የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w07 4/1 ገጽ 31
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በሰራፕታ የነበረችው መበለት ያሳየችው እምነት ክሷታል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • የአንዲት ድሃ ሴት ልጅ ከሞት ተነሳ
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ጢሞቴዎስ ‘በእምነት እውነተኛ ልጅ የሆነ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ባልና ሽማግሌ ኃላፊነቶቹን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ መወጣት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
w07 4/1 ገጽ 31

የአንባቢያን ጥያቄዎች

ጳውሎስ፣ አንዲት መበለት ከክርስቲያን ጉባኤ እርዳታ ለማግኘት ብቁ እንድትሆን “የአንድ ባል ሚስት የነበረች” መሆን እንዳለባት ሲገልጽ ምን ማለቱ ነበር?—1 ጢሞቴዎስ 5:9

ሐዋርያው ጳውሎስ “የአንድ ባል ሚስት የነበረች” ሲል ይህች እህት መበለት ከመሆኗ በፊት የነበራትን ሁኔታ ለማመልከት እንደሆነ ግልጽ ነው። ይህ ሲባል ይህች መበለት አንድ ጊዜ ብቻ ያገባች መሆን እንዳለባት መግለጹ ነው? ወይስ ጳውሎስ የተናገረው ነገር ሌላ ትርጉም ሊኖረው ይችላል?a

አንዳንዶች፣ ጳውሎስ እየተናገረ ያለው አንድ ጊዜ ብቻ ስላገቡ እህቶች እንደሆነ ይገልጻሉ። እርግጥ ነው፣ በበርካታ ባሕሎችና ማኅበረሰቦች ውስጥ ባሏ ከሞተ በኋላ ድጋሚ ሳታገባ የምትኖር ሴት ጥሩ እንዳደረገች ይታሰብ ነበር። ሆኖም ይህ ዓይነቱ አመለካከት ጳውሎስ በሌላ ደብዳቤው ላይ ከጻፈው ሐሳብ ጋር ይጋጫል። ለምሳሌ በቆሮንቶስ ለነበሩት ክርስቲያኖች በጻፈው ደብዳቤ ላይ በእርሱ አመለካከት፣ አንዲት መበለት ሳታገባ ብትኖር ደስተኛ እንደምትሆን ገልጿል፤ ሆኖም እንደገና ትዳር ለመመሥረት ከፈለገች “የፈለገችውን ሰው ለማግባት ነጻነት አላት፤ ሰውየው ግን በጌታ መሆን አለበት” በማለት በግልጽ ተናግሯል። (1 ቆሮንቶስ 7:39, 40፤ ሮሜ 7:2, 3) ከዚህም በተጨማሪ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ሲጽፍ “ባል የሞተባቸው ወጣት ሴቶች እንዲያገቡ . . . እመክራለሁ” ብሏል። (1 ጢሞቴዎስ 5:14) በመሆኑም አንዲት መበለት እንደገና ለማግባት ብትመርጥ አትነቀፍም ነበር።

ታዲያ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ በጻፈው ደብዳቤ ላይ ከላይ ያለውን ሲናገር ምን ማለቱ ነበር? “የአንድ ባል ሚስት የነበረች” የሚለው አባባል የሚገኘው በዚህ ጥቅስ ላይ ብቻ ነው። ጥቅሱ መጀመሪያ በተጻፈበት ቋንቋ፣ ይህ ሐረግ ቃል በቃል ሲተረጎም “የአንድ ወንድ ሴት” ማለት ነው። ይህ አባባል ደግሞ ጳውሎስ በደብዳቤው ላይ በተደጋጋሚ ከተጠቀመበት “የአንዲት ሚስት ባል” ወይም በግሪክኛው “የአንዲት ሴት ወንድ” ከሚለው አገላለጽ ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ትኩረት የሚስብ ነው። (1 ጢሞቴዎስ 3:2, 12፤ ቲቶ 1:6) ጳውሎስ፣ ክርስቲያን የበላይ ተመልካቾችና የጉባኤ አገልጋዮች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ብቃቶችን ሲዘረዝር “የአንዲት ሚስት ባል” የሚለውን አገላለጽ ተጠቅሞበታል። በዚያ ጥቅስ ላይ ይህ አባባል በዋነኝነት የተሠራበት፣ አንድ ያገባ ወንድ በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ኃላፊነት ለመሸከም ብቁ እንዲሆን ለሚስቱ ታማኝና በሥነ ምግባር ረገድ የማይነቀፍ መሆን እንዳለበት ለመግለጽ ነው።b በመሆኑም በ1 ጢሞቴዎስ 5:9 ላይ የሚገኘው አባባልም ተመሳሳይ ትርጉም አለው:- አንዲት መበለት በጉባኤ ውስጥ እርዳታ ለማግኘት ብቁ እንድትሆን ባሏ በሕይወት በነበረበት ወቅት ባሏን የምትወድ ታማኝ ሚስት የነበረች እንዲሁም በሥነ ምግባር ረገድ የማትነቀፍ መሆን ይኖርባታል። ጳውሎስ በቀጣዮቹ ቁጥሮች ላይ የዘረዘራቸው ሌሎቹ ብቃቶች በሙሉ እንደዚህ ዓይነት ምግባር ስላላት መበለት የሚገልጹ ናቸው።—1 ጢሞቴዎስ 5:10

[የግርጌ ማስታወሻዎች]

a ፖሊያንድሪ በመባል የሚታወቀው በአንድ ጊዜ ብዙ ባሎች የማግባት ልማድ በጳውሎስ ዘመን በነበረው የግሪካውያንና የሮማውያን ማኅበረሰብ ውስጥ ተቀባይነት አልነበረውም። በመሆኑም ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ በጻፈው ደብዳቤ ላይ ስለዚህ ዓይነቱ ልማድ እየተናገረ ወይም እንዲህ የሚያደርግን ሰው እያወገዘ ነበር ማለት አይቻልም።

b በዚህ ነጥብ ላይ ማብራሪያ ለማግኘት መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 15, 1996 ገጽ 17 እንዲሁም መስከረም 15, 1980 (እንግሊዝኛ) ገጽ 31 ላይ የሚገኘውን “የአንባቢያን ጥያቄዎች” ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ