የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w97 12/15 ገጽ 30
  • ታስታውሳለህን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታስታውሳለህን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የራስን ጥቅም የመሰዋትና በታማኝነት የመጣበቅ ምሳሌ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ‘እርስ በርስ በነፃ ይቅር መባባላችሁን ቀጥሉ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ኤልሳዕ የእሳት ሠረገሎችን አይቷል አንተስ ይታዩሃል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
w97 12/15 ገጽ 30

ታስታውሳለህን?

በቅርብ ጊዜ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች አንብበሃቸዋልን? ከሆነ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መመለስ ትችል እንደሆነ ተመልከት:-

◻ ለአንድ ወጣት ክርስቲያን የመማር ዋና ዓላማ ምንድን ነው?

የትምህርት ዋነኛ ዓላማ ወጣቶች ውጤታማ የይሖዋ አገልጋዮች እንዲሆኑ ማስታጠቅ ሊሆን ይገባል። ለዚህ የሚረዳው ከሁሉ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነው ትምህርት ደግሞ መንፈሳዊ ትምህርት ነው።​—⁠8/15፣ ገጽ 21

◻ አንድ ክርስቲያን ጓደኛችን የሠራውን ከባድ ኃጢአት ለሽማግሌዎች የምንገልጠው በምን ምክንያቶች የተነሳ ነው?

አንድን ከባድ ኃጢአት መግለጥ አስፈላጊ የሆነበት አንዱ ምክንያት የጉባኤውን ንጽሕና ለመጠበቅ የሚያስችል በመሆኑ ነው። ሌላው ምክንያት ደግሞ እንዲህ ማድረጋችን ለአምላክ፣ ለጉባኤውና ኃጢአት ለፈጸመው ግለሰብ ያለንን በመሠረታዊ ሥርዓት የሚመራ ክርስቲያናዊ ፍቅር የምናሳይበት እርምጃ ስለሆነ ነው።​—⁠8/15፣ ገጽ 28, 30

◻ ‘የይሖዋን ቀን መምጣት ሁልጊዜ አቅርቦ መመልከት’ ሲባል ምን ማለት ነው? (2 ጴጥሮስ 3:​12)

‘የይሖዋን ቀን’ ከአእምሮአችን አለማውጣት ማለት ነው። ይሖዋ በዚህ የነገሮች ሥርዓት ላይ እርምጃ የሚወስድበት ጊዜ በጣም ቅርብ እንደሆነ ልንዘነጋው አይገባም። ይህ ቀን ከፊት ለፊታችን እንዳለ ነገር ወለል ብሎ ሊታየን ይገባል። (ሶፎንያስ 1:​7, 14)​—⁠9/1፣ ገጽ 19

◻ የዚህ ክፉ ሥርዓት የመጨረሻ ቀኖች ብዙዎች ከጠበቁት በላይ ረዥም የሆኑት ለምንድን ነው?

ይሖዋ ለመላው የሰው ዘር የሚበጁትን ነገሮች ያውቃል። እርሱ የሰዎች ሕይወት ጉዳይ ያሳስበዋል። (ሕዝቅኤል 33:​11) እንግዲያውስ እጅግ ጥበበኛና አፍቃሪ የሆነውን ፈጣሪ ዓላማ ለማሳካት መጨረሻው በትክክለኛው ጊዜ እንደሚመጣ እርግጠኞች ልንሆን እንችላለን።​—⁠9/1፣ ገጽ 22

◻ በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ የሚገኙ ወንድሞች ችግሮች ቢገጥሟቸውም ደስታቸውን ጠብቀው መቀጠል የሚችሉት እንዴት ነው?

ስላገኟቸው ብዙ በረከቶችና ከዚህ የከፋ ችግር ስለሚደርስባቸው በሺህ የሚቆጠሩ ወንድሞች መለስ ብለው በማሰብ ነው። (1 ጴጥሮስ 5:​6-9)​—⁠9/15፣ ገጽ 24

◻ ዊልያም ቲንደል መጽሐፍ ቅዱስን የተረጎመው በምን ዓላማ ነበር?

የቲንደል ዓላማ ቅዱሳን ጽሑፎች በተቻለ መጠን ትክክልና ግልጽ በሆነ ቋንቋ ለተራው ሕዝብ እንዲደርሱ ለማድረግ ነበር።​—⁠9/15፣ ገጽ 27

◻ የአምላክ ቃል ታማኝ ደጋፊዎች መሆናችንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

የአምላክን ቃል ለሌሎች በቅንዓት በመስበክ ለአምላክ ቃል ታማኝ ጠበቆች መሆናችንን ማሳየት እንችላለን። የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች እንደመሆናችን መጠን መጽሐፍ ቅዱስን በጥንቃቄ ልንጠቀምበት ይገባል። ከእኛ ሐሳብ ጋር እንዲስማማ ለማድረግ ብለን ማጣመም ወይም መለጠጥ በጭራሽ አይገባንም። (2 ጢሞቴዎስ 2:​15)​—⁠10/1፣ ገጽ 20

◻ የዓለም መርዘኛ መንፈስ ፍጹም አቋማችንን ሊያዳክም የሚችለው እንዴት ነው?

የዓለም መንፈስ ባሉን ነገሮች እንዳንረካና የአምላክን ሳይሆን የራሳችንን ፍላጎቶችና ጥቅሞች እንድናስቀድም ግፊት በማሳደር ፍጹም አቋማችንን ሊያዳክም ይችላል። (ከማቴዎስ 16:​21-23 ጋር አወዳድር።)​—⁠10/1፣ ገጽ 29

◻ ይሖዋን በሙሉ ነፍስ ማገልገል ማለት ምን ማለት ነው?

“ነፍስ” አካላዊና አእምሮአዊ ችሎታን ጨምሮ የአንድ ሰው ሁለንተና ማለት ነው። ይሖዋን በሙሉ ነፍስ ማገልገል ማለት ራሳችንን ማቅረብ፣ ችሎታችንን ሙሉ በሙሉ መጠቀምና የመጨረሻ ኃይላችንን ተጠቅመን እርሱን ማገልገል ማለት ነው። (ማርቆስ 12:​29, 30)​—⁠10/15፣ ገጽ 13

◻ በአምላካዊ መሠረታዊ ሥርዓት የሚመራ ሰው ለመ ሆን ቁልፉ ምንድን ነው?

ቁልፉ ይሖዋን፣ እርሱ የሚወዳቸውንና የሚጠላቸውን ነገሮች እንዲሁም ዓላማዎቹን ጠንቅቆ ማወቅ ነው። አምላክ ያወጣቸው እነዚህ መሠረታዊ ሥርዓቶች ሕይወታችንን እንዲቆጣጠሩ ስንፈቅድላቸው መሠረታዊ ሥርዓቶቹ ሕያው ይሆናሉ። (ኤርምያስ 22:​16፤ ዕብራውያን 4:​12)​—⁠10/15 ገጽ 29

◻ የይሖዋ አገልጋዮች ለሰብዓዊ አገዛዝ ያላቸው ሚዛናዊ አመለካከት ምንድን ነው?

የአምላክ መንግሥት አምባሳደሮች ወይም መልእክተኞች ሆነው ስለሚያገለግሉ በፖለቲካ ጉዳዮች ገለልተኞች ናቸው። (2 ቆሮንቶስ 5:​20) በአንጻሩ ደግሞ በሥልጣን ላይ ላሉት ሰዎች በሚገባ ይገዛሉ።​—⁠11/1፣ ገጽ 17

◻ ነቢዩ ኤልሳዕ ከተከተለው አካሄድ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን?

ምንም እንኳ አንዳንድ ሥራዎቹ ዝቅተኛ እንደሆኑ የሚቆጠሩ ቢሆኑም ከኤልያስ ጋር እንዲያገለግል ለልዩ አገልግሎት ግብዣ በቀረበለት ጊዜ ኤልሳዕ ወዲያውኑ እርሻውን ትቶ ኤልያስን ለማገልገል ሄደ። (2 ነገሥት 3:​11) በዛሬውም ጊዜ አንዳንድ የአምላክ አገልጋዮች ራቅ ባሉ ቦታዎች ምሥራቹን ለመስበክ ሲሉ ተመሳሳይ የሆነ ራስን የመሠዋት መንፈስ በማሳየት መተዳደሪያዎቻቸውን ትተዋል።​—⁠11/1፣ ገጽ 31

◻ የያዕቆብ ደብዳቤ ምን ጠቃሚ ምክር ይዟል?

ደብዳቤው ፈተናዎችን እንዴት መወጣት እንደምንችል ይገልጽ ልናል፣ አድሏዊ እንዳንሆን ይመክረናል፣ በመልካም ሥራዎች እንድንካፈል አጥብቆ ያሳስበናል። ያዕቆብ አንደበታችንን እንድንቆጣጠር፣ የዓለምን ተጽእኖዎች እንድንቋቋምና ሰላምን እንድንከተል ያሳስበናል። እንዲሁም ትዕግሥተኞች እንድንሆንና በጸሎት እንድንተጋ ይረዱናል።​—⁠11/15፣ ገጽ 24

◻ ይሖዋ “ይቅር ለማለት ዝግጁ” የሆነው ለምንድን ነው? (መዝሙር 86:​5 NW)

ይሖዋ ወዲያውኑ ይቅር የሚለን ከአፈር የተሠራን ደካማ ፍጡሮች ወይም በአለፍጽምና ምክንያት ጉድለቶች ያሉብን መሆናችንን ስለሚያስታውስ ነው። (መዝሙር 103:​12-14)​—⁠12/1፣ ገጽ 10, 11

◻ ሌሎችን ይቅር ለማለት ፈቃደኞች መሆን ያለብን ለምንድን ነው?

ይቅር ለማለት የሚያስችል ጥሩ ምክንያት እያለ ሌሎችን ይቅር ለማለት እንቢተኞች ከሆንን ከአምላክ ጋር ባለን ዝምድና ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል። (ማቴዎስ 6:​14, 15)​—⁠12/1፣ ገጽ 17

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ