የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w96 8/1 ገጽ 32
  • “በሕልሜ ነው በውኔ?”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “በሕልሜ ነው በውኔ?”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
w96 8/1 ገጽ 32

“በሕልሜ ነው በውኔ?”

በ1995 የበጋ ወራት “ደስተኛ አወዳሾች” በሚል ጭብጥ በማላዊ ከተከናወኑት ታሪካዊ የሆኑ የይሖዋ ምሥክሮች የአውራጃ ስብሰባዎች መካከል አንዱን በሚመለከት የቀረበ ሪፖርት።

“ከማላዊ ሐይቅ ምዕራባዊ ዳርቻ ጥቂት ራቅ ብሎ ባለው አውራ ጎዳና ላይ ከ29 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ምልክት ይታይ ነበር። ‘የይሖዋ ምሥክሮች የአውራጃ ስብሰባ’ ይላል።

“ከምልክቱ አጠገብ አንድ ትልቅ የጭነት መኪና ቆሟል፤ በስብሰባው ላይ ለመገኘት በመኪናው ተሳቢ ተጭነው ከሙዙዙ ከተማ የመጡ ከ200 የሚበልጡ ወንድሞች ሲወርዱ ይታያሉ። ከሌሎች አካባቢዎች ከመጡ ወደ 3,000 የሚጠጉ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጋር አብረው ለመቆየት በርካታ ልብሶች፣ ብርድ ልብስ፣ ድስት፣ ባልዲ፣ ምግብ፣ የማገዶ እንጨትና መጽሐፍ ቅዱስ ይዘው መጥተዋል።

“እነርሱ ከመኪናው ላይ ሲወርዱ ሰላም እያልናቸው ሳለ የ63 ዓመቱ ጆርጅ ቺካኮ ንኮታኮታ ከተባለ መንደር ተነሥቶ የሁለት ቀን መንገድ ከተጓዘ በኋላ ብስክሌቱን በአሸዋ ውስጥ እየገፋ ብቅ አለ። ወንድም ቺካኮ ባለፉት ብዙ ዓመታት የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችን ለመጣስ አሻፈረኝ በማለቱ እሥር እየተፈረደበት አራት ጊዜ ወኅኒ ወርዷል። የአጎቱ ልጅ እስር ቤት እያለ በደረሰበት ድብደባ ሕይወቱ አልፏል። ወንድም ቺካኮ ‘በሕልሜ ነው በውኔ?’ ሲል ጠየቀ። ‘ይህ ትልቅ ስብሰባ የሚከናወነው ወለል ባለ የቀን ብርሃን ነው፤ እና እነዚህ ሰዎች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የመንግሥቱን መዝሙሮች ይዘምራሉ! ለረጅም ጊዜ ሌሊት በጨለማ ተሰብስበናል፣ የመንግሥቱን መዝሙሮች የምንዘምረው በሹክሹክታ ነበር፣ ለማጨብጨብም ሁለት እጃችንን እናፋትግ ነበር። አሁን በግልጽ ተሰበሰብን፤ ሰዎቹም በጣም ጥቂት እንደሆንን አድርገው ያስቡ ስለ ነበር ይህን ያህል ብዙ መሆናችንን ማየታቸው አስገርሟቸዋል!’

“ስብሰባው የሚደረግበት ቦታ በሣር የተከበበ ሲሆን በተረበረበ መቃ ዳስ ተሠርቶለታል። በስብሰባው ላይ ለመገኘት የመጡትን ወንድሞች ለማስተናገድ ትናንሽ የሰሌን ባርኔጣዎችና ሜዳ ላይ የተሠሩ ማረፊያ ክፍሎች ተዘጋጅተዋል። የምሽቱ አየር ከእንግዲህ የስደት ፍርሃት በማያፍነው ለዛ ያለው ዜማ ተሞልቷል።

“የአውራጃ ስብሰባው ጭብጥ ‘ደስተኛ አወዳሾች’ የሚል መሆኑ ምንኛ ተስማሚ ነው!”

[ምንጭ]

Mountain High Maps® Copyright © 1995 Digital Wisdom, Inc.

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ