የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w96 5/15 ገጽ 8-9
  • በድፍረት የተናገረች አንዲት ትንሽ ልጅ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በድፍረት የተናገረች አንዲት ትንሽ ልጅ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በግልጽ ለመናገር የሚያስችል ድፍረት
  • ንዕማን የተፈወሰበት መንገድ
  • ለእኛ የሚሆኑ ትምህርቶች
  • የመርዳት ፍላጎት ነበራት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • የሠራዊቱ አለቃና ትንሿ ልጅ
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • እምቢተኛ የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ ታዛዥ ሆኗል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • አንዲት ልጅ አንድ ኃያል ሰው ረዳች
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
w96 5/15 ገጽ 8-9

የይሖዋን ፈቃድ ፈጽመዋል

በድፍረት የተናገረች አንዲት ትንሽ ልጅ

በአሥረኛው መቶ ዘመን ከዘአበ በእስራኤልና በሶርያ መካከል የነበረው ዝምድና ሻክሮ ነበር። በየጊዜው እርስ በርስ ይዋጉ ስለነበር ሦስት ዓመት ያለ ጦርነት ማሳለፋቸው በታሪክ መዝገብ ውስጥ ትልቅ ቦታ ተሰጥቶት ነበር።—1 ነገሥት 22:1

በተለይ በዚያን ጊዜ አደጋ ይፈጥሩ የነበሩት በመቶ የሚቆጠሩ ወታደሮችን ያቀፉ የሶርያ ወራሪ ጭፍሮች ነበሩ። እነዚህ ጦረኞች በእስራኤላውያን ላይ ፈጣን ጥቃት እየሰነዘሩ ይዘርፉና ሰዎችን አፍነው በመውሰድ ልጆችን ሳይቀር ብዙዎቹን ባሪያ ያደርጓቸው ነበር።

አንድ ጊዜ ፈጣን ጥቃት ሰነዘሩና ‘አንዲት ትንሽ ልጅ’ በመማረክ ርኅራኄ በጎደለው ሁኔታ ፈሪሃ አምላክ ካላቸው ቤተሰቦቿ ነጥለው ወሰዷት። (2 ነገሥት 5:2) ወደ ሶርያ ከተወሰደች በኋላ አስፈሪና እንግዳ ከሆኑባት ሰዎች ጋር ለመኖር ተገደደች፤ እነዚህ ሰዎች ፀሐይን፣ ጨረቃን፣ ከዋክብትን፣ ዛፎችን፣ ዕፅዋትንና አልፎ ተርፎም ድንጋይ ያመልኩ ነበር። እውነተኛውን አንድ አምላክ ይሖዋን ከሚያመልኩ ቤተሰቦቿና ጓደኞቿ ምንኛ የተለዩ ነበሩ! ይሁን እንጂ ይህች ትንሽ ልጅ የምትኖረው በሰው አገር ቢሆንም ከይሖዋ አምልኮ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ከፍተኛ ድፍረት አሳይታለች። በዚህ የተነሳ የሶርያ ንጉሥ አገልጋይ የሆነ የአንድ ከፍተኛ ባለ ሥልጣን ሕይወት እንዲለወጥ አድርጋለች። ይህን ያደረገችው እንዴት እንደሆነ እንመልከት።

በግልጽ ለመናገር የሚያስችል ድፍረት

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በሰፈረው ታሪክ ውስጥ የልጅቷ ስም አልተጠቀሰም። ይህች ልጅ የንዕማን ሚስት አገልጋይ ሆነች፤ ንዕማን የንጉሡ የዳግማዊ ወልደ አዴር የሠራዊት አለቃ ሆኖ የሚያገለግል ጀግና ሰው ነበር። (2 ነገሥት 5:1) ንዕማን ከፍተኛ ቦታ የነበረው ሰው ቢሆንም አስከፊው የሥጋ ደዌ በሽታ ይዞት ነበር።

ምናልባት የልጅቷ ሰው አክባሪነት የንዕማን ሚስት ምሥጢሯን እንድታካፍላት ገፋፍቷት ሊሆን ይችላል። ሴትየዋ ‘እስራኤል ውስጥ የሥጋ ደዌ የያዛቸው ሰዎች ምን ይደረግላቸዋል?’ በማለት ልጅቷን ጠይቃት ሊሆን ይችላል። ይህች እስራኤላዊት አገልጋይ “ጌታዬ በሰማርያ ካለው ከነቢዩ ፊት ቢደርስ ኖሮ ከለምጹ [“ከያዘው የሥጋ ደዌ፣” አዓት] በፈወሰው ነበር” ብላ በድፍረት ለመናገር ምንም አላፈረችም።—2 ነገሥት 5:3

ልጅቷ የተናገረችውን ነገር ይህ የልጅ የፈጠራ ሐሳብ ነው ብለው ወደ ጎን ገሸሽ አላደረጉትም። ከዚህ ይልቅ ጉዳዩን ለንጉሥ ወልደ አዴር የነገሩት ሲሆን እርሱም ይህን ነቢይ እንዲፈልጉ 150 ኪሎ ሜትር ርቃ ወደምትገኘው ሰማርያ ንዕማንንና ሌሎች ሰዎችን ላከ።—2 ነገሥት 5:4, 5

ንዕማን የተፈወሰበት መንገድ

ንዕማንና አብረውት የነበሩት ሰዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ ከወልደ አዴር የተላከ ደብዳቤና ከፍተኛ መጠን ያለው የገንዘብ ስጦታ ይዘው ኢዮራም ወደተባለው የእስራኤል ንጉሥ ሄዱ። ጥጃ አምላኪ የሆነው ንጉሥ ኢዮራም አገልጋይዋ ልጅ እምነት ባሳደረችበት የአምላክ ነቢይ አለማመኑ አያስደንቅም። ከዚህ ይልቅ ንዕማን ጠብ ፍለጋ የመጣ መስሎት ነበር። ኢዮራም ፍርሃት እንዳደረበት የአምላክ ነቢይ የነበረው ኤልሳዕ ሲሰማ ንጉሡ ንዕማንን ወደ እርሱ ቤት እንዲልከው መልእክት ሰደደ።—2 ነገሥት 5:6-8

ንዕማን ኤልሳዕ ቤት ሲደርስ ነቢዩ “በዮርዳኖስም ሰባት ጊዜ ታጠብ፤ ሥጋህም ይፈወሳል፣ አንተም ንጹሕ ትሆናለህ” ብሎ እንዲነግረው መልእክተኛ ላከበት። (2 ነገሥት 5:9, 10) ንዕማን በጣም ተቆጣ። ተአምራዊና የሰዎችን ትኩረት የሚስብ የፈውስ ሥነ ሥርዓት ጠብቆ ነበር። “የደማስቆ ወንዞች አባናና ፋርፋ ከእስራኤል ውኆች ሁሉ አይሻሉምን? በእነርሱስ ውስጥ መታጠብና መንጻት አይቻለኝም ኖሮአልን?” በማለት ጠየቀ። ንዕማን ተቆጥቶ ከኤልሳዕ ቤት ተመለሰ። ሆኖም አገልጋዮቹ ምክንያታዊ ሐሳብ አቅርበው ሲያስረዱት የታዘዘውን አደረገ። በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ ሲታጠብ “ሥጋውም እንደ ገና እንደ ትንሽ ብላቴና ሥጋ ሆኖ ተመለሰ፣ ንጹሕም ሆነ።”—2 ነገሥት 5:11-14

ንዕማን ወደ ኤልሳዕ ተመለሰና “ከእስራኤል ዘንድ በቀር በምድር ሁሉ አምላክ እንደሌለ አወቅሁ” አለ። ንዕማን “ከእንግዲህ ወዲህ ከእግዚአብሔር በቀር ለሌሎች አማልክት የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት አላቀርብም” በማለት ተሳለ።—2 ነገሥት 5:15-17

ለእኛ የሚሆኑ ትምህርቶች

አንዲት የቤት አገልጋይ የሆነች ትንሽ ልጅ በድፍረት ባትናገር ኖሮ ንዕማን ወደ ነቢዩ ኤልሳዕ አይሄድም ነበር። በዛሬው ጊዜ ብዙ ልጆች እንደዚች ልጅ እያደረጉ ነው። በትምህርት ቤት ውስጥ አምላክን ለማገልገል ፍላጎት የሌላቸው ብዙ ተማሪዎች በዙሪያቸው ሊኖሩ ይችላሉ። ሆኖም የሚያምኑበትን ነገር በግልጽ ከመናገር ወደ ኋላ አይሉም። ከእነዚህም መካከል አንዳንዶቹ ገና በጨቅላነት ዕድሜያቸው እንዲህ ማድረግ ጀምረዋል።

ለምሳሌ አውስትራሊያ ውስጥ የምትኖረውን የአምስት ዓመቷን አሊግዛንድራን ተመልከት። አሊግዛንድራ ትምህርት ስትጀምር እናቷ ስለ ይሖዋ ምሥክሮች እምነቶች ለአስተማሪዋ ልትነግራት ቀጠሮ ያዘች። ሆኖም የአሊግዛንድራ እናት ያልጠበቀችው ነገር ተከሰተ። አስተማሪዋ “ብዙዎቹን እምነቶቻችሁን እንዲሁም አሊግዛንድራ ትምህርት ቤቱ ውስጥ በምን እንደምትሳተፍና እንደማትሳተፍ አውቄአለሁ” አለቻት። በትምህርት ቤቱ የሚማሩ ሌሎች የይሖዋ ምሥክሮች ልጆች ስለሌሉ የአሊግዛንድራ እናት ተገረመች። “አሊግዛንድራ ስለ እምነቷ ነግራናለች” በማለት አስተማሪዋ ግልጽ አደረገችላት። አዎን፣ ይህች ትንሽ ልጅ ቀድሞውኑ አስተማሪዋን በዘዴ አነጋግራት ነበር።

እንደነዚህ ያሉ ልጆች በድፍረት ይናገራሉ። በዚህም መንገድ ከመዝሙር 148:12, 13 ጋር በሚስማማ መንገድ ይመላለሳሉ፦ “ጎልማሶችና ቆነጃጅቶች፣ ሽማግሌዎችና ልጆች፤ የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ፤ ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሎአልና፣ ምስጋናውም በሰማይና በምድር ላይ ነው።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ