የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w97 10/1 ገጽ 3-4
  • ሕያው በሆነ አምላክ ማመን ትችላለህን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሕያው በሆነ አምላክ ማመን ትችላለህን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሥቃይና ሕያው የሆነ አምላክ
  • ፍጥረት ወይስ ዝግመተ ለውጥ?—ክፍል 1፦ አምላክ መኖሩን እንዳምን ያደረገኝ ምንድን ነው?
    የወጣቶች ጥያቄ
  • ፈጣሪ ስለመኖሩ እምነት ማዳበር ይቻላል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ሕያው አምላክ የሆነውን ይሖዋን እወቅ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ሁሉንም ነገሮች የሠራው ፈጣሪ
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
w97 10/1 ገጽ 3-4

ሕያው በሆነ አምላክ ማመን ትችላለህን?

አንድ በብሪታንያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በበላይነት የሚያገለግሉ ቄስ እንዲህ ብለዋል:- “ክርስቲያን ለመሆን የግድ በአምላክ ማመን አያስፈልግም። . . . ዛሬ መሠረታዊ የሆነ የአስተሳሰብ ለውጥ በሚደረግበት ጊዜ ላይ የምንገኝ ቢሆንም በ21ኛው መቶ ዘመን ግን ቤተ ክርስቲያን አምላክ የለሽ መሆኗ የተለመደ ነገር ይሆናል።” ቄሱ ይህን የተናገሩት ሲ ኦቭ ፌይዝ የተባለውን ቡድን ወክለው ሲሆን ቢያንስ አንድ መቶ የሚያህሉ የብሪታንያ ቀሳውስት በጉዳዩ ተስማምተውበታል። እነዚህ “በአምላክ መኖር የማያምኑ ክርስቲያኖች” ሃይማኖትን የፈጠረው ሰው እንደሆነና አንድ የቡድኑ አባል እንደተናገረው ደግሞ አምላክ “የሰው ሐሳብ የወለደው” ብቻ እንደሆነ በመግለጽ ይከራከራሉ። ከሰብዓዊ ባህርይ ውጪ የሆነ አምላክ አለ የሚለው አባባል ከሚያራምዱት አስተሳሰብ ጋር አይጣጣምም።

በ1960ዎቹ ዓመታት “አምላክ ሞቷል” የሚለው አስተሳሰብ በስፋት ተቀባይነትን አግኝቶ ነበር። ይህ አስተሳሰብ በ19ኛው መቶ ዘመን የነበረውን የጀርመን ፈላስፋ የፍሬድሪክ ኒትሸን አመለካከት የሚያንጸባርቅና ለብዙ ወጣቶች ደግሞ የፈለጉትን እንዲያደርጉ ማለትም በጋብቻ ሳይተሳሰሩ ከተቃራኒ ጾታ ጋር እንዲኖሩና አደንዣዥ ዕፅ እንዲወስዱ የሚያስችላቸውን ነፃነት የሚሰጥ ነበር። ይሁን እንጂ ይህን የመሰለው ነፃነት ፍላወር ቺልድረን የተባሉትን ሂፒዎች ይበልጥ አስደሳች የሆነ ሕይወት አስገኝቶላቸዋልን?

በነዚሁ አሥርተ ዓመታት ውስጥ የአንግሊካን ጳጳስ የሆኑት ጆን ኤ ቲ ሮቢንሰን ለአምላክ ሐቀኛ መሆን የሚል ርዕስ ያለው ከፍተኛ ውዝግብ ያስነሳ መጽሐፍ አሳተሙ። እንደሳቸው ያሉ ብዙ ቀሳውስት አምላክ “ሰዎች የራሳቸውን ተሞክሮ መሠረት አድርገው የፈጠሩት ሐሳብ ብቻ” እንደሆነ አድርገው በመግለጻቸው ነቀፋ ሰንዝረውባቸዋል። የቲኦሎጂ ፕሮፌሰር የሆኑት ኪት ዋርድ “በአምላክ የማመኑ ጉዳይ በአስተዋይ ሰዎች ገሸሽ የተደረገ ጊዜ ያለፈበት አጉል እምነት ነውን?” ሲሉ ጠይቀዋል። የራሳቸውን ጥያቄ ሲመልሱ “ዛሬ አንድ ሃይማኖት ከሁሉ ይበልጥ ሊያሳስበው የሚገባው ነገር አምላክን በተመለከተ የነበረው ባህላዊ አስተሳሰብ መልሶ እንዲያንሰራራ ማድረግ ነው” ብለዋል።

ሥቃይና ሕያው የሆነ አምላክ

ሕያው በሆነ አምላክ የሚያምኑ ብዙ ሰዎች እምነታቸውን ከሚያዩት አሳዛኝ መከራና ሥቃይ ጋር ለማዛመድ ይቸግራቸዋል። ለምሳሌ ያህል በመጋቢት 1996 በስኮትላንድ አገር በደንብሌን ከተማ 16 ልጆች ከመምህራቸው ጋር በሽጉጥ ተገድለዋል። አንዲት በሁኔታው ግራ የተጋባች ሴት “የአምላክ ፈቃድ ምን እንደሆነ አይገባኝም” ብላለች። ልጆቹ ይማሩበት ከነበረው ትምህርት ቤት ውጪ ከአበቦች ጋር የተቀመጠ አንድ ካርድ የደረሰው መከራ ያስከተለውን ሐዘን ይገልጻል። በካርዱ ላይ የተጻፈው “ለምን?” የሚል አንድ ቃል ብቻ ነበር። የደንብሌን ካቴድራል ቄስ መልስ ሲሰጡ “ምንም ማብራሪያ ለመስጠት አይቻልም። ይህ ለምን እንደተከሰተ መልስ ለመስጠት አንችልም” ብለዋል።

ይህ ከተፈጸመ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በዚያው ዓመት በእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ታዋቂ የነበረ አንድ ወጣት ቄስ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለ። ቸርች ታይምስ የተባለ ጽሑፍ የሊቨርፑሉ አቡን “የአምላክን በር ለምን? ለምን? በሚሉ ጥያቄዎች ስለመደብደብ” ሲናገሩ በድንጋጤ የተዋጠ አንድ ጉባኤ ያዳምጣቸው እንደነበር ዘግቧል። እኚህ ቄስም ቢሆኑ ሕያው ከሆነ አምላክ የተገኙ የሚያጽናኑ ቃላትን ለመናገር አልቻሉም።

ታዲያ እኛ ማመን ያለብን በምንድን ነው? ሕያው በሆነ አምላክ ለማመን የሚያስችል ጥሩ ምክንያት አለ። ይህ ደግሞ ከላይ የተነሱትን ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችል ቁልፍ ነው። ቀጥሎ በሚገኘው ርዕስ ውስጥ የቀረበውን ማስረጃ እንድትመለከት እንጋብዝሃለን።

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ካርዱ “ለምን?” በማለት ይጠይቃል

[ምንጭ]

NEWSTEAM No. 278468/Sipa Press

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ