የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w96 12/15 ገጽ 32
  • የተረጋጋ ልብ የሚያስገኛቸው ጥቅሞች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የተረጋጋ ልብ የሚያስገኛቸው ጥቅሞች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
w96 12/15 ገጽ 32

የተረጋጋ ልብ የሚያስገኛቸው ጥቅሞች

ዘመናዊ የሕክምና ሳይንስ ግልፍተኛ መሆን የሰውን አካል እንደሚጎዳ ከተገነዘበ ውሎ አድሯል። ከመቶ ዓመት በፊት ዘ ጆርናል ኦቭ ዘ አሜሪካን ሜዲካል አሶሲዬሽን (ጃማ) እንዲህ ብሎ ነበር፦ “ሰው በቁጣ ምክንያት ይሞታል፤ ከዚያም በአእምሮው ውስጥ የተፈጠረውን ውጥረት መቋቋም ባለመቻሉ በልብ ድካም ሞተ ይባል ይሆናል። ይሁን እንጂ የልብ ድካሙን ያስከተለው ለረዥም ጊዜ የቆየ ንዴት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ነው ብሎ የሚያስብ ሰው ያለ አይመስልም።”

ከላይ የተጠቀሱት ቃላት የአምላክ ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን ለሚማሩ ሰዎች አዲስ አይሆኑባቸውም። ጃማ የተባለው መጽሔት ንዴት የሚያስከትላቸውን አደጋዎች ከመናገሩ ከ29 መቶ ዘመናት በፊት ንጉሥ ሰሎሞን “የተረጋጋ ልብ የሥጋ ሕይወት ነው” ሲል በመንፈስ አነሣሽነት ጽፎ ነበር። (ምሳሌ 14:30 አዓት) እነዚህ ቃላት በዛሬው ጊዜም እውነተኛ ናቸው።

የተረጋጋ መንፈስ በመያዝ ብዙውን ጊዜ ከጭንቀት ጋር በተያያዘ ምክንያት ከሚመጡት እንደ ደም ግፊት፣ ራስ ምታትና የመተንፈስ ችግሮች ያሉ በሽታዎች ከመያዝ እንድናለን። ሆኖም ‘ከቁጣና ከግልፍተኛነት’ ለመራቅ ጥረት ካደረግን ከጥሩ ጤንነት በተጨማሪ ከሌሎች ሰዎች ጋር መልካም ግንኙነት ይኖረናል። (መዝሙር 37:8) ኢየሱስ የዋህና ለሌሎች ልባዊ አሳቢነት ያለው ሰው ስለ ነበረ ሰዎች ወደ እሱ በቀላሉ ይሳቡ ነበር። (ማርቆስ 6:31-34) በተመሳሳይም እኛ የተረጋጋ ልብ እንዲኖረን ከጣርን የሌሎችን መንፈስ የምናድስ እንሆናለን።—ማቴዎስ 11:28-30

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ