የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w98 6/15 ገጽ 32
  • የምድራችን የወደፊት ዕጣ ምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የምድራችን የወደፊት ዕጣ ምንድን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
w98 6/15 ገጽ 32

የምድራችን የወደፊት ዕጣ ምንድን ነው?

“ጭካኔ በተሞላበት የእርስ በርስ ጭፍጨፋ፣ በግጭቶች ብዛት፣ በከፍተኛ የስደተኞች ፍልሰት፣ በጦርነት በተገደሉት በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎችና ‘ለመከላከያ’ በተደረገው ከፍተኛ ወጪ ረገድ የትኛውም መቶ ዘመን ቢሆን 20ኛውን መቶ ዘመን አይተካከልም” በማለት ዎርልድ ሚሊተሪ ኤንድ ሶሻል ኤክስፔንዲቸርስ 1996 ዘግቧል። ይህ ሁኔታ የሚለወጥበት ጊዜ ይኖር ይሆን?

አምላክ ከብዙ መቶ ዘመናት በፊት የሰጠውን ተስፋ በመጥቀስ ሐዋርያው ጴጥሮስ ክርስቲያኖችን እንዲህ ሲል አስታውሷቸዋል:- “ነገር ግን ጽድቅ የሚኖርባትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደ ተስፋ ቃሉ እንጠብቃለን።” (2 ጴጥሮስ 3:​13) ይህ ሐሳብ በመጀመሪያ የኢሳይያስ ትንቢት ክፍል ነበር። (ኢሳይያስ 65:​17፤ 66:​22) የጥንቱ የእስራኤል ሕዝብ ለ70 ዓመታት በባቢሎን በግዞት ከቆየ በኋላ ተስፋ ወደ ተሰጠው ምድር ሲመለስ የዚህን ትንቢት የመጀመሪያ ፍጻሜ አይቷል። ጴጥሮስ ተስፋ ስለተሰጠበት “አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር” በድጋሚ በመናገር ትንቢቱ እንደገና በዓለም አቀፍ ደረጃ ታላቅ ፍጻሜውን እንደሚያገኝ አመልክቷል!

የአምላክ ፈቃድ በመላዋ ምድር ላይ ጽድቅ የሰፈነበት ሁኔታ እንዲቋቋም ሲሆን ይህንንም የሚያደርገው ክርስቶስ ንጉሥ ሆኖ በሚያስተዳድረው ሰማያዊ መንግሥቱ አማካኝነት ነው። “ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፣ ሰልፍም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም።” (ኢሳይያስ 2:​4) ኢየሱስ በተለምዶ አባታችን ሆይ ወይም የጌታ ጸሎት እየተባለ በሚጠራው በሚከተለው ጸሎት ውስጥ ተከታዮቹ እንዲጠብቁትና እንዲጸልዩለት ያስተማራቸው በምድር ላይ ስለሚሰፍነው እንዲህ ያለ ፍጹም ሰላምና ደህንነት ነው:- “መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን።”​—⁠ማቴዎስ 6:​9, 10

በሰማይ ያለው ዓይነት ጽድቅ የሚሰፍንበት ዓለም ውስጥ በመኖር ትደሰት ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ በሙሉ ልባቸው አምላክን ለማወቅና ከእሱ የጽድቅ መንገዶች ጋር ተስማምተው ለመኖር ለሚፈልጉ ሁሉ የያዘው ተስፋ ይህ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ