በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በዚያ ይገኛሉ—እርስዎስ?
የት ነው የሚገኙት? የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል ወደሚከበርበት ቦታ ነው። በ1996 በመላው ዓለም 12,921,933 ሰዎች ተገኝተው ነበር።
ሰዎች በበዓሉ ላይ የሚገኙት ለምንድን ነው? የኢየሱስ ሞት ለሰው ልጆች ካለው ትርጉም አንፃር ነው። የኢየሱስ ሞት ሰዎች ከበሽታ፣ ከሥቃይና ከመከራ እንዲሁም ከሞት የሚገላገሉበትን መንገድ ከፍቷል። ሌላው ቀርቶ በሞት የተለዩን የምናፈቅራቸው ሰዎች እንኳ ተመልሳ በምትቋቋመው ገነት ውስጥ ለመኖር ትንሣኤ ያገኛሉ።
የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እንዲህ ዓይነቱን በረከት ሊያመጣ የሚችለው እንዴት ነው? ይህን ጉዳይ እንዲመረምሩ ተጋብዘዋል። የይሖዋ ምሥክሮች በዚህ ትልቅ ትርጉም በሚሰጠው በዓል ላይ አብረዋቸው እንዲገኙ ሞቅ ያለ ግብዣ ያቀርቡልዎታል።
በአቅራቢያዎ ባለው የመንግሥት አዳራሽ ሊገኙ ይችላሉ። በዚህ ዓመት በዓሉ የሚከበረው እሑድ መጋቢት 23 ቀን (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ደግሞ መጋቢት 14, 1989) ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ነው። ትክክለኛውን ጊዜ በአካባቢዎ ከሚገኙት የይሖዋ ምሥክሮች ጠይቀው ይረዱ።