የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w96 6/1 ገጽ 3-4
  • ከወገናዊነት የመነጨ ጥላቻ ደርሶብሃልን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከወገናዊነት የመነጨ ጥላቻ ደርሶብሃልን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከወገናዊነት የመነጨ ጥላቻ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል
  • ጭፍን ጥላቻ ዓለም አቀፍ ችግር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ጭፍን ጥላቻ—አንተንም አጥቅቶህ ይሆን?
    ንቁ!—2020
  • ከጭፍን ጥላቻ የጸዳ ዓለም ይመጣ ይሆን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ጭፍን ጥላቻና መድሎ—መንስኤያቸውን ለይቶ ማወቅ
    ንቁ!—2009
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
w96 6/1 ገጽ 3-4

ከወገናዊነት የመነጨ ጥላቻ ደርሶብሃልን?

የጎሳ ግጭትን፣ ብሔርተኝነትን፣ የዘር መድልዎን፣ ወገናዊነትንና የዘር ጭፍጨፋን የሚያዛምዳቸው ነገር ምንድን ነው? እነዚህ ሁሉ በሰዎች ዘንድ በእጅጉ ተስፋፍቶ የሚገኘው ዝንባሌ ይኸውም ከወገናዊነት የመነጨ ጥላቻ ውጤት ናቸው!

ከወገናዊነት የመነጨ ጥላቻ [ፕሬጁዲስ] ምንድን ነው? አንድ ኢንሳይክሎፔድያ “ሚዛናዊ ፍርድ ለመስጠት ሲባል ጊዜ ወስዶ ካለማሰብና ካለመጨነቅ የተነሣ የሚመነጭ አመለካከት” የሚል ፍቺ ሰጥቶታል። ፍጹማን ባለመሆናችን በተወሰነ መጠንም እንኳ ቢሆን የወገናዊነት ዝንባሌ ማሳየታችን አይቀርም። ምናልባትም የነገሩን ግራና ቀኝ ሳታይ ፍርድ የሰጠህባቸው አጋጣሚዎች እንዳሉ ትዝ ሊልህ ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ዓይነቶቹን የወገናዊነት ዝንባሌዎች ይሖዋ አምላክ ፍርድ ከሚሰጥበት ሁኔታ ጋር በማነጻጸር ይናገራል። እንዲህ ይላል፦ “ሰው እንደሚያይ እግዚአብሔር አያይምና፣ . . . ሰው ፊትን ያያል፣ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል።”—1 ሳሙኤል 16:7

ከወገናዊነት የመነጨ ጥላቻ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል

ሁሉም ሰው ቢያንስ በአንድ አጋጣሚ በሌሎች ሰዎች ዘንድ የተሳሳተ ግምት ተሰጥቶት እንደሚሆን ምንም አያጠራጥርም። (ከመክብብ 7:20, 21 ጋር አወዳድር።) በጥቅሉ ሲታይ ሁላችንም ከወገናዊነት የመነጨ ጥላቻ ያጠቃናል። ይሁን እንጂ እንደዚህ ያሉትን ከወገናዊነት የመነጩ የጥላቻ ዝንባሌዎች ቶሎ ከአእምሮአችን ማስወጣት ጉዳቱን ሊቀንሰው ወይም ጨርሶ ሊያስቀረው እንደሚችል እሙን ነው። ጉዳት የሚያስከትለው እንዲህ ያለውን ሐሳብ አምቆ መያዝ ነው። እውነት ያልሆነውን ነገር አምነን እንድንቀበል ሊያደርገን ይችላል። ለምሳሌ ያህል አንዳንድ ሰዎች ከወገናዊነት በመነጨ ጥላቻ ተሸንፈው አንድ ሰው የአንድ ሃይማኖት አባል ስለሆነ፣ ከተወሰነ ዘር ወይም ብሔር ስለመጣ ብቻ ስስታም፣ ሰነፍ፣ ወይም ኩራተኛ ሊሆን እንደሚችል አድርገው ያምናሉ።

በአብዛኛው እንዲህ ዓይነቱ የተሳሳተ ግምት በሌሎች ሰዎች ላይ ፍትሕ የጎደለውና አግባብነት የሌለው ድርጊት አልፎ ተርፎም ኢሰብዓዊ ድርጊት ወደ መፈጸም ያመራል። በእርስ በርስ እልቂቶች፣ በዘር ማጥፋት ዘመቻዎች፣ በጎሳ ምንጠራና ከወገናዊነት በመነጩ ሌሎች መራራ ጥላቻዎች መዘዝ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በምድር ዙሪያ የሚገኙ መንግሥታት የሁሉም ሰዎች ነፃነት፣ ደህንነትና እኩልነት የተጠበቀ እንዲሆን በሕግ በመደንገግ ከወገናዊነት የመነጩ ጥላቻዎችን ለማስቀረት ታግለዋል። የአገርህን ሕገ መንግሥት ወይም ዋና ዋናዎቹን ሕጎች ብታነብ ዜጎች የዘር፣ የጾታ ወይም የሃይማኖት ልዩነት ሳይደረግባቸው መብታቸው እንዲከበር የሚያዝ ሐረግ ወይም ድንጋጌ እንደምታገኝ የታወቀ ነው። ይሁንና ከወገናዊነት የመነጨ ጥላቻና የዘር መድልዎ በዓለም ዙሪያ በእጅጉ ተስፋፍቷል።

ከወገናዊነት የመነጨ ጥላቻ ደርሶብሃልን? በዘርህ፣ በዕድሜህ፣ በጾታህ፣ በብሔርህ ወይም በሃይማኖታዊ እምነትህ ምክንያት ብቻ ስስታም፣ ሰነፍ፣ ወይም ኩራተኛ እንደሆንክ ተቆጥረህ ታውቃለህን? ከወገናዊነት በመነጨ ጥላቻ ተገቢ ትምህርት፣ ሥራ፣ የመኖሪያ ቤትና ማኅበራዊ አገልግሎቶች እንዳታገኝ ተከልክለሃልን? እንዲህ ያለ ሁኔታ ደርሶብህ ከሆነ እንዴት መቋቋም ትችላለህ?

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የወገናዊነት ስሜት በውስጣችን እንዲያቆጠቁጥ መፍቀድ የዘር ጥላቻን ያስፋፋል

[ምንጭ]

Nina Berman/Sipa Press

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ