ማመንን በይፋ የደገፉ
ባለፈው መቶ ዘመን መገባደጃ ላይ ለሳይንስ፣ ለፍልስፍና እና ለዓለማዊነት ይሰነዘሩ የነበሩት የድጋፍ አስተያየቶች አምላክን እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ አነሣሽነት የተጻፈ ነው ብሎ ማመንን የሚያፈርሱ ነበሩ።
ነገር ግን የተሰጡት አስተያየቶች እነዚህ ብቻ አልነበሩም። ብዙ ተመራማሪዎች አምላክ የለም ከማለት ይልቅ የአምላክን መኖር በመደገፍ ብዙ መናገር እንደሚቻል ተገንዝበዋል። ከዚህም በተጨማሪ ጥናታቸው መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ አነሣሽነት የተጻፈ የአምላክ ቃል መሆኑን የሚደግፉ መረጃዎች አስገኝቷል።
በዚህ ረገድ ለእምነት ግልጽ የድጋፍ አስተያየቶች ከሰጡት መካከል ታዋቂው ሲ ቲ ራስል ይገኝበታል። 1886 ገጽ ያለው መለኮታዊው የዘመናት ዕቅድ የተባለውን (የእንግሊዝኛ) መጽሐፍ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ አንብበውታል። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ “ከፍተኛ የማሰብ ችሎታ ያለው ፈጣሪ መኖሩ ተረጋገጠ” የሚል ኃይለኛ መልእክት የያዘ ምዕራፍ ይገኝበታል
በቀጣዮቹ አሥርተ ዓመታት ራስል በአምላክና በመጽሐፍ ቅዱስ ለማመን የሚያበቁ ጥናታዊ ጽሑፎችን፣ ትራክቶችንና መጻሕፍትን ጽፎ ነበር። እነዚህም ጽሑፎች በመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስና ትራክት ማኅበር አሳታሚነት ተዘጋጁ። ከእሱ ቀጥሎ የነበረው ሁለተኛው ፕሬዘዳንት ጄ ኤፍ ራዘርፎርድ ፍጥረት (በ1927) የተባለና ሌሎችንም ለእምነት ተጨማሪ ድጋፍ የሚሰጡ የስነ ጽሑፍ ሥራዎች አቅርቧል።
ያ ማኅበር በቅርቡም በዚህ ረገድ ወቅታዊ የሆኑ ተጨማሪ ማብራሪያዎችን አቅርቧል። በጥልቀት ለሚያደርጉት ምርምር የሚረዱዎትን እነዚህን ማብራሪያዎች ከይሖዋ ምሥክሮች ማግኘት ይችላሉ።
በዚህ በመከራ በተሞላ ዓለምም እንኳ ስለ አምላክ፣ ስለ መንግሥቱና እርሱ ለሰው ልጆች ስላለው አስደናቂ ዓላማ ትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት በማግኘት ደስተኛ መሆን ይችላሉ። ተጨማሪ መረጃ ብንሰጥዎ ደስ የሚልዎት ከሆነ ወይም አንድ የይሖዋ ምሥክር መጥቶ እንዲያነጋግርዎትና መጽሐፍ ቅዱስን ያለ ክፍያ እንዲያስተምርዎ የሚፈልጉ ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች፣ የፖ. ሣ. ቁ. 5522፣ አዲስ አበባ ብለው ወይም በገጽ 2 ላይ ካሉት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይጻፉ።
[ከገጽ 32 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]