የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w95 10/15 ገጽ 3-4
  • ፍርሃት ወዳጅ ነው ወይስ ጠላት?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ፍርሃት ወዳጅ ነው ወይስ ጠላት?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ይሖዋን የሚፈራ ልብ ይኑርህ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • ይሖዋን በመፍራት ደስታ ማግኘትን መማር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ይሖዋን ፍራ ትእዛዙንም ጠብቅ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • ይሖዋን ፍሩ ቅዱስ ስሙንም አክብሩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
w95 10/15 ገጽ 3-4

ፍርሃት ወዳጅ ነው ወይስ ጠላት?

“በምን ዓይነት መንገድ ለመሞት እንደምመርጥ አስባለሁ። በጥይት ለመገደል አልፈልግም፤ ሆኖም በጥይት የምገደል ከሆነ ወዲያውኑ ለመሞት እንድችል እዚህ ግምባሬ ላይ እንድመታ እፈልጋለሁ።”

የሎስ አንጀለስ ታይምስ ጋዜጣ ዘጋቢ አንዲት የ14 ዓመት ልጃገረድ ይህን ስትናገር ሰምቷል። ይህ ዘጋቢ በቅርቡ ወጣቶች በአዋቂዎችና በሌሎች ወጣቶች ላይ የፈጸሟቸውን ግድያዎች በተመለከተ ለተማሪዎች ቃለ መጠይቅ አድርጎ ነበር። ዘገባው “በፍርሃት የተሞላ ዓለም” የሚል ርዕስ ተሰጥቶት ነበር።

ብዙዎች በፍርሃት በተዋጠ ዓለም ውስጥ እንደሚኖሩ ማወቅ አያዳግትህም። የሚፈሩት ምንድን ነው? ይህን ይፈራሉ ብሎ የተወሰነ ነገር መጥቀስ ያስቸግራል። በዚህ ገጽ ላይ ባለው ሣጥን ውስጥ ጓደኞችህ ወይም አንተ በምትኖርበት አካባቢ የሚገኙ ብዙ ሰዎች የሚፈሯቸውን ነገሮች ልታገኝ ትችላለህ። ሣጥኑ ከኅዳር 22, 1993 ኒውስ ዊክ መጽሔት የተወሰደ ሲሆን “ከ10 እስከ 17 ዓመት ዕድሜ ውስጥ ለሚገኙ 758 ልጆችና ለወላጆቻቸው” የተደረገውን ቃለ ምልልስ ውጤት ያሳያል።

እነዚህ ልጆች ቃለ ምልልሱ የተደረገላቸው በአሁኑ ጊዜ ቢሆን ኖሮ እንደ መሬት መንቀጥቀጥ የመሳሰሉትን የሚያስፈሯቸውን ሌሎች ነገሮች ተጨማሪ ምክንያቶች አድርገው ይጠቅሱ ነበር። በጥር 1994 በሎስ አንጀለስ ውስጥ ከደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ በኋላ ታይም መጽሔት የሚከተለውን ዘገባ አቅርቦ ነበር፦ “አንድ አሠቃቂ ነገር የተፈጸመባቸው ወይም ሲፈጸም የተመለከቱ ሰዎች የሚደርስባቸው የአእምሮ መረበሽ ምልክቶች ከሆኑት ነገሮች መካከል መጥፎ ትዝታ፣ ቅዠቶች፣ ከልክ በላይ ከአደጋዎች መጠንቀቅና የራስን ሕይወት መቆጣጠር ካለመቻል የሚመጣ ንዴት ይገኙበታል።” የመሬት መንቀጥቀጥ ከደረሰበት አካባቢ ለቆ ወደ ሌላ አካባቢ ለመሄድ የወሰነ አንድ ነጋዴ እንዲህ ብሏል፦ “በንብረቴ ላይ የደረሰው ጥፋት ምንም አይመስለኝም። ድንጋጤውን ግን አልቻልኩትም። ምድር ቤት ውስጥ ጫማህን እንዳደረግህ ትተኛለህ። ምንም እንቅልፍ አይወስድህም። ሌሊት ሌሊት እዚያ ቁጭ ብለህ የመሬት መንቀጥቀጥ ይመጣል ብለህ ስትጠብቅ ታድራለህ። መጥፎ ነገር ነው።”

ሚያዝያ 11, 1995 ከቶኪዮ የተሰማው ዘገባ “በተከታታይ የተፈጸሙት አደጋዎች ጃፓናውያንን አስደንግጠዋቸዋል” የሚል ርዕስ ነበረው። ዘገባው እንዲህ ብሏል፦ “የነርቭ ጋዙ ጥቃት . . . ጃፓናውያንን በጣም ረብሿቸዋል። ይህ የሆነው ጥቃቱ ስለ ወደፊቱ ጊዜ አለመተማመንን የሚፈጥሩ በአንድ ላይ የተፈጸሙ ተከታታይ ድርጊቶች አንድ ክፍል በመሆኑ ነው።. . . ሕዝቡ በአንድ ወቅት በቀንም ሆነ በሌሊት ያለ ምንም ስጋት ይዘዋወርባቸው በነበሩ ቦታዎች በአሁኑ ጊዜ የመተማመን ስሜት የለውም።” ከዚህም በላይ የሚፈሩት አረጋውያን ብቻ አይደሉም። “[የሳጆ ዩንቨርሲቲ] ፕሮፌሰር የሆኑት ኤሺካዋ ስጋቱ . . . በተለይ አይሎ የሚታየው የወደፊቱ ጊዜ ምን እንደያዘላቸው በግልጽ ባልተረዱት በወጣቶች ላይ ነው ብለዋል።”

“ሰዎች ቀደም ሲል ያጋጠማቸው አሸባሪ ነገር የአእምሯቸውን ኬሚካላዊ አሠራር ሊያዛባ ስለሚችል ከበርካታ አሥርተ ዓመታት በኋላም እንኳ አካላቸው ለአንዳንድ ሁኔታዎች ምላሽ ለመስጠት አድሬናሊን የተባለ ሆርሞን እንደሚፈጥር” የተለያዩ ማስረጃዎች ያሳያሉ። ሳይንቲስቶች አእምሮ አንድን አስፈሪ ሁኔታ እንዴት እንደሚተረጉም ለመረዳት በመጣር ላይ ናቸው። ይህም የተለያዩ ዝርዝር ነገሮችን አመዛዝነን እንዴት ፍርሃት እንደሚያድርብን ለማወቅ ይጥራሉ ማለት ነው። ፕሮፌሰር ጆሴፍ ለዱ “አንድ ፍጡር ፍርሃት እንዲያድርበት የሚያደርጉትን የነርቭ አውታሮች በመመርመር የዚህ ዓይነቱን ትዝታ አጠቃላይ አሠራር ለማብራራት እንደምንችል ተስፋ እናደርጋለን” በማለት ጽፈዋል።

ሆኖም አብዛኞቻችን ፍርሃት የሚፈጥሩትን የኬሚካል ወይም የነርቭ ሥርዓቶች ለማወቅ ያን ያህል ፍላጎት የለንም። ከዚህ ይልቅ እንደሚከተሉት ላሉት ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት እንፈልግ ይሆናል፦ የምንፈራው ለምንድን ነው? ለፍርሃት ምን ምላሽ መስጠት አለብን? ጥሩ ፍርሃት ይኖራልን?

አንዳንድ ጊዜ ፍርሃት ሊጠቅምህ ይችላል ቢባል ሳትስማማ አትቀርም። ለምሳሌ ያህል፣ ወደ ቤትህ ስትቃረብ ጨለም ብሏል እንበል። በደንብ ዘግተኸው የሄድከው በር ገርበብ ብሏል። በመስኮት አንድ ጥላ የሚመስል ነገር ሲንቀሳቀስ ያየህ ይመስልሃል። ወዲያውኑ አንድ ችግር እንደተፈጠረ ይሰማህና ጭንቅ ጥብብ ይልሃል። ምናልባት ቤት ውስጥ ያለው አንድ ሌባ ወይም ጩቤ የያዘ ሰው ሊሆን ይችላል።

እንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙህ መፍራትህ ጥንቃቄ ሳታደርግ አደገኛ ወደ ሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ እንዳትገባ ጠብቆህ ሊሆን ይችላል። ፍርሃት ጥንቃቄ እንድታደርግ ወይም ሊያጋጥምህ የሚችለውን አደጋ ከመጋፈጥህ በፊት እርዳታ እንድትጠይቅ ሊረዳህ ይችላል። ለዚህ ምሳሌ የሚሆኑ ብዙ ነገሮች አሉ፦ ከእነዚህ ነገሮች መካከል የኮረንቲ ኃይል እየጨመረ እንደመጣ የሚያስጠነቅቅ ምልክት፣ አንድ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ የምትኖርበት አካባቢ እየገሰገሰ እንዳለ የሚገልጽ የሬዲዮ ማስጠንቀቂያና በተጨናነቀ መንገድ ላይ ስትነዳ መኪናህ የሚያሰማው ሲጥጥ የሚል ድምፅ ይገኙበታል።

አንዳንድ ጊዜ የፍርሃት ስሜት በእርግጥ ወዳጅ ሊሆን ይችላል። ራሳችንን ከአደጋ እንድንጠብቅ ወይም የጥበብ እርምጃ እንድንወስድ ሊረዳን ይችላል። ሆኖም የማያቋርጥ ወይም ከመጠን በላይ የሆነ ፍርሃት ወዳጅ እንዳልሆነ አሳምረህ ታውቃለህ። እንዲህ ዓይነቱ ፍርሃት ጠላት ነው። የትንፋሽ ቁርጥ ቁርጥ ማለት፣ የልብ ምታት መጨመር፣ ሕሊናን መሳት፣ መንቀጥቀጥ፣ ማቅለሽለሽ እና የሚይዙትንና የሚለቁትን የማጣት ስሜት ሊፈጥር ይችላል።

መጽሐፍ ቅዱስ ዘመናችን በምድር ላይ በሚፈጸሙ አስፈሪ ሁኔታዎችና በከፍተኛ ፍርሃት ተለይቶ እንደሚታወቅ እንደሚገልጽ ማወቅህ ትኩረት የሚስብ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ። ይህ የሆነው ለምንድን ነው? ይህ ሁኔታ በአኗኗርህና በአስተሳሰብህ ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል? በተጨማሪም ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር በየቀኑ ሊኖረን ስለሚገባው ጠቃሚና ጥሩ ፍርሃት ምን ሊባል ይችላል? እስቲ እንመልከት።

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

ብዙ ወላጆችና ልጆች እነሱንና ቤተሰባቸውን በይበልጥ ስለሚያሳስቧቸው ነገሮች ሲጠየቁ የሚከተሉትን ሁኔታዎች እንደሚፈሩ ተናግረዋል፦

ልጆች ወላጆች

56% በቤተሰብ አባል ላይ የሚፈጸም ከባድ ወንጀል 73

53% ከሥራ መባረር 60%

43% ምግብ ማግኘት አለመቻል 47%

51% ዶክተር ጋ ቀርቦ ለመታከም አለመቻል 61%

47% መጠለያ ለማግኘት አለመቻል 50%

38% የዕፅ ሱሰኛ የሆነ አንድ የቤተሰብ አባል መኖሩ 57%

38% የቤተሰባቸው መለያየት 33%

ምንጭ፦ የኅዳር 22, 1993 ኒውስ ዊክ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ