የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w04 2/1 ገጽ 2-4
  • መንፈሳዊነትና ጤንነትህ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መንፈሳዊነትና ጤንነትህ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ቀጥተኛ ተዛምዶ
  • መንፈሳዊነት ምንድን ነው? መንፈሳዊ ለመሆን የግድ የአንድ ሃይማኖት አባል መሆን ያስፈልገኛል?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2019
  • መንፈሳዊነትን ለማግኘት የሚደረግ ጥረት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • መንፈሳዊ ፍላጎትህን ማርካት የምትችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
w04 2/1 ገጽ 2-4

መንፈሳዊነትና ጤንነትህ

አካላዊ ጤንነትህን ለመጠበቅ ብዙ ጊዜ ታጠፋ ይሆናል። በየቀኑ ስምንት ሰዓት ያህል በእንቅልፍ፣ በርከት ያሉ ሰዓታት ምግብ በማብሰልና በመመገብ እንዲሁም ለቀለብ መሸመቻና ለመኖሪያ የምትከፍለው ገንዘብ ለማግኘት ስምንት ሰዓት ወይም ከዚያ በላይ ታጠፋለህ። ብትታመም ሐኪም ቤት ለመሄድ ወይም ባሕላዊ መድኃኒት ለማዘጋጀት ጊዜና ገንዘብ ማጥፋትህ አይቀርም። ጤናማ ለመሆን ስትል ቤትህን ታጸዳለህ፣ ሰውነትህን ትታጠባለህ እንዲሁም አዘውትረህ አካላዊ እንቅስቃሴ ታደርግ ይሆናል።

ይሁን እንጂ ጤናማ ለመሆን አካላዊ ፍላጎቶችህን ከማሟላት የበለጠ ነገር ማድረግ ያስፈልግሃል። በጤንነትህ ረገድ ጉልህ ሚና የሚጫወት ሌላም ነገር አለ። አካላዊ ጤንነትህ ከመንፈሳዊ ጤንነትህ ጋር በቅርብ የተሳሰረ መሆኑን የሕክምና ጥናት አሳይቷል።

ቀጥተኛ ተዛምዶ

የአውስትራሊያው ሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ሄድሊ ፒች “በዚህ መስክ የተደረጉ ጥናቶች ጥሩ መንፈሳዊ አቋም የተሻለ ጤንነት ከማግኘት ጋር ቀጥተኛ ተዛምዶ እንዳለው አሳይተዋል” በማለት ተናግረዋል። ዘ ሜዲካል ጆርናል ኦቭ አውስትራሊያ የተባለው መጽሔት በዚህ ግኝት ላይ ሐሳብ ሲሰጥ “ሃይማኖታዊ ሰው መሆን . . . የደም ግፊት፣ የስብ መጠን . . . እንዲሁም በደንዳኔ ካንሰር የመያዝ አጋጣሚ እንዲቀንስ አስተዋጽኦ ያደርጋል” ብሏል።

በተመሳሳይም በ2002፣ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በርክሌይ የሚገኘው የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ በ6,545 ሰዎች ላይ ባደረገው ጥናት “በሳምንት አንድ ጊዜ ሃይማኖታዊ ፕሮግራሞች ላይ የሚገኙ ሰዎች እምብዛም ቤተ ክርስቲያን ከማያዘወትሩት ወይም ጨርሶ ከማይሄዱት ሰዎች በተለየ መልኩ ረዥም ዕድሜ እንዳላቸው” ደርሶበታል። በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ፣ በርክሌይ በሚገኘው የሕዝብ ጤና ትምህርት ቤት የሚካሄደው ጥናት መሪና መምህር የሆኑት ደግ ኦማን “ማህበራዊ ግንኙነትን እንዲሁም እንደማጨስና የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ ያሉትን ጤናን የሚነኩ ነገሮች ሁሉ ከግምት ካስገባን በኋላም ጭምር እንደዚህ ዓይነት ልዩነት አይተናል” ብለዋል።

ዘ ሜዲካል ጆርናል ኦቭ አውስትራሊያ ስለ ሕይወት መንፈሳዊ አመለካከት ያላቸው ሰዎች የሚያገኟቸውን ሌሎች ጥቅሞችም ሲጠቁም እንዲህ ይላል:- “በአውስትራሊያ የተደረጉ ጥናቶች ሃይማኖታዊ የሆኑት ሰዎች ትዳራቸው የሰከነ እንደሆነ፣ የአልኮል መጠጥና አደገኛ ዕጽ እምብዛም እንደማይወስዱ፣ በአብዛኛው የራሳቸውን ሕይወት እንደማያጠፉና ብዙዎቹ የራሳቸውን ሕይወት ማጥፋትን እንደ አማራጭ አድርገው እንደማይመለከቱት፣ ጭንቀትና ውጥረት ብዙም እንደማያጋጥማቸው፣ እንዲሁም ለሌሎች ደህንነት በጣም አሳቢ እንደሆኑ አሳይተዋል።” በተጨማሪም ቀደም ሲል ዘ ብሪቲሽ ሜዲካል ጆርናል ተብሎ ይጠራ የነበረው መጽሔት “ጠንካራ መንፈሳዊ እምነት እንዳላቸው የሚናገሩ ሰዎች መንፈሳዊ እምነት ከሌላቸው ሰዎች በተለየ መልኩ የሚወዱት ሰው ሲሞትባቸው ከሐዘናቸው ቶሎ የሚጽናኑ ይመስላል” ብሏል።

እውነተኛ መንፈሳዊነት ምን ማለት ነው የሚለውን ጉዳይ በተመለከተ የተለያዩ አመለካከቶች አሉ። ሆኖም መንፈሳዊ ሁኔታህ በአካላዊና በአእምሯዊ ጤንነትህ ላይ ተጽዕኖ አለው። ይህ ሐቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከ2,000 ዓመት ገደማ በፊት ከተናገረው ነገር ጋር ይስማማል። ኢየሱስ “ለመንፈሳዊ ፍላጎታቸው ንቁ የሆኑ ደስተኞች ናቸው” ብሏል። (ማቴዎስ 5:3 NW) መንፈሳዊ ሁኔታህ በጤንነትህና በደስታህ ላይ ተጽዕኖ ስላለው ‘እምነት የሚጣልበት መንፈሳዊ መመሪያ ከየት ላገኝ እችላለሁ? መንፈሳዊ ሰው መሆን ምን ነገሮችን ይጨምራል?’ ብሎ መጠየቁ ምክንያታዊ ነው።

[በገጽ 2 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

Photo Credits: Page 18: Mao Tse-tung and Golda Meir: Hulton/Archive by Getty Images; Francis Ferdinand: From the book The War of the Nations; Hirohito, Lindbergh, & Einstein: U.S. National Archives photo; Stalin: U.S. Army photo; Roosevelt: Franklin D. Roosevelt Library; Churchill: The Trustees of the Imperial War Museum (MH 26392)

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ