የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w99 8/15 ገጽ 29
  • ታስታውሳለህን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታስታውሳለህን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “አንባቢው ያስተውል”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ይሖዋን መታመኛችሁ አድርጉት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • ቤተሰቦች፣ የጉባኤው ክፍል በመሆን አምላክን አወድሱ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ሁሉም ሰው ነፃ ይሆናል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
w99 8/15 ገጽ 29

ታስታውሳለህን?

በቅርቡ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች ተግባራዊ ጠቀሜታ ያላቸው ሆነው አግኝተሃቸዋል? ከሆነ ቀጥሎ ባሉት ጥያቄዎች ተጠቅመህ ምን ያህሉን እንደምታስታውስ ለምን ራስህን አትፈትንም:-

◻ የሥራ ምርጫ የቀረበላቸው በርካታ ክርስቲያኖች የግል ውሳኔ እንዲያደርጉ የረዷቸው የትኞቹ ሁለት ጥያቄዎች ናቸው?

የመጀመሪያው ቁልፍ ጥያቄ እንዲህ ይላል:- ሰብዓዊ ሥራው ራሱ በመጽሐፍ ቅዱስ የተወገዘ ነውን? ሁለተኛው ጥያቄ እንዲህ ይላል:- አንድ ክርስቲያን ይህን ሥራ መሥራቱ ከተወገዘ ተግባር ጋር ተባባሪ ያደርገዋልን?​—4/15 ገጽ 28

◻ ‘ሰብዓዊው ፍጥረት ለከንቱነት የተገዛው’ በምን መንገድ ነው?

(ሮሜ 8:​20) ‘ለከንቱነት የተገዛነው’ የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ማለትም አዳምና ሔዋን በወሰዱት እርምጃ ምክንያት ነው። ይህ ወደን ‘በፈቃዳችን’ ያደረግነው ወይም በግለሰብ ደረጃ በግል የመረጥነው ነገር አይደለም። በውርስ ያገኘነው ነው። ምንም እንኳ የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ሊያስተላልፉልን የሚችሉት ከአለፍጽምና፣ ከኃጢአትና ሞት በቀር ሌላ ባይኖርም ይሖዋ ምሕረት በማሳየት ልጆች እንዲወልዱ ፈቅዶላቸዋል። ሞት ለሰው ሁሉ ስለደረሰ ከዚህ አንጻር አምላክ ‘ፍጥረት ለከንቱነት እንዲገዛ’ አድርጓል።​—⁠5/1 ገጽ 5

◻ ‘ርኩሰቱ’ ‘በተቀደሰ ስፍራ የሚቆምበት’ ጊዜ ወደፊት ይመጣል ብሎ ማሰቡ ምክንያታዊ የሆነው ለምንድን ነው? (ማቴዎስ 24:​15)

በጥንቱ ፍጻሜ መሠረት ‘የርኩሰቱ በተቀደሰ ስፍራ መቆም’ በጄኔራል ጋለስ የሚመራው የሮማ ሠራዊት በ66 እዘአ ጥቃት ከመሰንዘሩ ጋር የተቆራኘ ነበር። የዚህ ጥቃት ዘመናዊ አምሳያ የሆነው “ታላቅ መከራ” የሚጀምረው ገና ወደፊት ነው። (ማቴዎስ 24:​21) ስለዚህ ‘የጥፋት ርኩሰት’ በተቀደሰው ስፍራ ላይ የሚቆመው ገና ወደፊት ነው።​—⁠5/1 ገጽ 16, 17

◻ ሰብዓዊ ሥራ ያላቸው አንድ አባትና እናት ከልጆቻቸው ጋር የሚያሳልፉት ጊዜ ማግኘት የሚችሉት እንዴት ነው?

ከቀኑ የሥራ ውሎ በኋላ ድካም የሚሰማት እናት ልጆችዋ አብረዋት ምግብ እንዲያዘጋጁ ልትጠይቃቸው ትችላለች። ቅዳሜና እሁድ ላይ የሚሠሩ በርካታ ሥራዎች ያሉት አባት ደግሞ አንዳንዶቹን ሥራዎች ከልጆቹ ጋር መሥራት ይችላል።​—⁠5/15 ገጽ 6

◻ ‘በይሖዋ መንገድ የሚሄዱ’ ሰዎች ማድረግ ያለባቸው ነገር ምንድን ነው? (ኤርምያስ 7:​23)

በይሖዋ መንገድ መመላለስ ታማኝ መሆን ማለትም እርሱን ብቻ ለማገልገል ቁርጥ ውሳኔ ማድረግን ይጠይቃል። በይሖዋ ላይ መታመንንም ይጨምራል፤ ይኸውም ይሖዋ የሰጠው ተስፋ እምነት የሚጣልበት እንደሆነና ፍጻሜውን እንደሚያገኝ ሙሉ በሙሉ ማመን ማለት ነው። በይሖዋ መንገድ መመላለስ ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ ሳይሉ ሕግጋቱን በመከተልና ከፍተኛ የአቋም ደረጃዎቹን በመጠበቅ መታዘዝን ይጠይቃል። (መዝሙር 11:​7)—⁠5/15 ገጽ 14

◻ ‘ስጦታ የሆኑ ወንዶች’ የሚያሟሏቸው አራት ዐበይት ኃላፊነቶች ምንድን ናቸው? (ኤፌሶን 4:​8)

በርኅራኄ ያስተካክሉናል፣ በፍቅር ይገነቡናል፣ ከጉባኤው ጋር ያለን አንድነት እንዲጠበቅ ያደርጋሉ እንዲሁም በድፍረት ከአደጋ ይጠብቁናል። (ኤፌሶን 4:​12-14)—⁠6/1 ገጽ 14

◻ ጳውሎስ በሐዋርያት ሥራና እርሱ በጻፋቸው ደብዳቤዎች ላይ ከተጠቀሱት አንድ መቶ ከሚያክሉ ሰዎች ጋር ከነበረው ጓደኝነት ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን?

ሁልጊዜ ከአምላክ ድርጅት፣ በአካባቢያችን ከሚገኘው ጉባኤና ከመሰል አማኞች ጋር ሆነን መሥራት አለብን። በጥሩም ሆነ በአስቸጋሪ ጊዜ የእነርሱ እርዳታ፣ ድጋፍና ማበረታቻ ያስፈልገናል።​—⁠6/1 ገጽ 31

◻ ሌሎች ስለ ፈጣሪ እንዲያስቡ ለመርዳት የትኞቹን ሦስት ነጥቦች መጠቀም እንችል ይሆናል?

በጣም ግዙፍ በሆነው ጽንፈ ዓለም ውስጥ የሚታየውን የማይዛባ ሥርዓት፣ በምድር ላይ ያለውን ሕይወት አመጣጥና የተለያዩ ነገሮችን ማከናወን የሚችለውን ልዩ የሆነ የሰው አንጎል።​—⁠6/15 ገጽ 18

◻ የፈጣሪ የግል ስም የያዘውን ትርጉም መረዳት እጅግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

የአምላክ ስም “እንዲሆን የሚያደርግ” የሚል ትርጉም ያለው ከመሆኑም በላይ ዓላማ አውጪና አስፈጻሚ መሆኑንም ጎላ አድርጎ ይገልጻል። ስሙን በማወቅና በመጠቀም የሰጠውን ተስፋ የሚፈጽምና ዓላማውንም ሙሉ በሙሉ እውን የሚያደርግ መሆኑን በተሻለ መንገድ ለመረዳት እንችላለን።​—⁠6/15 ገጽ 21

◻ ልጆች በቤተሰብ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

በተቻለ መጠን እያንዳንዱ ልጅ የራሱ መጽሐፍ ቅዱስና የሚጠናው ጽሑፍ ቅጂ እንዲኖረው ዝግጅት አድርጉ። በወጣትነት ዕድሜ ላይ የሚገኝ ልጅ በሚጠናው ጽሑፍ ላይ ያለውን ሥዕል እንዲያብራራ ሊጠየቅ ይችላል። ሌላ ትንሽ ልጅ ደግሞ አንድ ጥቅስ እንዲያነብ አስቀድሞ ሊመደብ ይችላል። በዕድሜ ከፍ ያለ ልጅ ደግሞ እየተጠና ያለው ትምህርት በየትኞቹ ወቅቶች ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል ማብራሪያ እንዲሰጥ ሊመደብ ይችላል።​—⁠7/1 ገጽ 15

◻ አንድ ቤተሰብ ለጉባኤ ስብሰባዎች በመዘጋጀት ረገድ ሊያካትታቸው የሚችለው አንዳንድ ግቦች ምንድን ናቸው?

(1) እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ሐሳብ ለመስጠት ዝግጁ መሆን፤ (2) በራሱ አነጋገር ለመመለስ ጥረት ማድረግ፤ (3) በመልሱ ውስጥ ጥቅሶችን ማከል እንዲሁም (4) ትምህርቱን በግለሰብ ደረጃ ተግባራዊ ማድረግን ግብ በማድረግ ማብላላት።​—⁠7/1 ገጽ 20

◻ ለተሳካ ትዳር ቁልፉ ምንድን ነው?

የተሳካ ትዳርን በር ለመክፈትና ከፍተኛ ደስታ ለማግኘት አንድ አስፈላጊ ነገር ጥሩ የሐሳብ ግንኙነት ነው። ይህ ስሜትንና ሐሳብን ማካፈልን ይጨምራል። እንዲሁም ጥሩ የሐሳብ ግንኙነት የሚያንጹ፣ መንፈስን የሚያድሱ፣ በጎ፣ ጥሩና የሚያጽናኑ ነገሮችን መናገርን ያጠቃልላል። (ኤፌሶን 4:​29-32፤ ፊልጵስዩስ 4:​8)—⁠7/15 ገጽ 21

◻ ‘የይሖዋ መንገድ’ ምንድን ነው? (መዝሙር 25:​8, 9, 12)

ይህ መንገድ የፍቅር መንገድ ነው። አምላክ ካወጣቸው መሥፈርቶች ጋር በመስማማት ትክክል የሆነውን ነገር በማድረግ ላይ የተመሠረተ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ይህን በመሠረታዊ ሥርዓት የሚመራ ፍቅር “ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ” ይለዋል። (1 ቆሮንቶስ 12:​31)—⁠8/1 ገጽ 12

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ