወሰድኩትን የመታወቂያ ካርድ ተመለከተ። ከዚያም ‘እንግዲያው ዋችታወር እዚህ ቆይ’ አለኝ።

“በመቀጠል በታክሲ ውስጥ ሳነጋግራት የነበረችውን ሴት ጠየቃት። እሷም ወዲያውኑ ሀብሏንና በቦርሳዋ ውስጥ የነበረውን ገንዘብ ሰጠችው። ዘራፊው በሚንቀጠቀጠው እጅዋ ላይ ብሮሹሩን ሲመለከት አንድ ላይ የነበርን መሰለውና ከእኔ ጋር እንድትቆይ በእጁ አመለከታት።

“በሌላው በኩል ሌሎቹ የታጠቁ የመንገድ ዘራፊዎች አብረውን ይጓዙ የነበሩትን ሰዎች በኃይል ይደበድቧቸው ነበር። ሹፌሩንና ከእኛ ጋር ይጓዝ የነበረውን ሌላ ሰው ደብድብው ዘረፏቸው። አንደኛው ሌባ የሁለተኛዋን ሴት ሃብል ለመንጠቅ በእጁ ያዘው። እንዳይወስድባት ስትታገለው እስክትሞት ድረስ ደረቷንና ጭንቅላቷን በሰደፍ በኃይል ቀጠቀጧት። ሶስተኛዋን ሴት ከመኪናው ውስጥ ጎትተው አወጧትና ደረቷ ላይ በጥይት መቷት። ያሳዝናል፣ እሷም ሞተች። ምንም ሳንጎዳ የቀረነው እኔና ከእኔ ጋር የነበረችው ወጣት ሴት ብቻ ነበርን።

“ትንሽ ከቆየን በኋላ ሞተር ብስክሌት እየነዳ በዚያ ያልፍ የነበረ አንድ ሰው ይዞን ሲሄድ በፍርሃት ተውጣ የነበረችው ሴት እየደጋገመች ‘የይሖዋ ምሥክሮች አዳኑኝ!’ ትል ነበር።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ