የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w96 10/15 ገጽ 3
  • ከሞት በኋላ ሕይወት አለን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከሞት በኋላ ሕይወት አለን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለረጅም ዘመን መልስ ያላገኘ ጥያቄ
  • ስለ ሞት የሚነገሩ አንዳንድ አፈ ታሪኮችን ጠለቅ ብሎ መመርመር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • ሙታንን ልትፈራ ይገባሃል?
    ንቁ!—2009
  • ሞትን የምንፈራው ለምንድን ነው?
    ንቁ!—2007
  • የሞቱ ሰዎች በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
w96 10/15 ገጽ 3

ከሞት በኋላ ሕይወት አለን?

የምናረጀውና በመጨረሻም የምንሞተው ለምንድን ነው? ሕይወት ከሞት በኋላ በሆነ መንገድ ሕያው ሆኖ ይቀጥላልን? የሚሉት ሁለት ጥያቄዎች ለብዙ ሺህ ዓመታት የሰውን ልጅ ግራ ሲያጋቡ ኖረዋል።

ድንቅ ግኝቶችን ያስመዘገበው ዘመናዊ የሕክምና ሳይንስ እንኳ ለመጀመሪያው ጥያቄ ቁርጥ ያለ ወይም የሚያረካ መልስ መስጠት ባለመቻሉ ይህ ጥያቄ ለብዙ ሰዎች እንቆቅልሽ እንደሆነ ቀርቷል።

ለሁለተኛው ጥያቄ ብዙ የተለያዩ መልሶች ሲሰጡ ኖረዋል። ይሁን እንጂ በጥቅሉ ሲታይ ከሞት በኋላ ሕይወት ይኖር ይሆን? ለሚለው ጥያቄ የሚሰጡት መልሶች ሕይወት ይህ ብቻ አይደለም እና ሞት የሕይወት መጨረሻ ነው በሚሉት ሁለት ሐሳቦች ዙሪያ የሚሽከረከሩ ናቸው። ሁለተኛውን ሐሳብ ከሚደግፉት ወገኖች መካከል ብዙዎቹ ከሰው ልጅ አጭር የሕይወት ዘመን ውጭ ሌላ ምንም ነገር አለመኖሩን ቅንጣትም ታክል እንደማይጠራጠሩ ይናገራሉ። እነዚህ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ከዚህ ተቃራኒ የሆኑ ሐሳቦች ሲቀርቡላቸው “ተመልሶ መጥቶ እንዲህ ነው ብሎ የነገረን የለም” የሚል ምላሽ ይሰጣሉ።

ሌሎች አወዛጋቢ ጥያቄዎች ሲነሡ እንደሚያደርጉት ሁሉ በዚህም ረገድ ቢሆን ምንም ዓይነት መደምደሚያ ላይ ያልደረሱና በዚህም ሆነ በዚያ አሳማኝ ምክንያት የሚያቀርበውን ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ እንደሆኑ የሚናገሩ ሰዎች አሉ። ይሁን እንጂ ሌሎች ደግሞ “ሲደርስ እናየዋለን!” የሚል የፌዝ መልስ ይሰጣሉ።

ለረጅም ዘመን መልስ ያላገኘ ጥያቄ

የምሥራቅ ሰው የነበረውና የደረሰበትን መከራ በትዕግሥት በማሳለፉ የሚታወቀው ኢዮብ ከ3,500 ዓመታት ገደማ በፊት ከሞት በኋላ ስላለው ሕይወት አንድ ጥያቄ አንሥቷል። ኢዮብ ጥያቄውን ያቀረበው እንደሚከተለው ሲል ነበር፦ “ሰው ግን ይሞትና ይጋደማል፤ የመጨረሻ ትንፋሹንም ይተነፍሳል ከዚያ በኋላም አይገኝም። ውኃ ከባሕር ውስጥ እንደሚያልቅ ወይም ወንዙ እንደሚደርቅና እንደሚሰነጣጠቅ ሰውም ተኝቶ አይነሣም፤ . . . በውኑ ሰው ከሞተ ተመልሶ ሕያው ይሆናልን?”—ኢዮብ 14:10-14 ኒው ኢንተርናሽናል ቨርሽን

ይሁን እንጂ ከሞት በኋላ ስላለው ሕይወት ጥያቄ ያነሣው ኢዮብ ብቻ አይደለም። ኢንሳይክሎፔድያ ኦቭ ሪሊጅን ኤንድ ኤቲክስ “ስቴት ኦቭ ዘ ዴድ” (ሙታን የሚገኙበት ሁኔታ) በሚለው ርዕሱ ሥር የሚከተለውን ጠቃሚ ሐሳብ አስፍሯል፦ “የሰው ልጅ በመንፈሳዊ ዓለም የሚኖረውን ሕይወት በተመለከተ ከሞት በኋላ ምን ዓይነት ሁኔታ ይኖረኝ ይሆን የሚለውን ጥያቄ ያክል አእምሮውን የሚያስጨንቀው ነገር የለም። በዓለም ዙሪያ ባሉ ሃይማኖቶች ውስጥ የታቀፉት [የአገሬው ሰዎች] በጥቅሉ ሲታይ ስለ መንፈሳዊው ዓለም ማለትም በዚያ ያለው ሕይወት ምን እንደሚመስል፣ ሁኔታው ሁሉ ሳይቀር ወለል ብሎ ይታያቸዋል፤ ይህም ስለዚህ ርዕሰ ጉዳይ ምን ያህል አጥብቀው እንደሚያስቡ ያሳያል። በጣም ተስፋፍቶ የሚገኘው የሙታን ፍርሃት ሙታን ሕልውናቸው አላከተመም የሚለውን ጥንታዊ ሐሳብ የሚያንጸባርቅ ነው። ሞት ሰዎች የነበራቸውን ኃይል ያጠፋል፤ ይህ ምንም የማያሻማ ነገር ነው፤ ይሁን እንጂ ሰውዬው ከሞተ በኋላ መሥራቱን የሚቀጥል ኃይል አይኖርምን? ካለስ ይህ ኃይል ረቂቅና ምሥጢራዊ በሆነ መንገድ ሊገለጥ አይችልምን? ሰዎች ከሥጋ የተለየ መንፈስ፣ ነፍስ ወይም ጣረሞት አለ ብለው በቀጥታ አመኑም አላመኑ ሙታን በሆነ መልኩ በሕይወት መኖራቸውን ይቀጥላሉ ብለው እንደሚያስቡ ለመናገር የሚያስደፍር በቂ ምክንያት ያለ ይመስላል።”

አንተም ከላይ ከተገለጹት ሦስት ወገኖች ከአንዱ ልትመደብ ትችል ይሆናል፤ እነዚህም፦ ከሞት በኋላ ምን እንዳለ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም የሚሉ፣ ከሞት በኋላ የሆነ ዓይነት ሕይወት ይኖራል ብለው የሚያምኑ እና ሕይወት ይህ ብቻ ነው የሚሉት ናቸው። ከየትኛውም ወገን ሆንክ ከየትኛው የሚቀጥለውን ርዕስ በጥንቃቄ እንድትመረምር እንጋብዝሃለን። በዚህ ርዕስ ውስጥ ከሞት በኋላ አስደሳች ሕይወት አለ ለሚለው ተስፋ እንዲሁም ይህ የሚሆነው እንዴት ነው? የት እና መቼስ? ለሚሉት ጥያቄዎች ሁሉ የሚቀርቡት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች ምን ያህል አሳማኝ እንደሆኑ ለማስተዋል ሞክር።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ