እባክዎ ይህን ልዩ አጋጣሚ ከእኛ ጋር ያሳልፉ ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 11, 1998
አምላክ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ስጦታ አድርጎ ሰጥቶናል። የይሖዋ ምሥክሮች ይህን ስጦታ አብረዋቸው እንዲያስቡ ልባዊ ግብዣ ያቀርቡልዎታል። ይህ ስጦታ ሰዎች በምድር ላይ ለዘላለም ተደስተው የመኖር ተስፋ እንዲያገኙ በር ከፍቷል።—ዮሐንስ 3:16
በዚህ ዓመት የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ የሚከበረው በመጽሐፍ ቅዱስ የጨረቃ የቀን አቆጣጠር መሠረት ኒሣን 14 ማለትም ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 11 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ሚያዝያ 3) ቀን ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ይሆናል። እባክዎ ትክክለኛውን ቦታና ጊዜ በአቅራቢያዎ ከሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች ጠይቀው ይረዱ።